South Ethiopia Region Finance Bureau

Call Directions Website

South Ethiopia Region Finance Bureau ይህ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ትክክለኛ የፌስቡክ ገጽ ነው። ወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ የፋይናንስ መረጃዎችን ለማግኘት ገጹን Follow, Like እና Share ያደርጉ።
(2)

የበጀት አመዳደብና የወጪ አጠቃቀምን በመቆጣጠር ውስን ሀብትን ከብክነት ለመታደግ በትኩረት እንሠራለን፦ አቶ ተወልደ ተስፋዬጥቅምት 20/2019 ዓ.ምየመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን የበጀት አመዳደብ...
30/10/2026

የበጀት አመዳደብና የወጪ አጠቃቀምን በመቆጣጠር ውስን ሀብትን ከብክነት ለመታደግ በትኩረት እንሠራለን፦ አቶ ተወልደ ተስፋዬ

ጥቅምት 20/2019 ዓ.ም

የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን የበጀት አመዳደብና የወጪ አጠቃቀም በመቆጣጠር ውስን የሆነውን ሀብት ከብክነት ለመታደግ በትኩረት እንደሚሠራ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተወልደ ተስፋዬ ገለጹ።

የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ማኔጅመንት የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን የበጀት አመዳደብና የወጪ አጠቃቀም ለመቆጣጠር በተዘጋጀው የተሻሻለ መመሪያ ላይ ውይይት አካሂዷል።

መመሪያው ተግባራዊ ሲደረግ የመንግሥትና የሕዝብ ሀብትን ከብክነት ከመታደግ ባለፈ የበጀት አጠቃቀምን ውጤታማና ቀልጣፋ ለማድረግ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ተገልጿል።

መመሪያው የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የበጀት አመዳደብና የወጪ አጠቃቀምን በተገቢው ሁኔታ በመቆጣጠር ውስን የሆነውን ሀብት በቁጠባና በብቃት እንዲጠቀሙ የሚያስችል ነው።

በተጨማሪም የክልሉን የፋይናንስ አስተዳደር ሥርዓት ይበልጥ ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግ፣ ለመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የሚመደበው በጀት በፕሮግራም በጀት አሠራር እንዲመራ፣ የዲጂታል ኤሌክትሮኒክ ክፍያ ሥርዓትና ነጠላ የትሬዠሪ አካውንትን በመጠቀም የበጀትና የወጪ ቁጥጥርን ለማጠናከር ያግዛል።

ይህም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ለተልዕኮአቸው ስኬት ወሳኝ በሆኑ የወጪ መደቦች ላይ በቂ በጀት እንዲመድቡና የተመደበላቸውን ሀብት በቁጠባና በውጤታማነት እንዲጠቀሙ ያስችላል።

በተጨማሪም የቢሮው ማኔጅመንት የተቋሙን ይፋዊ አርማና መፈክር አስመልክቶ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

በዚህም መሠረት "ውስን ሀብት ለሕዝብ ተጠቃሚነት" የሚለው መሪ ቃል የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ይፋዊ መፈክር እንዲሆን ተወስኗል።

በመድረኩ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተወልደ ተስፋዬን ጨምሮ የቢሮው ምክትል ኃላፊዎች፣ የተጠሪ ተቋማት ኃላፊዎችና የማኔጅመንት አባላት ተገኝተዋል።

ማኔጅመንቱ የድጋፋዊ ክትትል የመስክ ሪፖርትን ገምግሞ ቀጣይ የሥራ አቅጣጫ አስቀመጠጥቅምት 20/2019 ዓ.ምየደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተወልደ ተስፋዬ በተገኙበት የቢሮው...
30/10/2026

ማኔጅመንቱ የድጋፋዊ ክትትል የመስክ ሪፖርትን ገምግሞ ቀጣይ የሥራ አቅጣጫ አስቀመጠ

ጥቅምት 20/2019 ዓ.ም

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተወልደ ተስፋዬ በተገኙበት የቢሮው ማኔጅመንት የድጋፋዊ ክትትል የመስክ ሪፖርትን ገምግሞ ቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።

