Mayor office of Bahir Dar

Mayor office of Bahir Dar ይህ የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት ገፅ ነው። ከተማችን ውቢቱ ባህር ዳር እነደ ስሟ የተዋበች እና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለጎብኝዎቿ የምትናፍቅ እንድትሆን እንሰራለን።
" Smart City, Bright Future "

የባሕርዳር ከተማ ምክርቤት የ2019 በጀት ዓመት 16 ቢሊዮን 289 ሚሊዮን 212 ሺህ 513 ብር  መርምሮ አጽድቋል። ጥቅምት 24/2019 ዓ.ም (ባሕር ዳር ከተማ ኮሙዩኒኬሽን)፦ የባሕር ዳ...
03/11/2026

የባሕርዳር ከተማ ምክርቤት የ2019 በጀት ዓመት 16 ቢሊዮን 289 ሚሊዮን 212 ሺህ 513 ብር መርምሮ አጽድቋል።

ጥቅምት 24/2019 ዓ.ም (ባሕር ዳር ከተማ ኮሙዩኒኬሽን)፦ የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 4ኛ ዙር፣ 14ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፣ በ33ኛ መደበኛ ጉባኤው የቀረበውን ዕቅድና 16 ቢሊዮን 289 ሚሊዮን 212 ሺህ 513 ብር የበጀት መጠን መርምሮ አጽድቋል።

የባሕር ዳር ከተማ ከንቲባ አቶ ጎሹ እንዳላማው እንደተናገሩት በ2019 በጀት ዓመት ባሕርዳር ከተማን የበለጠ ውብ፣ጽዱ፣ አረንጓዴ ለነዋሪዎች እና ለጎብኝዎቿ የምትመች ተመራጭ ከተማ ለማድረግ በመንግሥት፣ በህብረተሰብ ተሳትፎ እና በአጋር አካላት ዘርፈ ብዙ ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ክቡር ከንቲባ እንደገለጹት በከተማዋ የሰላም፣ የልማትና የመልካም አስተዳድር ስራዎች በላቀ ስኬት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ማሕበረሰቡን ያሳተፈ የልማት ተግባር ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ አሳስበዋል።

በጉባኤው የዕለት ውሎ፤ የባሕርዳር ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት መምሪያ ሀላፊ አቶ ቶማስ ታምሩ የ2019 በጀት ዓመት መሪ እቅድ አቅርበዋል። በተመሳሳይ የባሕርዳር ከተማ ገንዘብ መምሪያ ሀላፊ ወ/ሮ አጸደ ምንዋጋው በመንግስት፣በህብረተሰብ ተሳትፎ እና በአጋር አካላት የሚከናወኑ ፕሮጀክቶችን አቅርበዋል።

"በአንድ እጅ ሰላምን በሌላ እጅ ደግሞ ልማትን ማስቀጠል ይገባል" አቶ ጎሹ እንዳላማውየባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ምክር ቤት 4ኛ ዙር፣ 14ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፣ 33ኛ መደበኛ ጉባኤውን እ...
03/11/2026

"በአንድ እጅ ሰላምን በሌላ እጅ ደግሞ ልማትን ማስቀጠል ይገባል" አቶ ጎሹ እንዳላማው

የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ምክር ቤት 4ኛ ዙር፣ 14ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፣ 33ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው።

የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው የተጀመረውን ሀገራዊ ለውጥ ዘላቂነት ለማረጋገጥ የሰላም፣ የጸጥታ እና የልማት ሥራዎችን በውጤታማነት መፈጸም ወሳኝ መኾኑን አመላክተዋል።

በልማት ሂደት ውስጥ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን ለመቋቋም በአንድ እጅ ሰላምን በሌላ እጅ ደግሞ ልማትን ማስቀጠል እንደሚገባም ገልጸዋል።

ባለፈው በጀት ዓመት በከተማዋ የተገኙ የሰላም እና የልማት ውጤቶችን መነሻ በማድረግ ሕዝብን ተጠቃሚ ለማድረግ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች፣ የፈጠራ ሥራዎች እና ዕውቀት ጥቅም ላይ መዋላቸውን ነው የተናገሩት።

በቅንጅት የውስጥ ሰላምን በማረጋገጥ እና አዳዲስ አሠራሮችን በመዘርጋት በሁሉም ተቋማት መልካም ውጤቶችን ማስመዝገብ ተችሏል ብለዋል።

