North Shoa Zone Land Department

Directions

North Shoa Zone Land Department Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from North Shoa Zone Land Department, Government Organization, Debre birehan, Debre Birhan.

30/10/2026

የአንድ ማዕከል አገልግሎት ለሁለንተናዊ ብልጽግና !

ሞሰብ የአንድ ማእከል አግልግሎት ማለት ተገልጋዮች የተለያዩ የመንግስት ወይም የግል ተቋማት አገልግሎቶችን በአንድ ጣሪያ ስር ወይም በአንድ የዲጂታል መድረክ ላይ በቀላሉ ማግኘት እንዲችሉ ታስቦ የተዘረጋ ዘመናዊ አሰራር ነው።
ስያሜው ከባህላዊው 'ሞሰብ' የተወሰደ ሲሆን፣ ልክ ሞሰብ የተለያዩ ማዕዶችን በአንድ ላይ አቅፎ እንደሚይዝ ሁሉ፣ ይህ አሰራርም የተበታተኑ አገልግሎቶችን በአንድ ማዕከል በማሰባሰብ የዜጎችን እንግልት ለማስቀረት ያለመ ነው።

ይህ ስርዓት ዜጎች ከአንድ ቢሮ ወደ ሌላ ቢሮ መንከራተት ሳይጠበቅባቸው፣ ሁሉንም ጉዳዮቻቸውን በአንድ ቦታ በአጭር ጊዜ እንዲያጠናቅቁ ያስችላቸዋል።

የዚህ አሰራር ዋነኛ ፋይዳ የቢሮክራሲን ሰንሰለት በማሳጠር ፈጣን እና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት ነው። ከዚህ ቀደም አንድን ጉዳይ ለማስፈጸም በተለያዩ ተቋማት መካከል የሚባክነውን ረጅም ጊዜና ጉልበት በማዳን፣ የተገልጋዩን እርካታ ከፍ ለማድረግ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል። በተጨማሪም ተቋማት መረጃዎችን በጋራ እንዲለዋወጡ እና በተቀናጀ መንገድ እንዲሰሩ በማድረግ፣ የመንግስትን የአሰራር ስርዓት ወደ ተሻለ የዘመናዊነት እና የቅልጥፍና ደረጃ የሚያሸጋግር ቁልፍ እርምጃ ነው።

የአንድ ማዕከል አገልግሎት መዘርጋት በርካታ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጠቀሜታዎችን ያስገኛል። ለተገልጋዮች የትራንስፖርት እና ተያያዥ ወጪዎችን ሲቀንስ፣ አላስፈላጊ ወረፋዎችን እና መጉላላቶችን በማስወገድ የምርታማነት ጊዜያቸውን እንዲቆጥቡ ይረዳል። ለመንግስት ደግሞ አሰራርን ግልጽ እና ተጠያቂነት ያለው በማድረግ፣ የሙስና እና የብልሹ አሰራር ክፍተቶችን በከፍተኛ ሁኔታ ይዘጋል። እንዲሁም የውጭም ሆነ የሀገር ውስጥ ኢንቨስተሮች ፈቃድ እና የተለያዩ ማረጋገጫዎችን በቀላሉ እንዲያገኙ በማድረግ የንግድ እና የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴን በእጅጉ ያፋጥናል።

ሞሰብ ወይም የአንድ ማዕከል አገልግሎት የዘመናዊ አስተዳደር እና የዲጂታል ኢኮኖሚ ሽግግር ወሳኝ መሰረት ነው። ዜጎች ጥራት ያለው፣ ፈጣን እና የተከበረ አገልግሎት የማግኘት መብታቸውን በተግባር የሚያረጋግጥ ከመሆኑም ባሻገር፣ በመንግስት እና በህዝብ መካከል ያለውን መተማመን ያጠናክራል። ስለዚህ ይህንን ስርዓት ይበልጥ ማጎልበት እና ወደ ሁሉም የአገልግሎት ዘርፎች ማስፋፋት የሀገርን ሁለንተናዊ እድገት ለማፋጠን እና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን የማይተካ ሚና ይኖረዋል መልክታችን ነው ።

*****
የደቡብ ወሎ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን

30/10/2026
30/10/2026
30/10/2026

#ዜና #ሹመት
በምክር ቤቱ ከ40 በላይ ሹመቶች ጸድቀዋል!

