30/10/2026
ከከፋፋይ አጀንዳዎች አባላት ራስን በመጠበቅ በመደመር መንግስት እና ፓርቲ የተወጠኑ ዕቅዶችን በሚፈልገው ልክ ለመመለስ በላቀ ትጋት ሊሰሩ ይገባል።
ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ
የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ጥቅምት 20/2019 ዓ.ም
የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ አመራርና ሰራተኞች በቀጣይ የፓርቲ እና የመንግስት የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ውይይት አካሂደዋል።
የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ በመልዕክታቸው በአዲሱ የመንግስት ምስረታ ማህበረሰቡን ለማገልገል ዕድል መገኘቱ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ሳይፈቱ የቆዩ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ በተገቢው ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል እንደሆነ ተናግረዋል።
የክልሉ ቀጣይ የፓርቲና የመንግስት የትኩረት አቅጣጫዎች በዋናነት የማህበረሰቡን የልማት ጉዞ ለማፋጠንና ወደ ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማሸጋገር ብሎም የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በየደረጃው ለመመለስ የሚያስችሉ እሳቤዎች ላይ ያተኮረ መሆኑን አባሉና ሰራተኛው በመገንዘብ ለውጤታማነቱ መትጋት እንደሚገባ የቢሮ ሀላፊዋ አክለው ገልፀዋል።
በመደመር መንግሥት መርህ የሕብረተሰቡን መሰረታዊ ፍላጎት በተገቢው ለማሟላትና ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጠናከረ የቅርብ ክትትልና የመደጋገፍ ባህል ማጎልበት፣ የአንድነትና የትብብር እሴቶችን በማጠናከር የሕዝቡን የጋራ ጥቅም ማስቀደም ይገባል ሲሉ ዶ/ር ሰላማዊት አሳስበዋል።
የቢሮ ሀላፊዋ አክለውም ለጋራ ቤታችን ህልውና እውነትን፣ ግልጸኝነትንና አንድነትን መሠረት አድርገን በትብብር በመሥራት የሕዝባችንን የልማትና የጤና ጥያቄዎች በተግባር ለመመለስ በቁርጠኝነት ልንሰራ ይገባል ብለዋል።
ተደራሽነቱና ተጽዕኖ ፈጣሪነቱ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ ባለው ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚለቀቁ አሉታዊና ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት፣በጎሳና በጎጥ ለመከፋፈል የሚደረጉ የፅንፈኝነት አካሄዶችን በአግባቡ በመገንዘብ መታገል እንደሚገባም በአፅንኦት ተናግረዋል።
በመደመር መንግስት ቀይ መስመር ተብለው የተለዩ ጎሰኝነት፣ ሌብነትንና ብልሹ አሰራርን በመፀየፍና ከአድልዎ ነፃ በመሆን በአገልጋይነት ስሜት መስራትና ለጋራ ዓላማ በጋራ መቆም እንደሚገባ አሳስበዋል።
በሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ የአስተዳደርና ፋይናንስ ዘርፍ ሀላፊ አቶ አዝመራ አመኑ በበኩላቸው የዜጎችን ክብር የሚነኩ ድህነትና ኋላ ቀርነትን፣ ብልሹ አሠራርንና ሌብነትን በቁርጠኝነት በመታገል በመደመር መንግሥት መርህ ላይ ተመሥርቶ ለማህበረሰብ ተጠቃሚነት ቁርጠኛ አቋም መያዝና መትጋት እንደሚገባ ተናግረዋል።
በክልሉ በአንድነት፣ በትብብር፣ በመተሳሰብና በጋራ ሥራ በመሳተፍ ለህብረተሰብ የተሻለ ነገ ከመትጋት ባሻገር ክልሉን የሰላም፣ የልማት፣ እና የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ በጋራ እና በቅንጅት መሥራት እንደሚገባም አቶ አዝመራ ጠቁመዋል ።
የቢሮው የብልጽግና ህብረት ሰብሳቢ አቶ አለማየሁ ቦኮ የፓርቲ እና የመንግስት የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ሰነድ በማቅረብ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን በተለይም በማህበራዊ ሚዲያዎች ማንነታቸውን ደብቀው የውሸት መረጃ በሚለቁ አካላት የህዝብ አንድነት በመሸርሸር የተጀመረውን የልማት ጉዞ ለማደናቀፍ የሚደረጉ የጽንፈኝነት ተግባራትን ማውገዝ ከአባሉ እንደሚጠበቅ፤ በውይይት ወቅት በተነሱ ሀሳቦች ተመላክቷል።
በመጨረሻም በክልሉ የመደመር መንግስት እና በፓርቲው የተቀመጡ የሥርዓቱ አደጋዎች ተብሎ በተለዩት ሌብነት ፣ ጎሰኝነት ፣ መከፋፈልና ኃይልን የሚበትኑ ጉድለቶች እንዲሁም በተሳሳተ መልኩ በሀሰተኛ ማህበራዊ ሚዲያ ከሚለቀቁ አሉባልታዎች አባላትና ደጋፍ ሠራተኞች ራሳቸውን እንድጠብቁ አቅጣጫ ተቀምጧል ። በሌላ በኩል አንድነታችንን በመጠበቅ እና ልዩነት በማስወገድ በሁሉም ዘርፍ በቀደሙት ጊዜያት የተመዘገቡ ጥንካሬዎችን በማስቀጠል፣የታዩ ጉድለቶችን በማረምና በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን ለይቶ በማውጣት በትጋት መፈጸም ተጠባቂ መሆኑ ተጠቁሟል።
የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ
ጥቅምት 20/2019 ዓ.ም
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
👇👇👇👇 ይመልከቱ
Website: https://www.shb.gov.et
Facebook:
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/share/1EUdJhqmFM/
https://www.facebook.com/1000649355740¡57/posts/1065870482254128/
Telegram : https://t.me/SidamaRHB
Twitter: https://x.com/sidama_health_bureau
WhatsApp:
https://chat.whatsapp.com/K7W4vwM1mqG8SyGz4PYC71
YouTube:
https://youtube.com/?si=bjGP9rGIpwIlZWQX
Tik Tok:
https://vm.tiktok.com/ZMBCWXXx