Dire Dawa Urban Development and Construction Bureau

Directions

Dire Dawa Urban Development and Construction Bureau Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Dire Dawa Urban Development and Construction Bureau, Government Organization, dire dawa mariam sefer, Dire Dawa.

31/10/2026
ጥቅምት 21/2019ለድሬዳዋ አስተዳደር የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የፋይናንስ ፣ግዥና ንብረት አስተዳደር ባለሙያዎች በዘርፉ አገልግሎት አሰጣጥና ካስኬዲንግ አፈፃፀም ላይ ስልጠና ተሰጠ...
31/10/2026

ጥቅምት 21/2019
ለድሬዳዋ አስተዳደር የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የፋይናንስ ፣ግዥና ንብረት አስተዳደር ባለሙያዎች በዘርፉ አገልግሎት አሰጣጥና ካስኬዲንግ አፈፃፀም ላይ ስልጠና ተሰጠ፡፡

30/10/2026
ጥቅምት 15/2019በአንድነትና በመግባባት ከተሰራ በበጀት ዓመቱ የላቀ ውጤት በማስመዝገብ ማህበሩን ሞደልና የማህበሩን አባላት ተጠቃሚ ማድረግ  እንደሚቻል ተገለፀ፡፡በጋራ መኖሪያ ቤት ነዋሪዎ...
25/10/2026

ጥቅምት 15/2019
በአንድነትና በመግባባት ከተሰራ በበጀት ዓመቱ የላቀ ውጤት በማስመዝገብ ማህበሩን ሞደልና የማህበሩን አባላት ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚቻል ተገለፀ፡፡
በጋራ መኖሪያ ቤት ነዋሪዎች የሚመሰረቱ ማህበራትን ብቻ ሳይሆን በማንኛውም የልማት መስክ የምናከናውናቸው ተግባራት ውጤታማና ማህበረሰብን ተጠቃሚ የሚያደርጉት በአንድነትና በመግባባት መስራት ስንችል ነው ያሉት የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ህንፃዎችና ቤቶች አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ኢብሳ ሙሳ ናቸው፡፡ ዳይሬክተሩ ይህን መልዕክት ያስተላለፉትም በቢፍቱ ኮንዱምኒየም ነዋሪዎች ማህበር አባላት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ተገኝተው ጉባኤውን በንግግር ሲያጠቃልሉ ነው፡፡
ዳይሬክተሩ አያይዘውም የማህበሩ መጠናከር ለቢፍቱ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ነዋሪዎች ብቻ ሳይሆን ለአካባቢው ህብረተሰብ የሚሰጠውን ጥቅምና ከማህበሩ አባላት የሚጠበቁ ሃላፊነቶችን ካብራሩ በኋላ እያንዳንዱ የቢፍቱ ኮንዱምኒየም ነዋሪዎች ማህበር አባላት የሚጠበቅበትን ሃላፊነት ከተወጣና የበኩሉን አስተዋጽኦ ካበረከተ ማህበሩ ወደፊት እንደሚሻገር ከወዲሁ መተንበይ ይቻላል ብለዋል፡፡

የማህበሩ አመራሮች ምርጫ ተካሄዶም የሥራ ርክክብ ተደርጎ ለማህበሩ እንቅስቃሴ መጎልበትና መጠናከር የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የቀድሞ አመራሮች የምስጋና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል፡፡

ጥቅምት 13/2019ለድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ልማትና ኮንስራክሽን ቢሮ የብልጽግና ፓርቲ ህብረትና ቤተሰብ አመራሮች ስልጠና ተሰጠ፡፡ለከተማ ልማትና ኮንሰትራክሽን ቢሮ የብልጽግና ፓርቲ ህብረት...
23/10/2026

ጥቅምት 13/2019
ለድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ልማትና ኮንስራክሽን ቢሮ የብልጽግና ፓርቲ ህብረትና ቤተሰብ አመራሮች ስልጠና ተሰጠ፡፡
ለከተማ ልማትና ኮንሰትራክሽን ቢሮ የብልጽግና ፓርቲ ህብረትና ቤተሰብ አመራሮች ስልጠናውን የሰጡት የድሬዳዋ አስተዳደር የከታማ ልማትና ኮንሰትራክሽን ቢሮ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ ኢማጅ አብደላ ሲሆኑ ስልጠናውን መውሰድ በየደረጃው የሚሰጡ ተልዕኮዎችን በአግባቡ ለመፈፀም የሚያስችል ግንዛቤ ያዳብራል ብለዋል፡፡
ስልጠና የተሰጠባቸው መመሪዎችም የፓርቲ የአሰራርና አደረጃጀት መመሪያ እና የአባላት ተልዕኮ ማስፈጸሚያ መመሪያ ናቸው፡፡ መመሪያዎቹ በንባብ ከቀረቡ በኋላም በስልጠናው ላይ የተሳተፉ የቢሮው የብልጽግና ፓርቲ ህብረትና የቤተሰብ አመራሮች በመመሪያዎቹ ላይ ሰፊ ውይይት ያደረጉ ሲሆን በዚህም ስልጠና ላይ የኢንስፔክሽን እና ስነ-ምግባር ኮሚሽን ኮሚቴዎች መሳተፋቸው ታውቋል፡፡፡፡

