South Achefer Cooperative Office

South Achefer Cooperative Office

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from South Achefer Cooperative Office, Government Organization, Dubrovnik.

27/02/2026

የመሠረታዊ የኅብረት ሥራ ማህበራት የአባላት መነሻ ቁጥር አወሳሰን
*
በኅብረት ሥራ ማበራት አዋጅ ቁጥር 985/2009 አንቀፅ 7 ንዑስ አንቀፅ 2 እና 3 እና በአንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 የተደነገገው
እንደተጠበቀ ሆኖ በማምረት ወይም አገልግሎት በመስጠት ወይም በማምርት እና አገልግሎት በመስጠት ተግባር ላይ የተሰማሩ ኅብረት ሥራ ማህበራት አባላት የመነሻ ቁጥር እንደሚከተሉትን ይሆናል፤

ሀ) በእንሰሳት እና እንሰሳት ተዋፅኦ የሚደራጁ የኅብረት ሥራ ማህበራት አባላት የመነሻ ቁጥር 80 ሰው ይሆናል፡፡
ለ) በሰብል እና የደን ውጤቶች የሚደራጁ የኅብረት ሥራ ማህበራት አባላት የመነሻ ቁጥር 100 ሰው ይሆናል፡፡
ሐ) በአከባቢ መሰረት አድረገው የሚደራጁ የሸማቾች የኅብረት ሥራ ማህበራት የአባላት የመነሻ ቁጥር 250 ሰው ይሆናል፡፡
መ) ተቋምን መሰረት አድረገው የሚደራጁ የሸማቾች የኅብረት ሥራ ማህበራት የአባላት የመነሻ ቁጥር 100 ይሆናል፡፡
ሠ) በአከባቢ መሰረት አድረገው የሚደራጁ በገንዘብ ቁጠባና ብድር የኅብረት ሥራ ማህበራት የአባላት የመነሻ ቁጥር 100 ሰው
ይሆናል፡፡
ረ) ተቋምን መሰረት አድረገው የሚደራጁ በገንዘብ ቁጠባና ብድር የኅብረት ሥራ ማህበራት የአባላት የመነሻ ቁጥር 80 ሰው
ይሆናል፡፡
ሰ) በመኖሪያ ቤቶች የኅብረት ሥራ ማህበራት የሚደራጁ አባላት የመነሻ ቁጥር በገጠር 50 በከተማ 24 ይሆናል፡፡
ሸ) የሁለገብ የገበሬዎች ኅብረት ሥራ ማህበራት የሚደራጁ አባላት የመነሻ ቁጥር 250 ይሆናል፡፡
ቀ) በአትክልትና ፍራፍሬ እና በመስኖ ሥራዎች ላይ የኅብረት ሥራ ማህበራት የሚደራጁ አባላት የመነሻ ቁጥር 50 ይሆናል፡፡
በ) የተለያዩ ቋሚ እና አላቂ ሀብቶችን መሰረት አድርገው የሚደራጁ የኅብረት ሥራ ማህበራት ባለው ሀብት እና በአዋጭነት ጥናት መሰረት የመነሻ ቁጥሩን አግባብ ያለው ባለስልጣን ይስናል፡፡ ሆኖም መነሻ ቁጥሩ ከ10 ሰው ማነስ አይችልም፡፡

በዚህ አንቀጽአንቀጽ 49 ንኡስ አንቀጽ 1 የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ ከአዋጅ 985/2009 አስቀድሞ የተደራጁ አባላት የመነሻ ቁጥር እንዳስፈላጊነቱ አዋጭነቱን መሰረት በማድረግ የአባላት ቁጥር እንዲጨምር አግባብ ያለው ባለስልጣን ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፡፡

Photos from South Achefer Cooperative Office's post 04/02/2026

የደቡብ አቸፈር ወረዳ ህብረት ስራ ማህበራት ተ/ጽ/ቤት በራስ አገዝ ለሚደራጁ የማህበረሰብ ክፍሎች የግንዛቤ ፈጠራ መድረክ አካሄደ::

