South Omo Zone Government Communications

Call Directions Contact the organization

South Omo Zone Government Communications This page belongs to the newly structured South omo zone gov't at Dimeka.

"አሰብ የማን ናት?"አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ታሪካዊ በደል እና የህልውና አጀንዳን አብሮ የያዘ የሀገራችን ፖለቲካ ምህዳር ውስጥ የቁ...
03/11/2026

"አሰብ የማን ናት?"

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ታሪካዊ በደል እና የህልውና አጀንዳን አብሮ የያዘ የሀገራችን ፖለቲካ ምህዳር ውስጥ የቁጭት ምንጭ የሆነ ምዕራፍ ነው።

በዚህ ወሳኝ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ጥልቅ የሆነ ሕጋዊ እና ታሪካዊ ዳሰሳ ከሚያደርጉ ሥራዎች መካከል በታዋቂው ሕግ ባለሙያ በያዕቆብ ኃይለማርያም (ዶ/ር) «አሰብ የማን ናት?» በሚል ርዕስ የተዘጋጀው መጽሐፍ ይጠቀሳል።

መጽሐፉ የኢትዮጵያን የባህር በር ባለቤትነት ከመጀመሪያው አንስቶ እስከ እያንዳንዱ ዘመን መስዋዕትነት ድረስ አሟጦ የያዘ ታላቅ ሰነድ ነው። ጸሐፊው ከፖለቲካ ወገንተኝነትና ጫና ገለል በማለት ምሁራዊ ድፍረትን በማሳየት የሀገራቸውን እውነት ያለማመንታት በመጽሐፋቸው አስፍረዋል።

የኢትዮጵያ እና የባህር በር ቁርኝት በተፈጥሮም ሆነ በታሪክ የማይካድ ሀቅ ቢሆንም ባለፉት ዘመናት የተከፈለው ግዙፍ የኢኮኖሚና የደም መስዋዕትነት ከዚህ እውነት ጋር ተመጣጣኝ ግምት አላገኘም።

ለአብነት ያህል በአጼ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት ብቻ የባህር በር መሰረተ ልማቶችን ለማልማት እና ከሀገር ውስጥ ጋር ለማስተሳሰር የወጣው ወጪ እጅግ ግዙፍ ሀብት ነበር።

ይሁን እንጂ የሻዕቢያ አገዛዝ ስልጣን ከያዘ በኋላ ይህንን የጋራ ሀብትና የባህር ኃይል አቅም በማውደም ሀገሪቱን ከባህር በር ያራቀ ፖለቲካዊ ስህተት ተፈጽሟል።

በተለይም የኢህአዴግ አስተዳደር በባህር በር ዙሪያ የሰራው ታሪካዊ ጥፋት በወደብ ላይ ያለውን የባለቤትነት መብት በእጅጉ ጎድቶታል።

በአልጀርስ ስምምነትም ቢሆን የአሰብ ጉዳይ ወደ ጎን እንዲገፋ እና ኢትዮጵያ ተገቢውን ሕጋዊና ታሪካዊ ክርክር እንዳታደርግ እጇ የታሰረበት፣ የውጭ ኃይሎች ተጽዕኖ በከፍተኛ ሁኔታ የተንጸባረቀበት እና በግፍና በሴራ የዲፕሎማሲያዊ ሽንገላ እንዲዘጋ የተደረገ አሳዛኝ ምዕራፍ ነው።

የያዕቆብ (ዶ/ር) መጽሐፍ ዛሬ ላይ ሲታይ እጅግ አስገራሚ የሆነ ትንቢታዊ ገጽታን ያንጸባርቃል።

በወቅቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር እያደገ ሲመጣ የጂኦግራፊ ሥራና የባህር በር ጥያቄ የህልውና ጉዳይ ሆኖ እንደሚመለስ የሀገሪቱ ሉዓላዊነት የሚገደውና የሚያስከብረው መንግሥት ሲመጣም ይህ ጥያቄ ሊቀር እንደሚገባው በግልጽ አስቀምጧል።