1, ወ/ሮ ፋንቱ ተስፋዬ:-የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ

2, አቶ አማረ ሰጤ የአማራ ክልል ምክር ቤት ም/ አፈ-ጉባኤ

3, አቶ አረጋ ከበደ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር

4, አብዱ ሁሴን (ዶ/ር) የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር

5, ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር) በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አስተባባሪ

6, ዘሪሁን ፍቅሩ (ዶ.ር) በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ዘርፍ አሥተባባሪ

7, ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ

8, አማኑኤል ፈረደ (ዶ.ር) በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአሥተዳደር ዘርፍ አስተባባሪ

9, አቶ ይርጋ ሲሳይ ፡ በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የርዕሰ መስተዳደሩ የህዝብ ግንኙነትና አደረጃጀት ዋና አማካሪ

10, አቶ ደረጀ ማንደፍሮ ፡ የአብክመ ርዕሰ መስተዳደር የአደረጃጀት ዘርፍ ዋና አማካሪ

11, መንገሻ ፈንታው(ዶ/ር)፡ የአብክመ ርዕሰ መስተዳደር የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ዋና አማካሪ

12, የአብክመ ግብርና ቢሮ ኀላፊ= ዶ/ር መስፍን አበጀ ተፈራ

13, የአብክመ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኀላፊ= ዶ/ር ኢብራሂም መሀመድ እንድሪስ

14, የአብክመ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኀላፊ= አቶ እንድሪስ አብዱ አህመድ

15, የአብክመ መሬት ቢሮ ኀላፊ = አቶ ሲሳይ ዳምጤ አበባዬ

16. የአብክመ ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ = ዶ/ር ሞላ መልካሙ ከበደ

17. የአብክመ ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ኀላፊ= ዶ/ር ዳኝነት ፈንታ መኮነን
18, የአብክመ ማዕድን ቢሮ ኀላፊ = አቶ ሃይሌ አበበ ብዙዓየሁ

19, የአብክመ መንገድ፣ ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ቢሮ ኀላፊ = ዶ/ር ጋሻው አወቀ ትኩየ

20, የአብክመ ስራና ክህሎት ቢሮ ኀላፊ= ዶ/ር ስቡህ ገበያው ታረቀ

21, የአብክመ ገንዘብ ቢሮ ኀላፊ = አቶ አታላይ ጥላሁን ጫኔ

22, የአብክመ ገቢዎች ቢሮ = አቶ ጥላሁን ፈንታው ተሾመ

23, የአብክመ ጤና ቢሮ ኀላፊ = አቶ አብዱከሪም መንግስቱ ይማም

24, የአብክመ ፍትህ ቢሮ ኀላፊ = አቶ ብርሃኑ ጎሽም አዘረፍ

25. የአብክመ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ = ዶ/ር እሸቱ የሱፍ አየለ

26, የአብክመ ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኀላፊ = ወ/ሮ ብርቱካን ሲሳይ እንየው

27, የአብክመ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኀላፊ= አቶ አባይ መንግስቴ ሰላምሰው

28, የአብክመ ሲቪል ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኀላፊ= ወ/ሮ ባንቻምላክ ገ/ማርያም በላይ

29, የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ኀላፊ =ዶ/ር ደመቀ ቦሩ ባህሩ

30,የአብክመ ባህል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት ቢሮ ኀላፊ = አቶ መልካሙ ጸጋየ ገላው

31, የአብክመ እንስሳትና ዓሳ ሀብት ቢሮ ኀላፊ= ዶ/ር ጋሻው ሙጭ አለምነው

32, የአብክመ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኀላፊ=ዶ/ር የሻለም ገዛኸኝ ዳምጠው