03/02/2026

ማስታወቂያ

Photos from South Achefer Cooperative Office's post 31/01/2026

የአዊ ህዝብ ባህሉን ከልማት ጋር አጣጥሞ ከፈረስ ወደ ትራክተር ትርዒት ተሸጋግሯል
*****
የአዊ ህዝብ ከፈረስ ወደ ትራክተር መሸጋገሩ የገጠር ትራንስፎርሜሽን ከኢንዱስትሪ ትራንስፎርሜሽን ጋር እንዴት አስተሳስሮ መሄድ እንደሚቻል የሚያሳይ ግልፅ ምሳሌ ነው።

የትራክተር ትርኢቱ የሚያሳየው፣ አርሶ አደሩ ቴክኖሎጂን ተቀብሎ ምርታማነቱን ለማሳደግ ያለውን ፍላጎትና ብቃት ነው።

ትራክተር መጠቀም የጊዜን ኪሳራ ይቀንሳል፣ የሥራ ጫናን ያቃልላል፣ የመሬት አጠቃቀምን ያሻሽላል፣ በመጨረሻም የምርት መጠንንና ጥራትን ያሳድጋል።

ይህ መሸጋገር ብቻ የግብርና ቴክኖሎጂ ለውጥ ሳይሆን፣ የአስተሳሰብ ለውጥ መሆኑን ያሳያል።

ይህም ወጣቱ በእርሻ ዘርፍ ላይ እንዲሳተፍ፣ እርሻን እንደ ዘመናዊ የሥራ ዕድል እንዲያይ ያበረታታል።

በአጠቃላይ፣ ዛሬ በትራክተር ትርኢት የታየው፣ አንድ የእርሻ ማሽን ብቻ ሳይሆን፣ የአዊ አርሶ አደር ወደ ብልፅግና፣ ወደ ምርታማነት እና ወደ ተስፋ የሚጓዝበት መንገድ መታየቱ ነው።

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ገፅን በምንጭነት ተጠቀምን

Photos from South Achefer Cooperative Office's post 28/11/2025

የተፋሰስ ኅብረት ስራ ማህበራት የማደራጀት እና የማቋቋም ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል...

Photos from South Achefer Cooperative Office's post 12/11/2025

በሰሜን ጎጃም ዞን በደቡብ አቸፈር ወረዳ በላሊበላ ቀጠና መሰረታዊ የገበሬዎች ሁለገብ ህብረት ስራ ማህበራት አመራሮችና የሀገር ሽማግሌዎች ስለማህበሩ የቀጣይ አገልግሎት አሰጣጥን በተመለከተ የተመደቡ የቀጠና አመራሮች በተገኙበት ውይይት ተደርጓል።

ህዳር 03/2018

Photos from South Achefer Cooperative Office's post 05/11/2025

''አርቆ ማየት አልቆ መስራት '' በሚል መሪ ቃል የ2017 ዓ/ም አፈፃፀም ግምገማ እና የ2018 ዓ/ም ዕቅድ ትውውቅ መድረክ እየተካሄደ ነወ።

በሰሜን ጎጃም ዞን በደቡብ አቸፈር ወረዳ ህብረት ሥራ ማህበር ጽ/ቤት ''አርቆ ማየት አልቆ ማየት'' በሚል መሪ ቃል የ2017 ዓ/ም በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2018 ዓ/ም እቅድ ትውውቅ መድረክ እየተካሄደ ነወ።

በመድረኩ የሰሜን ጎጃም ዞን ማዕድን መምሪያ ሀላፊ፣ የደቡብ አቸፈር ወረዳ እና የዱርቤቴ ከተማ አስተባባሪ አመራሮች፣ቋሚ ኮሚቴዎች፣የጽ/ቤቱ ሙያተኞች፣የሁለገብ ማህበር ፣የገንዘብ ቁጠባ ማህበር፣የወተት ማህበር ፣የሸማቾች ማህበር፣መስኖ እና አጋር አካላት ተሳትፈዋል።
ጥቅምት 26/2018 ዓ/ም