በቢሮው ምክትል ኃላፊዎች የተመራ ቡድን ባለፉት ቀናት በክልሉ በሚገኙት 12ቱ ዞኖችና 3ቱ ሪጅዮ ፖሊስ ከተማ አስተዳደሮች በሚገኙ የፋይናንስና ፕላንና ልማት መምሪያዎች የመስክ ድጋፋዊ ክትትል ሲያካሂድ ቆይቷል።

ድጋፋዊ ክትትሉ በፊስካል ፖሊሲ፣ በሲቪል ሰርቪስና ትብብር፣ በመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደር፣ በኢንስፔክሽንና የውስጥ ኦዲት ቁጥጥር አገልግሎት፣ እንዲሁም በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዘርፎች ላይ ያተኮረ ነበር።

ከዚህም በተጨማሪ በሥነ-ምግባር፣ በመልካም አስተዳደር፣ በሪፎርምና በሌሎች ተያያዥ የሥራ መስኮች የክትትልና የድጋፍ ሥራዎች ተከናውነዋል።

የክትትል ቡድኑ የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸምን፣ የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸምን እና የመንግሥትን የ100 ቀናት ዕቅድ መነሻ በማድረግ የግምገማ፣ የውይይትና የመረጃ ማጥራት ሥራዎችን አከናውኗል።

በዚህ መሠረት በየመዋቅሩ የተከናወኑ የመስክ ምልከታዎች ሪፖርቶች በማኔጅመንቱ ፊት ቀርበው ተገምግመዋል።

በክትትሉ ወቅት የታዩ ጠንካራ ጎኖች፣ ድክመቶችና ተግዳሮቶች በዝርዝር የቀረቡ ሲሆን፣ የተለዩ ጉድለቶችን ለማረም፣ ጠንካራ ጎኖችን ለማጠናከርና ቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ውይይት ተካሂዷል።

ማኔጅመንቱም በግምገማው የተለዩ ችግሮችን ለመፍታት የመፍትሔ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ፣ ቀጣይ የሥራ አፈጻጸምን ለማሻሻል፣ የተስተዋሉ ጉድለቶችን ለማረምና የተገኙ ጥንካሬዎችን ለማስቀጠል ትኩረት ሰጥቷል።

በመድረኩ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተወልደ ተስፋዬን ጨምሮ የቢሮው ምክትል ኃላፊዎች፣ የተጠሪ ተቋማት ኃላፊዎችና የማኔጅመንት አባላት ተገኝተዋል።

ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) በአርባምንጭ ከተማ አዲስ የተጀመሩ እና በግንባታ ላይ የሚገኙ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ምልከታ አድርገዋልየደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተስፋ...
30/10/2026

ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) በአርባምንጭ ከተማ አዲስ የተጀመሩ እና በግንባታ ላይ የሚገኙ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ምልከታ አድርገዋል

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)፥ በአርባምንጭ በመከናወን ላይ የሚገኘውን የኮሪደር ልማት ፣ የአርባምንጭ ስታዲዬም ፣ የኩልፎ ወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት እንዲሁም የክልሉ የአርባምንጭ ማዕከል የቢሮ ህንፃ የግንባታ ፕሮጀክት ጎብኝተዋል።

ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ አመራሩ በየአካባቢው የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶችን ህብረተሰቡን አስተባብሮ በጊዜ የለንም መንፈስ ቀንና ማታ በመስራት እንዲሁም ፕሮጀክቱ ያለበተን ደረጃ በየግዜው ክትትል እና ድጋፍ በማድረግ በተቀመጠለት ግዜ ማጠናቀቅ እንደሚገባ ማሳሰባቸው ይታወሳል።

