Żack Ĥaběśĥãŵĩ የፍቅር ሰው
እውነተኛ ፍቅር ያሸንፋል እንጅ አይሸነፍም
Traditional Restaurant
22/05/2026
የአለም አቀፉ የሶሻል ሚዲያ ኮከብ ዲላን ፔጅ (Dylan Page) እና ታዋቂው አዶኒ (Adoney) በአዲስ አበባ!
የዲጂታል ሚዲያው አለም ትኩረት አዲስ አበባ ላይ
ሁለቱ ታዋቂ ግለሰቦች የአዲስ አበባን ውበት፣ ባህልና ታሪካዊ እሴቶች ለአለም ለማስተዋወቅ ያለመ ረጅም የከተማ ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ።
ይህ ጉብኝት አዲስ አበባ በፈጣን ሁኔታ የአፍሪካ የዲጂታል ፈጣሪዎች ማዕከል (Global Creator Hub) እየሆነች መምጣቷን የሚያሳይ ትልቅ ማረጋገጫ ነው።
የከተማ ጉብኝቱን ተከትሎ፣ ዛሬ ምሽት 12:00 ሰዓት ጀምሮ በታዋቂው ቶቶት ባህላዊ ምግብ ቤት ልዩ የራት ፕሮግራም ተዘጋጅቷል።
ይህ ፕሮግራም የሀገራችንን ባህላዊ ምግቦች፣ ሙዚቃና መስተንግዶ ለዓለም አቀፉ እንግዳ ለማስተዋወቅ ታላቅ እድል ይፈጥራል።
በዚህ ልዩ የራት ፕሮግራም ላይ ለመሳተፍ ጥሪ የተደረገላቸው 100 የሚሆኑ ታዋቂ የኢትዮጵያ አንጋፋና ወጣት ኢንፍሉዌንሰሮች (Influencers) ይገኙበታል።
👏👏👏
ጉርሻ page
🌴🌴🌴
There is a factory burning on Dayal Road in Clairwood,
07/05/2026
ሰበር ዜና |
ጋና ለአፍሪካ ህብረት በደቡብ አፍሪካ ላይ የዜኖፎቢያ ጥቃቶችን አጀንዳ እንዲሆኑ ጠየቀች
ጋና የአፍሪካ ኩራት 🙏🏾🙏🏾🙏🏾🙏🏾🙏🏾
የጋና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በ6 ሜይ 2026 በወጣ ደብዳቤ፣ በደቡብ አፍሪካ በአፍሪካውያን ላይ እየተፈጸሙ ናቸው ያለቻቸውን የዜኖፎቢያ ጥቃቶች በአፍሪካ ህብረት 8ኛው የአማካይ ዓመት ኮርዲኔሽን ስብሰባ አጀንዳ ላይ እንዲካተቱ ጠይቃለች።
ደብዳቤው እንደሚገልጸው፣ በደቡብ አፍሪካ የሚከሰቱ የውጭ ዜጎችን የሚያነጣጥሩ ጥቃቶች የሰው ሕይወት መጥፋት፣ የንብረት ውድመት እና በሀገሪቱ የሚኖሩ አፍሪካውያን ላይ ከፍተኛ የደህንነት ስጋት ፈጥረዋል ተብሏል።
የጋና መንግስት በመግለጫው፣ እነዚህ ጥቃቶች የአፍሪካ አንድነትን፣ የፓን-አፍሪካኒዝም መንፈስን እና የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና (AfCFTA) ዓላማዎችን የሚጎዱ መሆናቸውን ገልጿል።
በተጨማሪም ጋና፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን በዚህ ጉዳይ ላይ አስቸኳይ ውይይት እንዲያካሂድ እና የአፍሪካ ዜጎች ደህንነት እንዲጠበቅ እርምጃ እንዲወስድ ጥሪ አቅርባለች።
07/05/2026
ማንዴላ ኢትዮጵያዊ ነበር
ዳቪድ ሞቲስማይ "ኢትዮጵያዊው" ጋዜጠኛ።
...
ይህ በቀዳማዊ ሀይለስላሴ ዘመነ መንግስት ለአንድ ሰው ተሰጥቶ የነበረ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ነው።
በፓስፖርቱ ላይ የተጻፈው
ስም ዳቪድ ሞቲስማይ
ስራ - ጋዜጠኛ
ዜግነት - ኢትዮጵያዊ ይላል።
......