አሁን ላይ ታዲያ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደነውር ይታሰብ የነበረውን የባህር በር ጥያቄ የመደመር መንግሥት የብሔራዊ አጀንዳ በማድረግ የጀመረው ሰላማዊ እና ሰጥቶ የመቀበል መርህን የተከተለ ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴ ይህንን ታሪካዊ ስብራት የሚጠግን ሁነኛ ርምጃ ነው።

ይሁን እና የታሪካዊ ጠላቶች እንቅስቃሴ ለኢትዮጵያ ፈተና ቢሆኑም የባህር በር ጥያቄ ጊዜያዊ የፖለቲካ ጩኸት ሳይሆን የሕዝቦች የዘለዓለም የህልውናና የፍትህ ጥያቄ መሆኑን ሁሉም ሊገነዘበው ይገባል።

የጥቅምት 24 ጠባሳ፦ መቼም የማይረሳ፣ የማይደገም ክህደት የአንድ ሀገር ሕልውና እና ብሔራዊ ክብር ጸንቶ የሚቆመው፣ ለሉዓላዊነቷ ዘብ በሚቆሙ ልጆቿ ጽናትና መሥዋዕትነት ነው። ኢትዮጵያም የብ...
03/11/2026

የጥቅምት 24 ጠባሳ፦ መቼም የማይረሳ፣ የማይደገም ክህደት

የአንድ ሀገር ሕልውና እና ብሔራዊ ክብር ጸንቶ የሚቆመው፣ ለሉዓላዊነቷ ዘብ በሚቆሙ ልጆቿ ጽናትና መሥዋዕትነት ነው። ኢትዮጵያም የብዙ ዘመናት የነፃነት ታሪኳን ጠብቃ ለዛሬ የበቃችው፣ ብሔራዊ ጥቅሟን ከምንም በላይ ያስቀደሙ የቁርጥ ቀን ልጆቿ በከፈሉት የደምና የአጥንት ዋጋ ነው።

ይሁን እንጂ በሀገራችን የፖለቲካና የጦርነት ታሪክ ውስጥ፣ የውጭ ወራሪ ኃይሎች እንኳን ሊፈጽሙት ያልደፈሩት እጅግ አሳፋሪና ዘግናኝ የክህደት ድርጊት ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ተፈጽሟል። ባንዳነት መገለጫው የሆነው ሕገወጡ የሕወሓት ቡድን፣ ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር በማበር ለሀገሩ ቅድሚያ በሰጠው የሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሠራዊታችን ላይ በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ የጭካኔ ተግባር ፈጽሟል።

ከሁሉም የኢትዮጵያ ማዕዘናት ተውጣጥቶ ለዓመታት በዱር በገደሉ የሕዝብን ሰላምና ደኅንነት ሲጠብቅ የኖረን ሠራዊት ከጀርባ መውጋት፣ በቃላት የማይገለጽ ታላቅ ክህደት ነው። ጠላት ሲመጣ መከታ፣ በሰላም ጊዜ ደግሞ የልማት አጋር ለነበረው ለዚህ ብርቅዬ ሠራዊት በደምና በላቡ ለከፈለው ደግነት የተሰጠው ምላሽ የጭካኔ ጥይት ሆነ።

የዚህ እኩይ ተግባር ዋነኛ ግብ፣ የኢትዮጵያ የአንድነትና የሉዓላዊነት ምልክት የሆነውን የመከላከያ ተቋም በማዋረድና በመበተን፣ እርስ በርስ መተማመንን በማጥፋት፣ ሀገራችንን ወደ ማያባራ የእርስ በርስ እልቂትና መፍረስ ለመውሰድ የተጠነሰሰ የባዳና የባንዳ ሴራ ነበር።