በዚህ አግባብ በአርባምንጭ በመከናወን ላይ የሚገኘውን አዲስ የኮሪደር ልማት ስራ ፣ የአርባምንጭ ስታዲዬም የግንባታ ሁኔታ ፣ የኩልፎ ወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት ጅምር ስራዎች እንዲሁም በክልሉ መንግስት በመገንባት ላይ የሚገኘውን የክልሉ የአርባምንጭ ማዕከል የቢሮ ህንፃ የግንባታ ፕሮጀክት ጎብኝተዋል።

#ርዕሰመስተዳድርጽቤት

ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) የጂንካ ከተማ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት የግንባታ ሂደትን ጎበኙጥቅምት 17/2019 ዓ.ም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በ...
27/10/2026

ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) የጂንካ ከተማ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት የግንባታ ሂደትን ጎበኙ

ጥቅምት 17/2019 ዓ.ም

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘውን የጂንካ ከተማ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት የግንባታ ሂደት ጎብኝተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በጉብኝታቸው የከተማውን የውሃ ማጠራቀሚያ ሪዘርቫየር ግንባታ በመመልከት፣ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በፕሮጀክቱ የአፈጻጸም ሂደትና ቀሪ ሥራዎች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

የጂንካ ከተማ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት ከ648 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ እየተገነባ ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ከ120 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች የንጹህ መጠጥ ውሃ አገልግሎት እንደሚያቀርብ ተገልጿል።

የፕሮጀክቱ ግንባታ አፈጻጸም 96 በመቶ መድረሱንና ቀሪ ሥራዎችን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ ጥረት እየተደረገ መሆኑም በጉብኝቱ ወቅት ተመላክቷል።

ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህ ወቅት የግንባታው ሂደት በጥሩ ደረጃ ላይ መሆኑን ገልጸዋል።

የጉብኝቱ ዋና ዓላማ የፕሮጀክቱን ወቅታዊ ሁኔታ በመገምገም ቀሪ ሥራዎች በአጭር ጊዜ እንዲጠናቀቁና ፕሮጀክቱ ለሕብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሰጥ ከክልሉ መንግሥትና ከዞኑ አስተዳደር የሚጠበቀውን ድጋፍ ለመለየት መሆኑን አስረድተዋል።

ፕሮጀክቱን በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ የሥራ ባህልን በመቀየር ቀንና ሌሊት በመሥራት ቀሪ ሥራዎችን በፍጥነት ማጠናቀቅና ለሕብረተሰቡ ንጹህ የመጠጥ ውሃ ተደራሽ ማድረግ እንደሚገባም አሳስበዋል።

የከተማው ነዋሪዎች ከፕሮጀክቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ግንባታው በአጭር ጊዜ ተጠናቆ ወደ አገልግሎት እንዲገባ የክልሉ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም አረጋግጠዋል።

#ርዕሰመስተዳድርጽቤት

በክልሉ በ12ቱ ዞኖችና በ3ቱ ሪጅዮ ፖሊስ ከተማ አስተዳደሮችየፋይናንስና ፕላንና ልማት መምሪያዎች የተጀመረው ድጋፋዊ ክትትል ተጠናክሮ ቀጥሏልጥቅምት 17/2019 ዓ.ምበደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ...
27/10/2026

በክልሉ በ12ቱ ዞኖችና በ3ቱ ሪጅዮ ፖሊስ ከተማ አስተዳደሮች
የፋይናንስና ፕላንና ልማት መምሪያዎች የተጀመረው ድጋፋዊ ክትትል ተጠናክሮ ቀጥሏል

ጥቅምት 17/2019 ዓ.ም

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊዎች የተመራ ቡድን በክልሉ በሚገኙት 12ቱ ዞኖችና 3ቱ ሪጅዮ ፖሊስ ከተማ አስተዳደሮች ለሚገኙ የፋይናንስና ፕላንና ልማት መምሪያዎች እያካሄደ የሚገኘው ድጋፋዊ ክትትል ተጠናክሮ ቀጥሏል።