እውነታውስ ካልን ፡ ሰውየው ስሙ ዳቪድ አይደለም ፡ በጋዜጠኝነት ስራም ተሰማርቶ አያውቅም ፡ ሌላው ቀርቶ በፓስፖርቱ ላይ እንደተጻፈው ዜግነቱ ኢትዮጵያዊም አልነበረም።
.....
በቀዳማዊ ሀይለስላሴ ትእዛዝ ለዚህ ሰው ይህ ፓስፖርት የተሰጠው ለአንድ ትልቅ አላማ ነበር።
ለአንድ ሀገር ነጻነት. ... አንድን ሀገር ከአፓርታይድ አገዛዝ ለማላቀቅ የሚደረገውን ትግል ለማገዝ ሲባል ነበር ይህ ፓስፖርት ለዚህ ሰው የተሰጠው።
....
እንጂ ሰውየው ደቡብ አፍሪካዊ እንጂ ኢትዮጵያዊም አልነበረም ፡ ስራውም ጋዜጠኛም አይደለም ፡ እውነተኛ ስሙም ዳቬድ ሞቲስሞይ ሳይሆን ፡ ኔልሰን ማንዴላ ይባል ነበር።
.....
የያኔው የነጻነት ታጋይ ወጣቱ ኔልሰን ማንዴላ ፡ ሀገሩ በአፓርታይድ አገዛዝ በነበረችበት ወቅት ፡ በድብቅ ከደቡብ አፍሪካ በመውጣት አዲስ አበባ ሲደርስ ፡ የኢትዮጵያ መንግስት የማንዴላን ደህንነት ለመጠበቅና ወደተለያዩ ሀገራት ተንቀሳቅሰው ድጋፍ ለመጠየቅ እንዲረዳቸው ነበር ይህን የኢትዮጵያን ፓስፖርት የሰጣቸው።
.....
ይህ ለማንዴላ የተሰጣቸው ፓስፖርት ማንዴላ ከኢትዮጵያ ወደ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት እንደ ግብፅ ሞሮኮ እና አልጄሪያ እንዲሁም ወደ አውሮፓ እንዲጓዙ አስችሏቸዋል።
ኔልሰን ማንዴላ ወደ ደቡብ አፍሪካ ሲመለሱም ይህንኑ ፓስፖርት ይዘው ነበር የገቡት። በኋላም በቁጥጥር ስር ሲውሉ ፓስፖርቱ ከመረጃዎቻቸው መካከል ተገኝቷል።
.....
ኢትዮጵያ ለማንዴላ ፓስፖርትና የተለያዩ ጉዞዎችን ማመቻቸት ብቻ አይደለም ፡ ወታደራዊ ስልጠና ያገኙትም እዚህ ነው።
...
ይህ ብቻ አይደለም። ኢትዮጵያ በዘመነ አፓርታይድ ስርአቱ እንዲገረሰስ ጠንካራ የሆነ ዲፕሎማሲያዊ ትግል ስታካሂድም ነበር።
....
ታዲያ. .. በዘመነ አፓርታይድ ይህን ሁሉ ነገር ያደረገችው ኢትዮጵያ ዛሬ ዜጎቿ በደቡብ አፍሪካ ሰዎች ሲ7ደሉ ማየትና መስማት ያሳዝናል።
...
ለነገሩ ደቡብ አፍሪካውያን አሁንም ድረስ ከዛ ዘመን ሜንታሊቲ አልተላቀቁም። ዛሬም ነጮች የበላይ እንደሆኑ የሚያምኑ ህዝቦች ናቸው። ለነሱ ጠላት መስሎ የሚታያቸው ጥቁሩ ነው።
....
አስገራሚው ነገር ሳንድቶን አካባቢ ያሉ የሀብታም ሰፈሮች በብዛት በነጮች የተያዙ ናቸው። እና ጥቁሮቹ ደቡብ አፍሪካውያን ብዙ ጊዜ ወደነዚህ አካባቢዎች አይሄዱም ፡ ቢሄዱም ደግሞ እንደ እንግዳ ተሳቀው ነው።
ደቡብ አፍሪካውያን ወደነዚህ ሰፈሮች ሲሄዱ የሚሳቀቁት ማንም ተቆጥቷቸው ፡ ማንም አትሂዱ ብሏቸው አይደለም። በቃ አእምሯቸው ራሱ ይህንን ተቀብሎታል። በግልፅም ባይሆን በድብቅ ከነሱ እኩል እንዳልሆኑ ያምናሉ። እና ይህን የበታችነት ስሜት የሚወጡት አፍሪካውያን ወንድሞቻቸው ላይ ጭካኔ በማሳየት ነው።
©Wasihune Tesfaye
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Telephone
Address
Durban