33, የአብክመ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን = አቶ ተስፋሁን አለምነህ ይስማው

34, የአብክመ ትምህርት ቢሮ ኀላፊ = አቶ ጥላሁን ወርቅነህ ተክሌ

35, አቶ ከፍ ያለው ሙላቴ:- የግብርና፣ አካባቢ ጥበቃ እና ውኃ ሃብት ልማት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ

36, አቶ አበራ ፈንታው :-የሰው ሃብት እና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ

37, ወይዘሮ እመቤት ከበደ:- የመንግሥት ወጪ አሥተዳደር ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ

38, ወይዘሮ አድና ምኅረቱ :- የሴቶች፣ ሕጻናት እና ወጣቶች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ

39, ወይዘሮ ሃናን አብዱ:- የበጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ

4., አቶ ደሴ መኮንን:- የሕግ እና ፍትሕ አሥተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ

41, አቶ አራጌ ይመር:- የከተማ ንግድ እና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆነው ተሹመዋል።
#ገንዘብ #መምሪያ
#አማራ #ክልል #ምክር #ቤት

ለ9ኙ ከተማ መሬት አስተዳደሮች በከተማ ካዳስተር ትግበራ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደየከተማ ካዳስተር ስራን በጥራትና በውጤታማነት ለማስጀመር የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ላ...
28/10/2026

ለ9ኙ ከተማ መሬት አስተዳደሮች በከተማ ካዳስተር ትግበራ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደ

የከተማ ካዳስተር ስራን በጥራትና በውጤታማነት ለማስጀመር የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ከከተማ መሬት አስተዳደሮች ጋር በበይነ-መረብ (Google Meet) ተካሂዷል።

በመድረኩ እንደተገለጸው፤ የከተማ ካዳስተር ስራን በስኬት ለመጀመር በመጀመሪያ ደረጃ የመረጃ ማጣራት፣ የተጓደሉ ሰነዶችን ማሟላት እንዲሁም ከሚመለከታቸው አካላት የሰነድ ርክክብ በማድረግ የማመሳከር ስራዎች ሊከናወኑ እንደሚገባ እና እነዚህም ተግባራት በመመሪያ ቁጥር 61/2010፣ 16/2011 እና 24/2011 መሰረት በጥብቅ መፈጸም እንዳለባቸው ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቷል።

ከዚህም በተጨማሪ አስፈላጊዎቹ ሰነዶች ከተዘጋጁ በኋላ የቅየሳ ስራን ለማከናወን የቀጠናና የሰፈር መረጣ ማካሄድ፣ የቅየሳ መቆጣጠሪያ ቦታዎችን በተሰጠው ኮኦርዲኔት መሰረት መምረጥ እና በስታንዳርዱ መሰረት የሞኑመንት (የምልክት ማቆሚያ) ማምረት ስራዎች ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ዋና ዋና ጉዳዮች መሆናቸው ተመላክቷል።

በመድረኩ ላይ በከተማ መሬት ሃላፊዎችና በሚመለከታቸው ባለሙያዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን፣ አስፈላጊ ሰነዶችና መመሪያዎችም በባለሙያዎቹ የቴሌግራም ቻናል በኩል እንዲላኩላቸው ተደርጓል።

በመጨረሻም የመምሪያው ሃላፊ አቶ ሸዋንግዛው ሃ/ሚካኤል ለካዳስተር ስራው አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶች ማለትም የቅየሳ መሳሪያዎች፣ ኮምፒውተር፣ የቢሮ ቁሳቁሶች እና በቂ የሰው ሃይል እንዲሟሉ አቅጣጫ ሰጥተዋል። ለስራው በቂ በጀት ተመድቦ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ መሬት ላይ ትግበራ እንዲገባም ሃላፊው ጠበቅ ያለ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

27/10/2026
26/10/2026

Address

Debre Birehan
Debre Birhan

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when North Shoa Zone Land Department posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share