ድጋፋዊ ክትትሉ ዓላማ በ2019 በጀት ዓመት በዞኖችና በከተማ አስተዳደሮች በሚከናወኑ የሀብት አስተዳደር ሥራዎች ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን መለየት፣ ተገቢ የመፍትሔ አቅጣጫዎችን ማስቀመጥና የአፈጻጸም አቅምን በማጠናከር ውጤታማና ቀልጣፋ የሀብት አስተዳደርን ማረጋገጥ ነው።

ክትትሉ በፊስካል ፖሊሲ፣ በሲቪልና ትብብር፣ በመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደር፣ በኢንስፔክሽንና የውስጥ ኦዲት ቁጥጥር አገልግሎት እንዲሁም በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዘርፎች ላይ ያተኮረ ነው።

በተጨማሪም በሥነ-ምግባር፣ በመልካም አስተዳደር፣ በሪፎርምና በሌሎች ተያያዥ የሥራ መስኮች ላይ የክትትልና የድጋፍ ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።

የክትትሉ ዋና ትኩረት የመምሪያዎቹን የሥራ አፈጻጸም መገምገም፣ የተመዘገቡ ውጤቶችንና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን መለየት፣ በሥራ ሂደቶች ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን ለማረም የሚያስችሉ የመፍትሔ ሐሳቦችን ማቅረብና ለቀጣይ ሥራዎች የተቀናጀ አቅጣጫ ማስቀመጥ ነው።

የድጋፋዊ ክትትሉ ሥራ የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸምን፣ የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸምንና የመንግሥትን የ100 ቀናት ዕቅድ መነሻ በማድረግ የግምገማ፣ የውይይትና የመረጃ ማጥራት ሥራዎችን በማከናወን ተጀምሯል።

በዚህም የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸምን ከዕቅድ አንጻር መገምገም፣ የ100 ቀናት ዕቅድ አፈጻጸምን መከታተልና የሥራ ሂደቶችን ለማሻሻል የሚረዱ መረጃዎችን ማጥራት ላይ ትኩረት ተደርጓል።

የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ በ12ቱም ዞኖችና በ3ቱም ሪጅዮ ፖሊስ ከተማ አስተዳደሮች ድጋፋዊ ክትትል እያካሄደ ነውጥቅምት 16/2019 ዓ.ምበደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊዎ...
26/10/2026

የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ በ12ቱም ዞኖችና በ3ቱም ሪጅዮ ፖሊስ ከተማ አስተዳደሮች ድጋፋዊ ክትትል እያካሄደ ነው

ጥቅምት 16/2019 ዓ.ም

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊዎች የተመራ ቡድን በክልሉ በሚገኙት 12ቱም ዞኖችና 3ቱም ሪጅዮ ፖሊስ ከተማ አስተዳደሮች የፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያዎችን ያማከለ ድጋፋዊ ክትትል እያካሄደ ይገኛል።

ድጋፋዊ ክትትሉ የፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያዎች የሥራ አፈጻጸምን በመገምገም፣ የተገኙ ውጤቶችንና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በመለየት እንዲሁም ለቀጣይ ሥራዎች የተቀናጀ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ ነው።

የክትትሉ ሥራ የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም፣ የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም እና የመንግሥትን የ100 ቀናት ዕቅድ መነሻ በማድረግ የግምገማ፣ የውይይትና የመረጃ ማጥራት ሥራዎችን በማከናወን ተጀምሯል።

በዚህም የበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸምን በዕቅድ አንጻር መመርመር፣ የ100 ቀናት ዕቅድ አፈጻጸምን መከታተልና የሥራ ሂደቶችን ለማሻሻል የሚያስችሉ መረጃዎችን ማጥራት ላይ ትኩረት ተደርጓል።