ዳሩ ግን የሴረኞቹ ስሌት የኢትዮጵያውያንን የአይበገሬነት መንፈስና የሠራዊቱን ጽናት ያገናዘበ አልነበረም። በወንድሞቹ ላይ የተፈጸመው ግፍ የቁጭት ነበልባል የለኮሰበት ቀሪው የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ በፍጥነት ራሱን አደራጅቶ የቡድኑን የጥፋት ህልም በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ቅዠት ቀይሮታል።

ሠራዊታችን በዚያ አስከፊ የፈተና ወቅት ለበቀል ሳይሆን ለሕግ የበላይነትና ለወታደራዊ መርሕ በመገዛት፣ በከፈለው መተኪያ የሌለው መሥዋዕትነት ሀገርን ከመፍረስ፣ ሕዝብንም ከመበተን ታድጓል። ዛሬ የምንተነፍሰው የነፃነት አየር፣ “ከወገኔ በፊት እኔ ልቅደም” ብለው የግፍ ጽዋን በተጎነጩት በእነዚያ ሰማዕታት ደምና አጥንት የተገኘ የውለታ ዕዳችን ነው።

በመሆኑም ይህ የጭካኔ ተግባር በፍጹም መደገም የሌለበትና መቼም የማይረሳ የታሪካችን አካል ነው። ጥቅምት 24 ቀን በሰሜን ዕዝ ላይ የተፈጸመው ተግባር መቼም ቢሆን የማይረሳ የሀገር ክህደት ሆኖ እንዳይደገም በታሪካችን ሲታወስ የሚኖርም ነው።

ይህ መራራ የታሪክ ጠባሳ በአንድ በኩል ሀገርን መክዳትና የታሪካዊ ጠላቶች መሣሪያ መሆን የሚያስከፍለውን ከባድ የውርደት ዋጋ ያሳየ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ ከመቼውም ጊዜ በላይ በአደረጃጀቱ፣ በሥነ-ልቦናውና በአቅሙ የጠነከረ፣ የማይደፈር የሀገር መከላከያ ሠራዊት እንድንገነባ አስችሎናል።

እንዲህ ዓይነቱ ብሔራዊ ክህደት በኢትዮጵያ ምድር ዳግም እንዳይከሰት፣ የሀገርን ህልውና የማስጠበቅ ኃላፊነትን ለሠራዊቱ ብቻ ሳንተው፣ ሁላችንም ልዩነቶቻችንን ወደ ጎን በመተው እና ሁለንተናዊ ሥራዎቻችንን ከብሔራዊ ጥቅም ጋር በማስተሳሰር ለሀገራችን አንድነት በጋራ ልንቆም ይገባል።

የታሪክ ሚዛን ለሀገር የቆሙ ጀግኖችን ስም በወርቅ ቀለም ጽፎ ለዘለዓለም ያኖራል። በየጦር ግንባሩ በጀግንነት እየተዋደቀ የሀገርን ሉዓላዊነት ላስከበረውና ዋጋ ለከፈለው ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ተመን የለሽ መስዋዕትነት ክብርና እውቅና እንሰጣለን።

የሰማዕታቱ አደራ በትውልድ ቅብብሎሽ ሕያው ሆኖ ይኖራልና፣ "ጥቅምት 24ትን እንዳይደገም መቼም አንረሳውም!" #ኢቢሲ

02/11/2026
"በክልሉ አዲስ የተመሠረተው የመደመር መንግስት ሴቶች ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ እየሰራ ይገኛል":- ደምሴ አድማሱ (ዶ/ር)ጥቅምት 23/201...
02/11/2026

"በክልሉ አዲስ የተመሠረተው የመደመር መንግስት ሴቶች ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ እየሰራ ይገኛል":- ደምሴ አድማሱ (ዶ/ር)