ጥቅምት 12/2019የህብረተሰቡን የመኖሪያ ቤት አቅርቦት ጥይቄ ለመመለስ የሚያስችል አሰራር ዘርግተን መተግበር አለብን ተባለ፡፡በቤቶች ልማት ድርጅት በኩል የተከናወኑ የልማት ተግባራት አበራታ...
22/10/2026

ጥቅምት 12/2019
የህብረተሰቡን የመኖሪያ ቤት አቅርቦት ጥይቄ ለመመለስ የሚያስችል አሰራር ዘርግተን መተግበር አለብን ተባለ፡፡
በቤቶች ልማት ድርጅት በኩል የተከናወኑ የልማት ተግባራት አበራታች ውጤቶች የተመዘገበባቸውና መጠናከር ያለባቸው መሆኑን ገልፀው በቀጣይ የሚከናውኑ ማናቸውም የቤት ልማት ተግባራት የህብረተሰቡን የመኖሪያ ቤት ጥያቄ መመለስ የሚያስችሉ መሆናቸውን በማለት ያሳሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ቤቶች ልማት ድርጅት ሃላፊ ወ/ሮ ረሂማ አወል ናቸው፡፡
ሃላፊዋ ይህን መልዕክት ያስተላለፉትም ከድሬዳዋ አስተዳደር የቤቶች ልማት ድርጅት ሰራተኖች ጋር ለመተዋወቅና በተቋሙ የ2019 ዕቅድ ላይ ለመወያየት የተዘጋጀውን የውይይት መድረክ ሲከፍቱ ነው፡፡
የህብረተሰቡን የመኖሪያ ቤት አቅርቦት ጥይቄ ለመመለስ መሟላት ያለባቸው የተለያዩ ግብዓቶች መኖራቸው ቢታወቅም ያለንን ውስን ሃብት ተጠቅመን በሙሉ አቅማችን ወደ ሥራ ከገባን ማንቀርፈው ተግዳሮት የለም ያሉት የበቶች ልማት ድርጅት ሃላፊ ለለውጥ ሥራዎች ትኩረት በመስጠትና ሰራተኞችን የማስፈፀም አቅም በማጎልበት ተቋማችንን አፈፃፀም ወደላቀ ደረጃ ማሸጋገር አለብን ብለዋል፡፡
የህብረተሰቡ የመኖሪያ ቤት ጥያቄ በመንግስት አቅርቦት ብቻ የሚመለስ ስላልሆነ የግል ባለሃብቱን ተሳትፎ የሚሳድግ አሰራር መተግበርን ጨምሮ ተለያዩ የቤት ልማት አማራጮችን መጠቅም እንደሚስፈልግም አሳስበዋል፡፡

ጥቅምት 11/2019በግል መኖሪያ ቤት አዋጅ ቁጥር 1320/2016 አተገባበር ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ተካሄደ፡፡የድሬዳዋ አስተዳደር የከተማ ልማና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ሐየር ...
21/10/2026

ጥቅምት 11/2019
በግል መኖሪያ ቤት አዋጅ ቁጥር 1320/2016 አተገባበር ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ተካሄደ፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር የከተማ ልማና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ሐየር ሃጂ ኑር ባስተላለፉት መልዕክትም አዋጁ የሚተገበረው በየወረዳው ስለሆነ እያንዳንዱ ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅበትን ሃላፊነት በአግባቡና ውጤታማ በሆነ አሰራር መወጣት አለበት ብለዋል፡፡

ጥቅምት 10/2019ከተማን በፕላን መምራት የህብረተሰቡን የኗኗር  ዘይቤ ምቹ እንደሚያደርግ ተገለፀ፡፡ከተማን በፕላን መምራት ለከተማ ዕድገትና የአኗኗር ዘይቤ ምቹነት ወሳኝ መሆኑን የተናገሩት...
20/10/2026

ጥቅምት 10/2019
ከተማን በፕላን መምራት የህብረተሰቡን የኗኗር ዘይቤ ምቹ እንደሚያደርግ ተገለፀ፡፡
ከተማን በፕላን መምራት ለከተማ ዕድገትና የአኗኗር ዘይቤ ምቹነት ወሳኝ መሆኑን የተናገሩት የድሬዳዋ አስተዳደር የከተማ ልማትና ኮንሰትራክሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ሐየር ሃጂ ኑር ሲሆኑ መልዕክቱን ያስተላለፉትም በተራራ ልማት ፕሮጀክት ጥናት ላይ ለመወያየት የተዘጋጀ የባለድርሻ አካለት መድረክ ሲከፍቱ ነው፡፡