ድጋፋዊ ክትትሉ በክልሉ የፋይናንስ አስተዳደርን የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ፣ የዕቅድና የአፈጻጸም ትስስርን ለማጠናከር፣ በሥራ ሂደቶች የሚታዩ ክፍተቶችን ለመለየትና ተገቢውን የሙያ ድጋፍ ለመስጠት የሚያግዝ ነው።

የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ በድጋፋዊ ክትትሉ የሥራ አፈጻጸምን ከመገምገም ባሻገር ተግዳሮቶችን በጋራ በመፍታት፣ የተሻሉ አሠራሮችን በማስፋፋትና የፋይናንስ አስተዳደርን በማጠናከር ለተሻለ የሕዝብ አገልግሎት ለመሥራት ትኩረት ሰጥቷል።

"የሕዝቡን የልማት ጥያቄዎች በቅድሚያ በመለየት ደረጃ በደረጃ ለመመለስ እንሠራለን"፦ ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)ጥቅምት 15/2019 ዓ.ምከሕብረተሰቡ የሚነሱ የልማትና የመልካም...
25/10/2026

"የሕዝቡን የልማት ጥያቄዎች በቅድሚያ በመለየት ደረጃ በደረጃ ለመመለስ እንሠራለን"፦ ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)

ጥቅምት 15/2019 ዓ.ም

ከሕብረተሰቡ የሚነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በመለየት ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡትን በማስቀደም ደረጃ በደረጃ ለመመለስ እንደሚሠራ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ገለጹ።

በሳውላ ከተማ ከሕብረተሰቡ ጋር በተደረገው ውይይት፣ የቡልቂ ጤና ጣቢያን ወደ መለስተኛ ሆስፒታል የማሳደግ፣ የሳውላ ሪፈራል ሆስፒታል ግንባታ፣ የስታዲየምና የኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ፣ የመንገድ፣ የመጠጥ ውሃና የኤሌክትሪክ አቅርቦትን ጨምሮ ሌሎች መሠረተ ልማቶች እንዲሟሉ ሕብረተሰቡ ጥያቄ አቅርቧል።

በተጨማሪም የሶዶ–ሳውላ መንገድ ግንባታ ጥራቱን ጠብቆ እንዲጠናቀቅ ጠይቋል።

ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) በውይይቱ ማጠቃለያ ሳውላና አካባቢው ታላቅ ሕዝብ የሚኖርበት አካባቢ መሆኑን ጠቅሰው፣ ከሕብረተሰቡ ጋር በመተባበር ያሉትን እምቅ የልማት አቅሞች በመጠቀም ለሕዝቡ የሚጠቅሙ ሥራዎችን ለማከናወን ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የመንገድ፣ የውሃ፣ የጤና፣ የኤሌክትሪክ፣ የኢንዱስትሪ ፓርክና የስታዲየም ግንባታ ለአካባቢው ልማት ወሳኝ መሆናቸውን አመላክተዋል።

በውይይቱ የተነሱት ጥያቄዎች በተገቢው መረጃ ተመሥርተው ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ ፕሮጀክቶች እንዲለዩና ተገቢውን ምላሽ እንዲያገኙ እንደሚሠራ ርዕሰ መስተዳድሩ አረጋግጠዋል።

በተጨማሪም በኢንዱስትሪው ዘርፍ ኢንቨስትመንትን በማስፋፋት የሥራ ዕድልና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን ለማሳደግ እንደሚሠራ አመልክተዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዋና የመንግሥት ተጠሪ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ለተደረገላቸው አቀባበል ምስጋና አቅርበዋል።

ከዚህ ቀደምም ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጋር በመወያየት የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመፍታት ጥረቶች ሲደረጉ መቆየታቸውን ገልጸዋል።

የብልጽግና ፓርቲ አካታችነትን መሠረት ያደረገ ፓርቲ በመሆኑ፣ ከመላው ሕዝብ ጋር በጋራ በመሥራት የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመፍታት በትኩረት እንደሚሠራም አረጋግጠዋል።