ጥቅምት 23/2019 ዓ.ም

በየደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የ2018 ዓ/ም የሴቶች ልማት ህብረትና የአካቶ ትግበራ ስትሪንግ ኮሚቴ በዕቅድ አፈፃፀም እና ቀጣይ ተግባራት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በወላይታ ሶዶ እየተካሄደ ነው።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ ምስተዳድርና የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ደምሴ አድማሱ (ዶ/ር) የመደመር መንግስት ሴቶች ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ እየተጋ ይገኛል ብለዋል።

የሴቶች ልማት ህብረትን ማጠናከር የሴቶችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን ለማጎልበት አቅም በመሆኑ በጉዳዩ ላይ መምከርና አቅዶ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

የሴቶች ጤና መጠበቅ፣ በትምህርትና መሰል ጉዳዮች ላይ ተሳትፏቸውን ማሳደግ ለልማት አቅም እንደሚሆንም አመላክተዋል።

የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ አለምነሽ ደመቀ በበኩላቸው መድረኩ የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ጠርንካራ ጎኖችን ለማስቀጠልና በጉድለት የተለዩትን ደግሞ በመቀናጀት ለመፍታት ያለመ መሆኑን ገልፀዋል።

የመድረኩ ዓላማ ቃልን በተግባርና በውጤት ለማረጋገጥ እንዲሁም የሴቶችን ልማት ህብረትና የአካቶ ትግበራን በኃላፊነትና በትኩረት ለመስራትና ቀጣይ አቅጣጫ ለማመላከት ያለመም እንደሆነም አመላክተዋል።

ሴቶች ለዘላቂ ልማት ያላቸው ሚና የላቀ መሆኑን የገለጹት ኃላፊዋ በግብርና፣ በዕደ ጥበብ፣ በቴክኖሎጂና ገቢ ማስገኛ እንዲሁም ስራ ፈጠራ ላይ ይበልጥ እንዲሳተፉ በቅንጅት ይሰራ ብለዋል።

በመድረኩ የሴቶች ልማት ህብረትና የአካቶ ትግበራ ስትሪንግ ኮሚቴ አባላትና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

የደቡብ ኦሞ ዞን ስራና ክህሎት መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምና የ2019 የቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ምክክር እያደረገ ነው::ጥቅምት 23/2019 ዓ.ም ዲ...
02/11/2026

የደቡብ ኦሞ ዞን ስራና ክህሎት መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምና የ2019 የቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ምክክር እያደረገ ነው::

ጥቅምት 23/2019 ዓ.ም ዲመካ

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ መድረኩን በይፋ ባስጀመሩበት ወቅት እንደገለፁት በዞኑ ስራ ፈላጊ ወጣቶችን በኢንተርፕራይዝ በማደራጀት ወደ ስራ ለማስገባት እና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት እየተሰራ እንደሆነ ገልፀዋል ::

ይሁን እንጂ ወጣቶች ዝንባለያቸው ላይ መሠረት በማድረግ አደራጅቶ ውጤታማ እንዲሆኑ ከማድረግ አንፃር እና ብድርና መሰል ድጋፎችን በወቅቱ ከማድረግ አኳያ ክፍተት ያለበት መሆኑን ዋና አስተዳዳሪው ተናግረዋል ::

በመሆኑም ሁሉም መዋቅሮች በዘርፉ የሚታዩ ክፍተቶችን ፈጥኖ በማረም የዞኑን ወጣቶች ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አመራሩ ሊረባረቡ እንደሚገባ አቶ ማዕከል አሳስበዋል ::

የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና የስራና ክህሎት መምሪያ ኃላፊ የሆኑት አቶ ታደለ ጋያ በበኩላቸው በአፈፃፀሙ ወቅት በጥንካሬ የተስተዋሉትን በማስቀጠልና ችግሮችን ቆጥሮ ለማረም የምክክር መድረኩ ዋሳኝ እንደሆነ ገልፀዋል ::