የሥራ አጥ ቁጥርን ለመቀነስ አዳዲስ ኢንተርፕራይዞችን በማቋቋም እና ነባሮችን በማጠናከር፣ የመንገድ መሰረተ ልማቶችን እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በማከናወን ረገድ ውጤታማ ሥራዎች ተሠርተዋል ነው ያሉት።

በከተማ ግብርና በተለይ የሌማት ቱፋትን ተግባራዊ ማድረግ፣ የደን ልማት እና የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ሥራን ማስቀጠል፣ የበጋ መስኖ ስንዴ እና ሌሎች የአትክልት እና ፍራፍሬ ልማት ሥራ በሰፊው ተከናውኗል ብለዋል።

ሕገ ወጥ ግንባታ እና የጎዳና ላይ ንግድን የመከላከል፣ በእንስሳት እና ዓሳ ሀብት ሥራዎች ላይ የተሻለ ውጤት የማስመዝገብ፣ ከተማዋን መልሶ የማልማት፣ የማስዋብ፣ ለነዋሪዎች ምቹ የማድረግ ሥራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።

ምቹ የኢንቨስትመንት ምኅዳርን ለመፍጠርም በትኩረት መሠራቱን ጠቁመዋል።

!

! 🇪🇹



✍️ በስማቸው አጥናፍ

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የተሻሻለው የመንግስት ሠራተኞችን አዋጅ ለመደንገግ የወጣ አዋጅ (አዋጅ ቁጥር ፫፻፱ /፪ሺ፲፰)የቀጠለባሕር ዳር፡- ጥቅምት፣ 24/2019ዓ.ም           ...
03/11/2026

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የተሻሻለው የመንግስት ሠራተኞችን አዋጅ ለመደንገግ የወጣ አዋጅ (አዋጅ ቁጥር ፫፻፱ /፪ሺ፲፰)
የቀጠለ
ባሕር ዳር፡- ጥቅምት፣ 24/2019ዓ.ም

የዓመት ዕረፍት ፈቃድ ማስተላለፍ

1/ የዚህ አዋጅ አንቀጽ 59 (1) ድንጋጌ ቢኖርም የሥራው ሁኔታ በማስገደዱ ምክንያት መሥሪያ ቤቱ ለሠራተኛው የዓመት ዕረፍት ፈቃዱን በበጀት ዓመቱ ውስጥ ሊሰጠው ያልቻለ እንደሆነ የመሥሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ ከሁለት የበጀት ዓመት ላልበለጠ ጊዜ ሊያስተላልፈው ይችላል፣ ሆኖም ያልተጠቀመበት የዓመት ዕረፍት ፈቃድ በሦስተኛው በጀት ዓመት ለሠራተኛው መሰጠት አለበት።
2/ የዚህ አዋጅ አንቀጽ 57 (3) ድንጋጌ ቢኖርም ማንኛውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) መሠረት የዓመት ዕረፍት ፈቃዱ ለሚተላለፍበትና ፈቃዱ በገንዘብ ተለውጦ እንዲሰጠው ለሚጠይቅ ሠራተኛ በጀት በቅድሚያ በማስያዝ ከተላለፈው የዓመት ዕረፍት ፈቃድ ውስጥ የመጀመሪያውን የአንድ ዓመት ዕረፍት ፈቃድ ብቻ በገንዘብ ተለውጦ እንዲሰጠው ማድረግ አለበት፡፡
3/ የአንድ መንግሥት ሠራተኛ የዓመት ዕረፍት ፈቃድ በገንዘብ ሲለወጥ የሠራተኛው የአንድ ቀን ደመወዝ የሚታሰበው ያልተጣራ የወር ደመወዙን በሠላሳ ቀናት በማካፈል ነው፡፡

ያልተወሰደ የዓመት ዕረፍት ፈቃድ

1/ የመንግሥት ሠራተኛው አገልግሎት በመቋረጡ ያልተወሰደ የዓመት ዕረፍት ፈቃድ የሥራ ቀናት ብቻ ታስበው በገንዘብ ተለውጦ ይሰጠዋል፡፡
2/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) ድንጋጌ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 50 መሠረት ለተዛወረ ወይም በአንቀጽ 52 መሠረት ለተደለደለ የመንግሥት ሠራተኛ ተፈፃሚ አይሆንም፡፡ ሆኖም ሠራተኛው በነበረበት የመንግሥት መሥሪያ ቤት በዚህ አዋጅ አንቀጽ 60 (1) መሠረት የተላለፈለት የዓመት ዕረፍት ፈቃድ ወደ ተዛወረበት ወይም ወደ ተደለደለበት የመንግሥት መሥሪያ ቤት ይተላለፍለታል፡፡
የወሊድ ፈቃድ