የሕዝብ ተሳትፎ ለልማት ሥራዎች ውጤታማነት ወሳኝ መሆኑን ያስገነዘቡት ዶ/ር አበባየሁ፣ ሕብረተሰቡ በቀጣይ በሚከናወኑ የልማት ሥራዎች በንቃት እንዲሳተፍና እንዲያግዝ ጥሪ አቅርበዋል።

ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ወደ ጎፋ ዞን ሣውላ ከተማ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸውሣውላ፤ ጥቅምት 15/2019 ዓ.ምየደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በል...
25/10/2026

ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ወደ ጎፋ ዞን ሣውላ ከተማ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

ሣውላ፤ ጥቅምት 15/2019 ዓ.ም

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ለይፋዊ የሥራ ቆይታ በጎፋ ዞን ሣውላ ከተማ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው።

ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ በሰላምና በብዝኃነት ተምሳሌት በሆነችው ሣውላ ከተማ ሲደርሱ፣ በክልሉ የሣውላ ማዕከል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ በጎፋ ዞንና በሣውላ ከተማ አስተዳደር አመራሮች፣ በሀገር ሽማግሌዎችና በከተማው ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። መላው የአካባቢው ማኅበረሰብም ልባዊ ፍቅሩንና አክብሮቱን ገልጾላቸዋል።

ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ በጎፋ ዞን በሚኖራቸው ቆይታ፣ ከዞኑና ከሣውላ ከተማ አስተዳደር ከተውጣጡ የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ተወካዮችና አመራሮች ጋር በሰላም፣ በመልካም አስተዳደርና በልማት ጉዳዮች ዙሪያ ይመክራሉ።

ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ በሁሉም ዘርፎች የሚከናወኑ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎችን ውጤታማነት ለማረጋገጥ፣ ከሕዝቡ ጋር በመወያየትና የጋራ መግባባት በመፍጠር የልማት ትብብርንና ተሳትፎን ማሳደግ መሠረታዊ መሆኑን በማመን፣ በተለያዩ ዞኖች ከሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎች ተወካዮች ጋር ውይይቶችን እያካሄዱ ይገኛሉ።

የዚሁ ጥረት አካል በሆነው የዛሬው የሣውላ ከተማ ቆይታቸውም፣ ከጎፋ ዞንና ከሣውላ ከተማ ከተውጣጡ የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ተወካዮች ጋር በመወያየት በቀጣይ የልማት ተግባራት ዙሪያ የጋራ መግባባት እንደሚፈጥሩ ይጠበቃል።

"በመደመር መንግሥት ሌብነትና ብልሹ አሠራር ቀይ መስመር ነው"-  ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)ጥቅምት 14/2019 ዓ.ም ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ከጌዴኦ ዞንና...
24/10/2026

"በመደመር መንግሥት ሌብነትና ብልሹ አሠራር ቀይ መስመር ነው"- ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)

ጥቅምት 14/2019 ዓ.ም

ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ከጌዴኦ ዞንና ከዲላ ከተማ ከተውጣጡ የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ተወካዮችና አመራሮች ጋር በሰላም፣ በመልካም አስተዳደርና በልማት ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ።

በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

በመደመር መንግሥት መሪነት፣ በአዲስ የሥራ ባህልና የአመራር ሥርዓት እንዲሁም በአዲስ ጉልበት የክልሉን ሕዝብ አንድነትና የልማት ትብብር በማጠናከር ለሁሉም የተመቸችና የበለጸገች ደቡብ ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በሙሉ አቅም ወደ ሥራ መገባቱን አስታውቀዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በውይይቱ ከማኅበረሰቡ የተነሱ የመልካም አስተዳደር፣ የልማት፣ የሰላም፣ የሕዝቦች አንድነትና የዕርስ በዕርስ ትስስር ማጠናከር ጋር በተያያዘ የቀረቡ ጥያቄዎችን በተገቢው መንገድ ለመመለስ እንደሚሠራ አረጋግጠዋል።