በቀጣይ በአከባቢው ፀጋ ላይ መሠረት ያደረገ አደረጃጀት በመስራት ውጤታማ እንዲሆኑ ታስቦ በቀጣይ ትኩረት በመስጠት መሠራት እንዳለበት አቶ ታደለ አሳስበዋል::

በመድረኩ የዞን የወረዳ እና የከተማ አስተዳደር አመራሮች ተሳታፊ የሆኑ ስሆን የዘርፉ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም በምክትል መምሪያ ኃላፊ አማካኝነት እየቀረበ ይገኛል::

በ2018 በጀት ዓመት በማህበረሰብ ዐቀፍ ጤና መድህን  የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ መዋቅሮችና ጤና ፅፈት ቤቶች ዕውቅናና የዋንጫ ሽልማት ተበረከተላቸው ::ጥቅምት 23/2019 ዓ.ም ዲመካየደ...
02/11/2026

በ2018 በጀት ዓመት በማህበረሰብ ዐቀፍ ጤና መድህን የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ መዋቅሮችና ጤና ፅፈት ቤቶች ዕውቅናና የዋንጫ ሽልማት ተበረከተላቸው ::

ጥቅምት 23/2019 ዓ.ም ዲመካ

የደቡብ ኦሞ ዞን ጤና መምሪያ በዛሬው ዕለት የ2019 በጀት ዓመት የማህበረሰብ ዐቀፍ ጤና መድህን /ማዐጤመ/ ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ የንቅናቄ መድረክ አካህዷል ::

የ2018 በጀት ዓመት የማዐጤመ ዕቅድ አፈፃፀም መሠረት በማድረግ መምሪያው የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ መዋቅሮችና ጤና ፅፈት ቤቶች ዕውቅናና የዋንጫ ሽልማት አበርክቷል ::

በዚህም መሠረት በዞኑ ካሉ ወረዳዎች ዳሰነች ሐመር እና በና ፀማይ ወረዳዎች በቅደም ተከተላቸው ከ1ኛ እስከ 3ኛ በመውጣት የዋንጫ ተሸላሚ ሆነዋል::

‎በደቡብ  ኦሞ ዞን በሣላማጎ ወረዳ የባህላዊ ፍርድ ቤቶች የእውቅና መስጫና የዳኞች ሹመት መርሐ ግብር ተካሂዷል።‎‎ጥቅምት 23/2019 ዓ.ም ‎‎በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የባህላዊ ዳኝነት አቋ...
02/11/2026

‎በደቡብ ኦሞ ዞን በሣላማጎ ወረዳ የባህላዊ ፍርድ ቤቶች የእውቅና መስጫና የዳኞች ሹመት መርሐ ግብር ተካሂዷል።
‎
‎ጥቅምት 23/2019 ዓ.ም
‎
‎በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የባህላዊ ዳኝነት አቋቋምና ዕውቅና መስጫ አዋጅ ቁጥር 63/2017 መሠረት፣ በደቡብ ኦሞ ዞን ሣላማጎ ወረዳ የባህላዊ ፍርድ ቤቶች የእውቅና መስጫና የዳኞች ሹመት መርሐ ግብር ተካሂዷል።
‎
‎የደቡብ አሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕርድበት ፕሬዝዳንት አቶ ተመስገን ጋርሾ የደቡብ ኦሞ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ምክትል ፕረዝዳንት አቶ ጋሻህ ረዳህኝ ክሎት የሣላማጎ ወረዳ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ተወካይ አቶ አበራ በመሆን የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል።