1/ ነፍሰጡር የሆነች የመንግሥት ሠራተኛ፡-
ሀ) ከእርግዝናዋ ጋር የተያያዘ ምርመራ ለማድረግ ሐኪም በሚያዘው መሠረት ደመወዝ የሚከፈልበት ፈቃድ ይሰጣታል፤
ለ) ከመውለዷ በፊት ዕረፍት እንድታደርግ ሐኪም ካዘዘ ደመወዝ የሚከፈልበት ዕረፍት ይሰጣታል፡፡
2/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) የተመለከተው ፈቃድ እንደ ህመም ፈቃድ አይቆጠርም፡
3/ ነፍሰጡር የሆነች የመንግሥት ሠራተኛ መውለጃዋ ሲደርስ እወልዳለሁ ብላ ከገመተችበት ቀን በፊት ሠላሳ ተከታታይ ቀናት የቅድመ ወሊድ ፈቃድ፣ እንዲሁም ስትወልድ ከወለደችበት ቀን ጀምሮ ዘጠና ተከታታይ ቀናት፣ በአጠቃላይ አንድ መቶ ሃያ ተከታታይ ቀናት ደመወዝ የሚከፈልበት የወሊድ ፈቃድ ይሰጣታል፡፡
4/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (3) መሠረት ሠራተኛዋ የተሰጣት የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ከማለቁ በፊት ከወለደች ያልተጠቀመችበትን ቀሪ የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ከወለደች በኋላ እንድትጠቀምበት ይደረጋል፡፡
5/ ሠራተኛዋ የወሰደችው የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ሲያልቅ ያልወለደች እንደሆነ እስከምትወልድበት ቀን ድረስ ባሉት የሥራ ቀናት የምትቆይበት ዕረፍት በበጀት ዓመቱ ካላት የዓመት ዕረፍት ፈቃድ ወይም በበጀት ዓመቱ የዓመት ፈቃድ የሌላት እንደሆነ ከሚቀጥለው የበጀት ዓመት የዕረፍት ፈቃዷ ይተካል፡፡
6/ ሠራተኛዋ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (3) የተወሰነውን የወሊድ ፈቃድ ከጨረሰች በኋላ ብትታመምና ተጨማሪ ፈቃድ የሚያስፈልጋት መሆኑ በሀኪም ከተረጋገጠ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 63(1) በተደነገገው መሠረት የሕመም ፈቃድ መውሰድ ትችላለች።
7/ ማንኛዋም ስድስት ወር የሞላት ነፍሰጡር የሆነች የመንግስት ሠራተኛ የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ከመውሰዷ በፊት ጽንሱ የተቋረጠባት ከሆነ ይህንኑ የሚያረጋግጥ የሕክምና ማስረጃ ስታቀርብ የስልሳ ቀን የድህረ ወሊድ ፈቃድ ይሰጣታል፡፡
8/ የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ከወሰደች በኋላ የጽንስ መቋረጥ ካጋጠማት የወሰደችው የቅድመ ወሊድ ፈቃዷ ተቋርጦ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (3) የተመለከተው የዘጠና ቀን የድህረ ወሊድ ፈቃድ ይሰጣታል፡፡
9/ ከሦስት እስከ ስድስት ወር ባለው የእርግዝና ጊዜ ውስጥ የፅንስ መቋረጥ ያጋጠማት የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ የሚከፈልበት ሠላሳ ተከታታይ ቀን ፈቃድ ይሰጣታል፡
10/ ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ የትዳር ጓደኛው ስትወልድ ደመወዝ የሚከፈልበት አስር የሥራ ቀን ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡
11/ አንድ እናት ከሶስት ወር ያልበለጠው ህፃን ልጅ ለማሳደግ በጉዲፈቻ የተረከበች ከሆነ ሦስት ወር ፍቃድ ይሰጣል ፡፡

