17/12/2023
የሚሌ ወረዳ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤት ከሉሲ የተቀናጀ የልማት ማህበር ጋር በመተባበር በዛሬው እለት ከወረዳ ሴክተር ፅ/ቤቶች ለተመረጡ ባለሙያዎች እና ከቀበሌ ለተውጣጡ የማህበረሰብ ተወካዬች ማለትም የሀ/አባቶች ፣ የቀበሌ ሊቀመንበሮች እና አወላጆች (ኡለቲና)በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ - ልማዳዊ ድርጊቶች በተለይ የሴት ልጅ ግርዛት እና ፆታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን መከላከል የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል
14/11/2023
በዛሬው እለት በቀን 04/03/2016 የሚሌ ወረዳ ሴ/ማ/ጉ/ፅ/ቤት እና የሚሌ ወረዳ ጤና ፅ/ቤት በጋራ ከኬር ኢትዩጲያ ጋር በመተባበር በ12ቱም ቀበሌዎች የሚገኙ የእናቶች ለእናቶች የውይይት ቡድን እና ከጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ጋር በእናቶች እና ህፃናት ጤና አጠባበቅ፣ በነብሰጡር እናቶች ጤና ዙሪያ ፣ የሴት ልጅ ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን መከላከል ዙሪያ በውይይት ሂደት ውስጥ ስለተከናወኑ ስራዎች ያጋጠሙአቸውን ችግሮችና አካባቢያዊ መፍትሄዎች እና ቀጣይ አቅጣጫዎችን በተመለከተ ውጤታማ የሆነ ውይይት ተደርጓል ስራዎችንም አጠናክረን መቀጠል እንዳለብን በመግባባት የእለቱ ውይይት ተጠናቋል።