‎በመርሐ ግብሩ በተለያዩ ክላስተሮች የሚያገለግሉ ባህላዊ ዳኞች ሹመት የተሰጣቸው ሲሆን፣ ዳኞቹም በፍርድ ቤቱ ፊት ቃለ መሐላ ፈጽመዋል።
‎
‎የሣላማጎ ወረዳ ፍርድ ቤት መስማትና መወሰን ስራ ሂደት አስተባባሪ ዳኛ አቶ አንተነህ ዘርሁን ለተሾሙት ዳኞች በሕጋዊ የሥራ ኃላፊነታቸው፣ በዳኝነት አሠራርና በችሎት አመራር ዙሪያ ሥልጠና ሰጥተዋል።
‎
‎በዝግጅቱ ላይ የደቡብ ኦሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ተመስገን ጋርሾ የባህላዊ ዳኝነት ሥርዓት ለማኅበረሰቡ ፍትሕን በቅርበት ለማዳረስና ክርክሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ያለውን ፋይዳ ገልጸዋል።
‎
‎በወረዳው ፍርድ ቤት ለባህላዊ ዳኞች ሹመትና ሥልጠና ረገድ ላደረገው ጥረትም አድናቆታቸውን ገልጸው፣ የባህላዊ ፍርድ ቤቶቹ በተገቢው ሁኔታ እንዲሠሩ ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግ አስታውቀዋል።
‎
‎በኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 34(5) እና 78(5) የባህላዊ ዳኝነት ሥርዓቶችን በሕግ ማዕቀፍ ውስጥ የማቋቋምና ዕውቅና የመስጠት መሠረት የተቀመጠ ሲሆን፣ ይህም የማኅበረሰቡን የፍትሕ ተደራሽነትና የባህል እሴቶችን ለማጠናከር ወሳኝ ብለዋል ።
‎
‎በመርሐ ግብሩ የደቡብ ኦሞ የዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕዝዳንት የወረዳው ፍርድቤት ዳኞች የወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና ሰላምና ፀጥታ ፤ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፣ የወረዳው ባለድርሻ አመራሮችና ባለሙያዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
‎

"የቱሪዝም ሀብቶችን ከመደመር መንግስት እሳቤ ጋር  በማጣመር ለሀገራዊ ዕድገት የሚኖራቸውን አስተዋጽኦ ማሳደግ ይገባል" ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር) ጥቅምት 23/2019 ዓ.ም የደቡብ ኢትዮጵያ ክል...
02/11/2026

"የቱሪዝም ሀብቶችን ከመደመር መንግስት እሳቤ ጋር በማጣመር ለሀገራዊ ዕድገት የሚኖራቸውን አስተዋጽኦ ማሳደግ ይገባል" ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር)

ጥቅምት 23/2019 ዓ.ም

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቱሪዝም ቢሮ በ2019 በጀት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈፃፀምና በቀጣይ ጊዜያት የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ በካራት ከተማ የምክክር መድረክ እያካሄደ ይገኛል።

በክልሉ ያሉት የቱሪዝም አቅም ለአለም ማስተዋወቅ የቀጣይ ጊዜያት የትኩረት አቅጣጫ መሆኑም ተጠቁሟል።

የክልሉ የቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር) በመድረኩ መክፈቻ ላይ እንደገለፁት፣ቱሪዝም ከአምስቱ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ምሶሶዎች አንዱ መሆኑን ገልጸዋል።

መንግስት ለዘርፉ የሰጠውን ትኩረት በአግባቡ በመረዳት ያሉትን የቱሪዝም ሃብቶችን በተገቢው መንገድ ማስተዋወቅ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

በየአካባቢው የሚገኙ የተፈጥሮ የታሪክና የባህል ፀጋዎችን በመለየትና በማልማት ለአለም ማስተዋወቅ እንደሚገባም ኃላፊው ጠቁመዋል።

የቱሪዝም ሀብቶችን በአግባቡ በማልማትና በመጠበቅ ለሀገራዊ ዕድገትና ለሀገር ግንባታ የድርሻውን እንዲወጣ ልዩ ትኩረት መስጠት እንደሚያስፈልግም ዶ/ር ዝናቡ ገልጸዋል።

ዘርፉ በህዝቦች መካከል ያለውን ትስስርና መግባባት የሚያጠናክር እንደመሆኑ ይህንኑ በዲጂታል ቴክኖሎጂ የማስተዋወቅ ስራ ማጠናከር እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል።