በባሕር ዳር ከተማ እየተገነባ ያለው አዲሱ የዓባይ ወንዝ ድልድይ መዳረሻ መንገድ ግንባታ እየተፋጠነ ነው።በባሕር ዳር ከተማ እየተገነባ ያለው አዲሱ የዓባይ ወንዝ ድልድይ መዳረሻ መንገድ ግንባ...
03/11/2026

በባሕር ዳር ከተማ እየተገነባ ያለው አዲሱ የዓባይ ወንዝ ድልድይ መዳረሻ መንገድ ግንባታ እየተፋጠነ ነው።

በባሕር ዳር ከተማ እየተገነባ ያለው አዲሱ የዓባይ ወንዝ ድልድይ መዳረሻ መንገድ ግንባታ 95 በመቶ መድረሱ ተገልጿል።

ከሄኒ ጋርደን መገንጠያ እስከ ዘንዘልማ ጎንደር መውጫ የሚዘልቀው ይህ 4 ነጥብ 72 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ዘመናዊ መንገድ፣ 59 ሜትር ስፋት ያለው ሲኾን በአንድ ጊዜ እስከ 6 ተሽከርካሪዎችን የማስተናገድ አቅም አለው።

የመኪና ማቆሚያዎች፣ የእግረኛ መንገዶች፣ የጠጠር ንጣፎች እና የአስፓልት ዝርጋታዎችን ጨምሮ ዋና ዋና ሥራዎች የተጠናቀቁ ሲኾን፣ አሁን ላይ የዘንዘልማ መጋጠሚያ፣ የመብራት ዝርጋታ እና ቀሪ ውስን ሥራዎች በመከናወን ላይ ናቸው።

የኢትዮ-ሱዳን ዋና መስመር አካል የኾነው ይህ ፕሮጀክት፣ አዲሱን የዓባይ ድልድይ ከዋናው አውራ ጎዳና ጋር በማገናኘት በአገልግሎት ብዛት የተጎዳውን ነባር ድልድይ ከፍተኛ የትራፊክ ጫና ሙሉ በሙሉ ያስተነፍሰዋል ተብሎ ይጠበቃል።

ግንባታውን ሀፍኮን ከክሮስላንድ ኮንስትራክሽን ጋር በመኾን እያከናወኑት ሲኾን፣ ለሥራው 825 ሚሊዮን ብር ተመድቧል ሲል የኢትዮጵያ መንገዶች አሥተዳደር ገልጿል።

!

! 🇪🇹


"በመጀመሪያው ሩብ አመት ስኬታማ የሠላም፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራት ተከናውነዋል።" ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደየአማራ ክልል የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የፓር...
03/11/2026

"በመጀመሪያው ሩብ አመት ስኬታማ የሠላም፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራት ተከናውነዋል።" ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

የአማራ ክልል የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የፓርቲና የመንግሥት ሥራዎች አፈጻጸም ግምገማ እየተካሄደ ነው።

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ፣ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያዎቹ ሦስት ወራት የተከናወኑ የፓርቲና የመንግሥት ሥራዎችን በመገምገም፣ የተመዘገቡ ውጤቶችን፣ የታዩ ክፍተቶችንና ቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎችን በጋራ መፈተሽ አስፈላጊ መኾኑን አመልክተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ "በመጀመሪያው ሩብ አመት ስኬታማ የሠላም፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራት ተከናውነዋል።" ብለዋል።

የግምገማው መድረኩ የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታ፣ ባለፉት ወራት የተመዘገቡ የሥራ ውጤቶች፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችንና የአፈጻጸም ክፍተቶችን በጥልቀት በመመርመር የቀጣይ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ አስፈላጊ መሆኑንም አመላክተዋል።

የአመራር አቅምን ማጠናከር፣ የሥራ አፈጻጸምን ማሻሻል፣ የተቋማትን ቅንጅት ማሳደግና ለሕዝቡ የተገቡ ቃል ኪዳኖችን በተግባር ማሳካት በግምገማው ትኩረት የሚሰጣቸው ጉዳዮች መሆናቸውም ተገልጿል።

ሥራዎችን በማቀናጀት፣ በመከፋፈልና በቅንጅት ለመምራት የሚደረገው ጥረትም እንደ አዎንታዊ ጎን ተመልክቷል። የሪፎርም ሥራዎችን በትክክል በመረዳትና በአግባቡ ለመምራት የተጀመረው ጥረትም አበረታች መኾኑ ተጠቁሟል።