ድሬዳዋ በፕላን የተመሰረተችና ለሌሎች የአገራችን ከተሞች በፕላን መቆርቆር አስተዋጽኦ ያበረከተች ዘመናዊ ከተማ መሆኗን ያስታወሱት የቢሮው ሃላፊ በተጀመረው ተራራ ልማትም የአካባቢውን ነዋሪዎች የአኗኗር ዘይቤ የሚያሻሽል ፕላን በመተግበር ድሬዳዋ እንደቀደመው ታሪኳ የአገራችን ተምሳሌት እንድትሆን በጋራ መሥራት አለብን ብለዋል፡፡

በዕለቱ የውይይት መድረክ የተሳተፉ የባለድርሻ አካላትም የተጀመረው የተራራ ልማት ፕሮጀከት ጥናት የተራራ ላይ ነዋሪዎችን ኑሮ ምቹና የልማት ተጠቃሚ የሚያደርግ ስለሆነ የሚጠበቅብንን ሃላፊነት ሁሉ ለመወጣት ዝግጁ ነን ብለዋል፡፡

ጥቅምት 07/2019በአዋጅ ቁጥር1320/2016 አተገባር ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡የግል መኖሪያ ቤቶች አከራይ ተከራይ አዋጅ ቁጥር 13202016 እንደ ድሬዳዋ አስተዳደር መተግበር ከጀመረ ሁለት...
17/10/2026

ጥቅምት 07/2019
በአዋጅ ቁጥር1320/2016 አተገባር ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡
የግል መኖሪያ ቤቶች አከራይ ተከራይ አዋጅ ቁጥር 13202016 እንደ ድሬዳዋ አስተዳደር መተግበር ከጀመረ ሁለት ዓመት ያለፈውና አበረታች ውጤት የታየበት ቢሆንም በሚፈለገው ልክ ትኩረት ያገኘ ነው ለማለት አይቻልም ያሉት የድሬዳዋ አስተዳደር ገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ አብዱሰመድ መሀመድ ናቸው፡፡

የአዋጁ መተግበር የአስተዳደሩን ገቢ ከማሳደግ ባለፈ ከህብረተሰቡ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነትና የተረጋጋ ህይወት ከመምራት አንፃር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው ስለሆነ የህብረተሰቡና የአስፈፃሚ አካለትን ግንዛቤ በማዳበርና የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ በማጠናከር በበጀት ዓመቱ የላቀ ውጤት ማስመዝገብ አለብን በማለት አሳስበዋል፡፡

በዚህ የውይይት መድረክም ገቢዎች ባለስለልጣን፣ ከተማልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮና የወረዳ አመራሮች፣ የየወረዳው ፖሊስ አባላትና የሚመለከታቸው ተቋማት ባለሙያዎች መገኘታቸው ታውቋል፡፡ ከጥቅምት 09/2019 ጀምሮም አዋጁን ለመተግበር የሚያስችሉ ተግባራት እንዲከናወኑ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

ጥቅምት 04/2019የድሬዳዋ አስተዳደር የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ አመራሮች ከዘጠኙም ወረዳ አመራሮች ጋር ውይይት አካሄዱ፡፡የቢሮውና የዘጠኙም ወረዳ አመራሮች የተወያዩት በቀጣይ በጋራ...
14/10/2026

ጥቅምት 04/2019
የድሬዳዋ አስተዳደር የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ አመራሮች ከዘጠኙም ወረዳ አመራሮች ጋር ውይይት አካሄዱ፡፡
የቢሮውና የዘጠኙም ወረዳ አመራሮች የተወያዩት በቀጣይ በጋራ በሚያከናውኗቸው ተግባራትና ትኩረት በሚሰጣቸው የጋራ አገልግሎቶች ላይ ሲሆን ውይይቱን የመሩት የድሬዳዋ አስተዳደር የከተማ ልማና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ሐየር ሃጂ ኑር ናቸው፡፡

የቢሮው ሃላፊም በቀጣይ በመንግስት ቤቶች አስተዳደር፣ ፍትሃዊ አገልግሎት አሰጣጥና በመዘጋጃቤታዊ ገቢ አሰባሰብ ዕቅዶችን አፈፃፀም ውጤታማ ለማድረግ በጋራ መገግባባትና በተጠናከረ ግንኙነት መሥራት እንዳለባቸው አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡ የመንግሳት ቤቶችን አስተዳደርና ፍትሃዊ ተደራሽነትም ሆነ የማዘጋጃ ቤታዊ ገቢን ዕቅድ በላቀ ደረጃ ለማሳካት በየሁለት ሳምንት እየተገናኙ ሥራውን እንደሚገመግሙ ውሳኔ አስተላልፈዋል፡፡

Address

Dire Dawa Mariam Sefer
Dire Dawa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dire Dawa Urban Development and Construction Bureau posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share