መንግስት ለዘርፉ የሰጠውን ትኩረት በሚገባ በመረዳና ከሀገር ግንባታ አቅጣጫ ጋር በማስተሳሰር ለሀገራዊ ዕድገት የሚኖራቸውን አስተዋጽኦ ማሳደግ ያስፈልጋል ሲሉም አሳስበዋል።

የክልሉ ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊና የመዳረሻና መሠረተ ልማት ማስፋፊያ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተካልኝ ጌታሁን በበኩላቸው ክልሉ በብዝሃነት የሚታወቅ በመሆኑ ያሉትን የቱሪዝም ሀብቶች በአግባቡ በማልማትና ለስራ ዕድል ፈጠራ መጠቀም እንደሚገባ ገልጸዋል።

በክልሉ ያሉ ዘርፈብዙ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ክፍተቶችን በመለየት ዘርፉን ለማጠናከር ይሰራልም ብለዋል።

በመድረኩም የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጨምሮ ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።

የደቡብ ኦሞ ዞን ጤና መምሪያ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን የንቅናቄ መድረክ በድመካ ከተማ እያካሄደ ነው::ጥቅምት 23/2019 ዓ.ም ድመካ"ኑ ለነገ ወጪያችን አብረን እናስብ" በሚል መሪ ...
02/11/2026

የደቡብ ኦሞ ዞን ጤና መምሪያ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን የንቅናቄ መድረክ በድመካ ከተማ እያካሄደ ነው::

ጥቅምት 23/2019 ዓ.ም ድመካ

"ኑ ለነገ ወጪያችን አብረን እናስብ" በሚል መሪ ቃል የዞኑ ጤና መምሪያ የ2019 በጀት ዓመት የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን የንቅናቄ መድረክ እያካሄደ ይገኛል ::

መድረኩን በይፋ ያስጀመሩት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ማዕከል ማሊኮ ከንቅናቄው በኋላ ሁሉም መዋቅር ከወትሮው በተለየ መንገድ በመስራት ዕቅዱን መቶ በመቶ ለማሳካት መረባረብ እንዳለበት አሳስበዋል ::

በማአጤመ ፕሮግራም ዙሪያ የሚታዩ ውስብስብ ችግሮች በመቅረፍ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ አመራሩ በጊዜ የለሽ መንፈስ መስራት እንዳለበትም አቶ ማዕከል በአፅኖት ተናግረዋል ::

የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ የሆኑት አቶ ይሄነው ተስፋዬ በበኩላቸው እንደገለፁት የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ በመገምገም የታዩ ክፍተቶችን ለመለየት እና ማህበረሰቡና መንግስት ተቀናጅቶ እንዲሰራ ለማስቻል ያለመ መድረክ እንደሆነም ተናግረዋል ::

በ2018 በጀት ዓመት 63 ሺህ በላይ ሰዎች የማጤመ ፕሮግራም አባል ሆነው የተመዘገበ ቢሆንም የአባልነት መዋጮ በአግባቡ ከማስተላለፍ እንዲሁም በጤና ተቋማት የመዲሃንት እጥረት ችግር በአፈፃፀሙ ላይ አሉታዊ አስተዋፅኦ ማስከተላቸውን የመምሪያው ኃላፊ ገልፀዋል ::

የ2018 በጀት ዓመት የማአጤመ ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እየቀረበ ሲሆን በቀጣይ የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ከቀረበ በኋላ ሰፋ ያለ ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል ::

በዞኑ ከሚገኙ ሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ዋና አስተዳዳሪዎች ከንቲባዎች ባለሙያዎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት በመድረኩ ተገኝተዋል::

Address

SNNPRS-Ethiopia
Jinka

Telephone

+251903983112

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when South Omo Zone Government Communications posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to South Omo Zone Government Communications:

Shortcuts

Share