ህዝብ በምርጫ የሰጠውን አደራ ለመወጣት ያለው የሩብ አመት ዝግጅትና የተከናወኑ ተግባራት በቀጣይ ለሚከናወኑ ሁለንተናዊ የሠላምና የልማት ተግባራት መደላድል የፈጠሩ መሆናቸውም ተነስቷል።

በአመራሩ መካከል የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት እየተሻሻለ መምጣቱና በራስ የመተማመን አቅም መጎልበቱም የተጠቀሱ አዎንታዊ ጎኖች ናቸው።

በወቅታዊ የክረምት ሥራዎች ውጤታማነት ላይ ከፍተኛ ጥረት መደረጉና የሰብዓዊ ድጋፍ ሥራዎችን በራስ አቅም በማንቀሳቀስ ንቅናቄውን ለመምራት የተደረገው ርብርብ መሻሻል ማሳየቱም በግምገማው ከተነሱ ጥንካሬዎች መካከል ናቸው።

በተመሳሳይ፣ የክልሉን ሠላም ለማረጋገጥ የሚደረገው ትግልና ጥረት ውጤት የተመዘገበበት ስለመሆኑም ተጠቅሷል።

የተመዘገቡ ጥንካሬዎችን ማስቀጠል፣ የታዩ ድክመቶችን በግልጽ መለየትና በተግባር ማረም፣ እንዲሁም የአመራርና የፈጻሚዎችን አቅም ማጠናከር የቀጣይ ሥራዎች ዋነኛ አቅጣጫ ተደርጎ ሊወሠድ እንደሚገባውም ተጠቁሟል።

የግምገማ መድረኩ በሩብ አመቱ የተከናወኑ ተግባራትን በመገምገም ሳይወሰን፣ የአፈጻጸም ደረጃን በማስረጃ ለመፈተሽ፣ የተሻሉ ተሞክሮዎችን ለማስፋትና የተስተዋሉ ክፍተቶችን ለማረም የሚያግዝ እንደሚኾን ይጠበቃል።

የባሕር ዳር ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዙር ምረጫ 14ኛ ዓመት የስራ ዘመን 33ኛ መደበኛ ጉባዔ መካሄድ  ጀመረ። ጥቅምት 24/2019 ዓ.ም (ባሕርዳር ከተማ ኮሙዩኒኬሽን) የባሕር ዳር ከተማ ምክ...
03/11/2026

የባሕር ዳር ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዙር ምረጫ 14ኛ ዓመት የስራ ዘመን 33ኛ መደበኛ ጉባዔ መካሄድ ጀመረ።

ጥቅምት 24/2019 ዓ.ም (ባሕርዳር ከተማ ኮሙዩኒኬሽን) የባሕር ዳር ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዙር ምረጫ 14ኛ ዓመት የስራ ዘመን 33ኛ መደበኛ ጉባዔ ክቡር ከንቲባ አቶ ጎሹ እንዳላማውን ጨምሮ የከተማ አመራሮች እና የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴና አባላት በተገኙበት ተጀምሯል።

የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ ጌትነት እውነቱ (ዶ/ር) በመክፈቻው እንደገለፁት ጉባኤው ከዛሬ ጥቅምት 24 እስከ 26/2019 ድረስ የሚካሄድ መሆኑን በመጠቆም በቆይታውም፦

#የባህርዳር ከተማ ምክርቤት 32ኛ መደበኛ ጉባኤን ቃለ-ጉበኤ ገምግሞ ማጽደቅ፣
#የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር የ2018 ዓ.ም እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ገምግሞ ማጽደቅ፣
#የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር የ2019 ዓ.ም መሪ እቅድና በጀት ገምግሞ ማጽደቅ፣
#የባህር ዳር ከተማ ም/ቤት የ2018 ዓ.ም እቅድ አፈጻጸም ገምግሞ ማጽደቅ፣
#የባህር ዳር ከተማ ምክርቤት የ2019 ዓ.ም እቅድ እና በጀት ገምግሞ ማጽደቅ፣
#የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ልዩ ልዩ ደንቦች ገምግሞ ማጽደቅ እና የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ልዩ ልዩ ሹመቶችን ገምግሞ ማጽደቅ፣ በአጀንዳነት በመያዝ ጉባኤው ተጀምሯል።