በተለይም በአጭር ጊዜ ምላሽ የሚያስፈልጋቸውንና ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ አጣዳፊ ጥያቄዎችን በመለየት በተያዘው የ100 ቀናት ዕቅድ ውስጥ አካቶ ከዳር ለማድረስ እንደሚሠራ ገልጸዋል።

የቀሩትን ጥያቄዎች ደግሞ በመካከለኛና በረጅም ጊዜ ዕቅዶች በማካተት ምላሽ ለመስጠት እንደታቀደ አስረድተዋል።

መንግሥትና ሕዝብ እጅና ጓንት ሆነው በጋራ ሲሠሩ ልማት ይሳካል ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)።

የጌዴኦ ዞንና የዲላ ከተማ ማኅበረሰብ ጥያቄ አቅራቢ ብቻ ሳይሆን የልማቱ ባለቤት በመሆን በሁሉም ዘርፍ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ በሚደረገው ጥረት የልማት ተሳትፎውን በማሳደግ የራሱን አሻራ ማኖር እንዳለበት አሳስበዋል።

ከሰላም አኳያም የክልሉ መንግሥት ጥቂት ግለሰቦች የግል ፍላጎታቸውን ለማሳካት ሲሉ የሕዝቦችን አንድነት ለመከፋፈል፣ የወንድማማችነት ትስስርን ለማዳከምና ሰላምን ለማደፍረስ የሚሠሩ አካላትን እንደማይታገስ ገልጸዋል።

ለዚህም የአመራሩ ቁርጠኝነትና የማኅበረሰቡ ተሳትፎ እና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

በክልሉ ሌብነትና ብልሹ አሠራር ቀይ መስመር እንደሆኑ ያስገነዘቡት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ ሕዝቡን በአግባቡ ለማገልገል፣ የሕዝብ ሀብት ለሕዝብ ጥቅም እንዲውልና የመንግሥት ሥልጣን ለሕዝብ አገልግሎት እንዲውል በትኩረት እንደሚሠራ አረጋግጠዋል።

በዚህ ረገድ የጌዴኦ ማኅበረሰብ ያሉትን ድንቅ አገር በቀል እሴቶች በመጠቀም፣ ወጣቱ ትውልድ ስርቆትንና ሌብነትን የሚጸየፍ ስብዕና እንዲገነባ የሃይማኖት ተቋማት ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ሁሉም አካላት ይህንን ታሪካዊ ኃላፊነት እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል።

መዳረሻችን ሁለንተናዊ ብልጽግና ነው፤ ተደማሪ አቅማችንም ትልቅ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

በክልሉ ያሉ ጸጋዎችንና እምቅ የልማት አቅሞችን ወደ ተጨባጭ ዕድገት በመቀየር የክልሉን ሕዝብ ፍትሐዊ ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ ባለፈ፣ ዘላቂ ሰላምን፣ ልማትንና ብልጽግናን ለማረጋገጥ መንግሥት በትጋት እንደሚሠራ አስታውቀዋል።

የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ የአመራር ስኬት የሚለካው በፈታው ችግር መጠን እንደሆነ ገልጸው፣ ከአመራሩ ጋር በዚህ ላይ መግባባት መደረሱን ጠቁመዋል።

የሕዝብን ጥያቄዎች ለመመለስ ያለውን አቅም በሙሉ በመጠቀም በልዩ ትኩረት እንደሚሠራም ተናግረዋል።

ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ በዲላ ከተማ የኮሪደር ልማት ጅምር ሥራዎችን ጎበኙየደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) በዲላ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ጅ...
24/10/2026

ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ በዲላ ከተማ የኮሪደር ልማት ጅምር ሥራዎችን ጎበኙ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) በዲላ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ጅምር ሥራዎችን ጎብኝተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በከተማዋ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን በመጎብኘት ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ ጉብኝቱም በከተማዋ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎችን ለመመልከት ያለመ ነው።

Address

Wolaita S**o Town
Awassa
104

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when South Ethiopia Region Finance Bureau posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share