15/10/2025

ለ2018 በጀት ዓመት ለተቋማችን ደመወዝና ስራ ማስኬጃ የፀደቀ በጀት

Photos from South Achefer Cooperative Office's post 30/09/2025

የደ/አቸ/ወረዳ ኅብረት ስራ ማኅበራት የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም እና የ2018 ዕቅድ ትውውቅ ለጠቅላላ ለተቋሙ ሰራተኞች ተሰጠ

Photos from South Achefer Cooperative Office's post 08/09/2025

የአብችክሊ ሁለገብ ኅብረት ስራ ማህበር ያስገነበው መጋዝን

08/09/2025

ኅብረት ስራ ማህበራት ለእመርታዊ እድገት መሰረቶች ናቸው
*******
የኅብረት ስራ ማህበራት በራስ በመረዳዳትና በዲሞክራሲያዊ አስተዳደር አባላቶቻቸውን በማብቃት፣ የገቢ ማስገኛ ተግባራትን በማጎልበት፣ የሰው ሃይል አቅምን በማሳደግና የማህበረሰብ አቀፍ ኢኮኖሚን ​​በማጠናከር ዘላቂ ልማትን በማስፈን ረገድ ጉልህ ሚና ይጫወታሉ።

በተጨማሪም ለማህበራዊ ማካተት እና ፍትሃዊነት የበኩላቸውን አስተዋፅዖ እያበረከቱ ነው፡፡ ይህም ላሉን ሁሉን አቀፍ እና ተራማጅ ማህበረሰቦች ጠቃሚ ሞዴሎች መሆናቸው የአደባባይ እውነታ ነው፡፡ በአለም አቀፍ ደረጃ የልማት ግቦችን ለማሳካት ቁልፍ ተዋናዮችም ናቸው::

የህብረት ስራ ማህበራት ዜጎች ሀብትን በማሰባሰብ እና በምርት ፣በግብይት እና በሌሎችም የንግድ ስራዎች ኢኮኖሚን በማሳካት ገቢ እንዲያፈሩ እና ቀጣይነት ያለው ስራ እንዲሰሩ እመርታዊ እድል ይፈጥራሉ።
የወረስነው ዕዳ ብዙ፤ የምንጓዝበት መንገድ ረዥም፤ ሕዝባችንም ፍላጎት ሰፊ ነው፡፡ ቀስ በቀስ በሚደረግ የተለምዶ ጉዞ ወደምንፈልገው የብልጽግና ምእራፍ አንደርስም፡፡

ያለን አማራጭ አንዳንድ እርከኖችን መዝለል ነው፡፡ ህብረት ስራ ማህበራት ለሀገራዊ እድገት ትልቅ የኢኮኖሚ አቅም ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡

ለዚህ ደግሞ ፈጠራና ፍጥነት ወሳኞች ናቸው፡፡ ከተለመደው መንገድ ወጣ ማለት፣ ከተለመደው ጊዜ በላይ መሥራት፣ ከተለመደው ዋጋ በላይ መክፈልም ያስፈልገናል፡፡

ዓላማችን ከአንድ ምዕራፍ ወደ ሌላ ምዕራፍ መሻገር አይደለም፡፡ ከትናንት ዘለን ወደ ነገ መድረስ ይጠበቅብናል፡፡ የህብረት ስራ ማህበራት የሀገር ውስጥ ሃብትና ዕውቀትን በማሰባሰብ በታችኛው ደረጃ በራስ የሚተማመን ልማትን ይገነባሉ፡፡

ከዚህም ባሻገር የአባላቶችን ኢኮኖሚ በማጠናከር ማህበራዊ ትስስርን ያጎለብታል። በመሆኑም ኅብረት ስራ ማህበራት ለእመርታዊ ሃገራዊ እድገት መሰረት በመሆናቸው በመጪው አመታት ከማንኛውም ጊዜ በላቀ ሁኔታ ማዘመንና ማጠናከር ያስፈልጋል፡፡

Want your business to be the top-listed Government Service in Dubrovnik?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address


Dubrovnik