የሰላም፣ የቱሪዝም እና የኮንፈረንስ ማዕከልነቷን ያረጋገጠችው ባሕር ዳር 🇪🇹ባሕር ዳር ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ጨዋታዎችን፣ ስፖርታዊ ሁነቶችን እና መጠነ ሰፊ ኮንፈረንሶችን...
02/11/2026

የሰላም፣ የቱሪዝም እና የኮንፈረንስ ማዕከልነቷን ያረጋገጠችው ባሕር ዳር 🇪🇹

ባሕር ዳር ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ጨዋታዎችን፣ ስፖርታዊ ሁነቶችን እና መጠነ ሰፊ ኮንፈረንሶችን በስኬት ማስተናገዷ በከተማዋ አስተማማኝ ሰላም እና መረጋጋት መኖሩን ለሀገር ውስጥ እና ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ያሳየችበት ሕያው ምስክር ነው።

እነዚህ ትላልቅ ሁነቶች በሰላማዊ መንገድ መከናወናቸው የከተማዋን ገጽታ ከመገንባት ባለፈ ለከተማዋ ሁለንተናዊ እድገት ያለው አስተዋጽኦም ከፍተኛ ነው። የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ባሕር ዳር ትላልቅ ሁነቶችን ማስተናገድ መቻሏ የከተማዋን አስተማማኝ ጸጥታ በተግባር የሚያረጋግጥ መኾኑን መናገራቸው ይታወሳል።

በሺዎች የሚቆጠሩ እንግዶች፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ ስፖርተኞች እና ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ወደ ከተማዋ በነጻነት መጥተው መሳተፋቸው ከተማዋ ሰላሟ የሰፈነ እና ለእንግዶቿ ምቹ መኾኗን ማስመስከሩን ገልጸዋል።

በተጨማሪም የባሕር ዳር እና የአካባቢው ነዋሪ በመልካም የእንግዳ ተቀባይነት እሴት እንግዶችን ማስተናገዳቸው የከተማዋ ነዋሪ ለሰላም እና ለልማት ያለውን ጽኑ ፍላጎት የሚያንጸባርቅ መኾኑን ጠቅሰዋል።

በባሕር ዳር ከተማ ከተከናወኑ ሁነቶች ጋር ተያይዞ የወጡ የአማራ ክልል ባሕል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት ቢሮ መረጃዎች እንደሚያመለክቱትም ሁነቶቹ በከተማዋ ለሚገኙ ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች፣ የጎብኝ መዳረሻዎች ለባሕል አልባሳት እና የእጅ ጥበብ አቅራቢዎች የገቢ መነቃቃት ፈጥረዋል።

እንዲህ ዓይነት ሁነቶች ለከተማዋ የሚያስገኟቸው ዘለቄታዊ ጥቅሞች ይኖራሉ። አንደኛው የኢንቨስትመንት እና የመሠረተ ልማት እድገት መፍጠር ነው።

እንደ ባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም፣ በኮሪደር ልማት እየተሠሩ እንዳሉ መሠረተ ልማቶች እና ሌሎችም ሥራዎች ደረጃቸውን ጠብቀው እንዲሠሩ እና ሥራዎች እንዲቀጥሉ ከማድረጉም በላይ ሰላም እና ምቹ ሁኔታን የተመለከቱ ባለሀብቶች በክልሉ መዋዕለ ንዋይ እንዲያፈስሱ መንገድ ይከፍታሉ።

ማኅበራዊ ትስስር እና ብሔራዊ አንድነትንም ይፈጥራሉ፤ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚመጡ እንግዶች እና ስፖርተኞች በባሕል እና በእሴት ልውውጥ ብሔራዊ አንድነትን ያጠናክራሉ። እንዲህ አይነት ሁነቶች እና ኮንፈረንሶች የሥነ ልቦና መነቃቃትንም ይፈጥራሉ። የከተማዋ ወጣቶች እና ነዋሪዎች በከተማቸው የመኩራት እና የሥነ ልቦና መነቃቃት ስሜት እንዲኖራቸውም ያደርጋል።

!
! 🇪🇹


ዘጋቢ፦ ሮዛ የሻነህ

ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በደብረ ብርሃን ከተማ የተሠሩ የልማት ሥራዎችን መርቀው ሥራ አስጀመሩ። ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር የተሠሩ የልማት ሥራዎችን ...
01/11/2026

ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በደብረ ብርሃን ከተማ የተሠሩ የልማት ሥራዎችን መርቀው ሥራ አስጀመሩ።

ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር የተሠሩ የልማት ሥራዎችን መርቀው አስጀምረዋል።

በማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓቱ ከርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በተጨማሪ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይን እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር እቴጌ ጣይቱ ክፍለ ከተማ የቀበሌዎችን ደረጃ ለማዘመን የተሠራውን የልቼ ቀበሌ አሥተዳደር ጽሕፈት ቤትን፣ የደብረ ብርሃን ከተማ የፍሳሽ ማጣሪያ ፕሮጄክትን፣ የደብረ ብርሃን የኮሪደር ልማትን እና የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ መምሪያ የሕንጻ ግንባታን ነው መርቀው ሥራ ያስጀመሩት።

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ከተሞችን ውብ፣ ለነዋሪዎች እና ለጎብኝዎች የተመቹ ለማድረግ በትኩረት እየተሠራ መኾኑን ገልጸዋል። ጽዱ፣ ደኅንነቱ የተጠበቀ እና ጤናው የተጠበቀ ማኅበረሰብ እንዲኖር እንዲህ አይነት ሥራዎች አስፈላጊ መኾናቸውንም ገልጸዋል። የፍሳሽ ማስወገጃ ፕሮጄክቱ ጽዱ ከተማን ለመፍጠር እንደሚያስችልም ተናግረዋል። የተሠሩትን ፕሮጄክቶች በአግባቡ መጠበቅ እንደሚገባም አመላክተዋል።

ፕሮጄክቶቹን ሠርተው ለፈጸሙ ሁሉ ምሥጋናም አቅርበዋል። በፍሳሽ ማጣሪያው ውስጥ የሚቀሩ ሥራዎችን ማጠናቀቅ እንደሚገባም አስገንዝበዋል። የተሠሩ ሥራዎችን በአግባቡ መጠቀም ደብረ ብርሃንን የኢንዱስትሪ እና የአገልግሎት መስጫ ከተማ ማድረግ ያስችላታል ነው ያሉት።

የልቼ ቀበሌ አሥተዳደር ጽሕፈት ቤት ግንባታ የከተማ አሥተዳደሩ ሕዝብን ለማገልገል ያለውን ቁርጠኝነት፣ ሕዝብ በዘመናዊ ተቋም ለመገልገል ያለውን ፍላጎት እና ድጋፍ ያሳየበት መኾኑንም ተናግረዋል። ግንባታው ዘመናዊ መኾኑንም አንስተዋል።

🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊

01/11/2026
ዳሽን ቢራ ፋብሪካ አ.ማ እና ባህር ዳር ከነማ ለቀጣይ ሶስት ዓመት የሚቆይ የብራንድ ስፓንሰርሽፕ ስምምነት ተፈራረሙ።የፊርማ ስነስርዓቱ የተፈፀመው በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጎሹ ...
01/11/2026

ዳሽን ቢራ ፋብሪካ አ.ማ እና ባህር ዳር ከነማ ለቀጣይ ሶስት ዓመት የሚቆይ የብራንድ ስፓንሰርሽፕ ስምምነት ተፈራረሙ።

የፊርማ ስነስርዓቱ የተፈፀመው በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው እና በዳሽን ቢራ ፋብሪካ አ.ማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ማትያስ ጌታቸው መካከል በባህር ዳር ከተማ ነው።

ዳሽን ቢራ ፋብሪካ አ.ማ ላለፉት 5 ዓመታት የባህር ዳር ከነማ ስፓርት ክለብ የብራንድ ስፖንሰር ሆኖ የቆየ ሲሆን አሁንም ይህን ትብብር ይበልጥ ለማሳደግ ለቀጣይ 3 ዓመታት የሚቆይ ስምምነት ተፈርሟል።

የስፓንሰርሽፕ ስምምነቱ የክለቡን ተፎካካሪነት ይበልጥ ያጠናክረዋል ተብሎ ይገመታል።
_

Address

Bahir Dar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mayor office of Bahir Dar posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share