ANRS Prison Commission

Call Directions

ANRS Prison Commission Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ANRS Prison Commission, Government Organization, Bahir Dar.

የአማራ ክልል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን /Amara Prison Commission/ is a Government Organization works with the federal prison commission under the mission to administer prisoners and make them skilled, patriotic and horned citizen.

በምዕራብ ጎንደር ዞን ማረሚያ ቤት በሰብል ልማት የሰለጠኑ 11 ታራሚዎች የምስክር ወረቀት ተረከቡ ጥቅምት 16/2019 ዓ.ም (ገንድውሀ) ማረሚያ ቤቶች የቅጣት ብቻ ሳይሆን የስልጠና፣ የትምህ...
26/10/2026

በምዕራብ ጎንደር ዞን ማረሚያ ቤት በሰብል ልማት የሰለጠኑ 11 ታራሚዎች የምስክር ወረቀት ተረከቡ

ጥቅምት 16/2019 ዓ.ም (ገንድውሀ)

ማረሚያ ቤቶች የቅጣት ብቻ ሳይሆን የስልጠና፣ የትምህርት እና የብቃት ማበልጸጊያ ማዕከላት እየሆኑ መምጣታቸውን የሚያሳይ ዜና ከምዕራብ ጎንደር ዞን ማረሚያ ቤት ተሰምቷል።
ማረሚያ ቤቱ ከሐምሌ 2018 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ በግብርናው ዘርፍ በሰብል ልማት ዙሪያ ለሶስት ወራት ሲሰጥ የቆየውን ጥልቅ የዕውቀትና የተግባር ስልጠና በተሳካ ሁኔታ አጠናቀዋል።

በዚህም መሰረት በስልጠናው ቆይታቸው ከፍተኛ ተነሳሽነትና ትጋት ያሳዩ 11 ታራሚዎች የስኬት ማረጋገጫ የሆነውን የምስክር ወረቀት ተረክበዋል።

ታራሚዎች ጊዜያቸውን በቁጭት ብቻ እንዲያሳልፉ ሳይሆን፣ ከማኅበረሰቡ ሲገለሉ የቆዩባቸውን ክፍተቶች በክህሎት ሞልተው በምርት ዘመን ዳግም አብበው እንዲወጡ ለማስቻል የታለመው ይህ መርሃ ግብር፣ በግብርናው መስክ ዘመናዊና ስልታዊ አሰራሮችን በማስተማር ረገድ ትልቅ ትርጉም አለው።

ለሶስት ወራት ያህል ንድፈ-ሀሳብን ከተግባር ጋር በማቀናጀት በተሰጠው በዚህ ስልጠና፤
የሰብል አያያዝ፣
የምርትና የዘር ዝግጅት፣
እንክብካቤና አሰባሰብ ቴክኒኮች በጥልቀት ተሰጥተዋል።

ይህ ስልጠና ታራሚዎቹ የእስር ጊዜያቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙበት በማድረግ በምርት ዘመኑ አምራች ዜጎች እንዲሆኑ ትልቅ እምነት የጣለና የወደፊት ሕይወታቸውን በብሩህ ተስፋ እንዲቃኙ የሚያስችል ነው።

በምዕራብ ጎንደር ዞን ማረሚያ ቤት የተሰጠው ይህ የምስክር ወረቀት አሰጣጥ ስነ-ሰርዓት፣ በታራሚዎች ሕይወት ውስጥ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ነው።

የዕውቀት ባለቤት ሆነው ከእስር ሲወጡ በግብርናው ዘርፍ እራሳቸውንና ቤተሰባቸውን ለመደገፍ፣ እንዲሁም ለሀገራቸው እድገት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት የሚያስችል ጠንካራ መሰረት ጥሏል።
ይህ ክስተት ማረሚያ ቤቶች ማረሚያ ብቻ ሳይሆኑ፣ ሰውን ሰርቶ የማብቃት እና የማነጽ ታላቅ አቅም እንዳላቸው የሚመሰክር ድንቅ የለውጥ ምዕራፍ ሆኖ ተመዝግቧል።

በ2026  # በሴነጋል ሀገር ዳካር ከተማ ለሚካሄደው የወጣቶች ኦሎምፒክ ውድድር ለሀገሬ ጥሩ ውጤት ለማምጣት በቂ ዝግጅት አድርጊያለው ፦ ም/ሳጅን ኤልሳቤጥ አማረጥቅምት :- 16/2019 ዓ/...
26/10/2026

በ2026 # በሴነጋል ሀገር ዳካር ከተማ ለሚካሄደው የወጣቶች ኦሎምፒክ ውድድር ለሀገሬ ጥሩ ውጤት ለማምጣት በቂ ዝግጅት አድርጊያለው ፦
ም/ሳጅን ኤልሳቤጥ አማረ

ጥቅምት :- 16/2019 ዓ/ም
/የአማራ ክልል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን /

በ2026 # በሴነጋል ሀገር ዳካር ከተማ በህዳር ወር ለሚካሄደው በ1,500 ሜትር የወጣቶች ኦሎምፒክ ውድድር ለሀገሬ ጥሩ ውጤት ለማምጣት በቂ ዝግጅት መደረጉ ተገለፀ።

የአማራ ክልል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን አትሌቲክስ ክለብ ካፈራቸው ስመ ጥርና ጀግና አትሌቶች መካከል አንዷ የሆነችው አትሌት ም/ሳጅን ኤልሳቤጥ አማረ እንደገለፀችሁ ከዚህ በፊት በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር በተለያዩ የውድድር አይነቶች በመሳተፍ በርካታ የወርቅና የብር ሜዳልያ ለሀገራቸው ማስመዝገባቸውን አስታውሰው በቀጣይ ህዳር ወር 2026 # ሴኔጋል ዳካር ከተማ ለሚካሄደው የወጣቶች ኦሎምፒክ በ1,500 ሜትር ውድድር ለመሳተፍ ከግንቦት ወር ጀምሮ ወደ ሆቴል በመግባት በማናጀር እየታገዝን ጥሩ ዝግጅት እያደረኩ እንገኛለን ብለዋል አትሌቷ አክለውም በኦሎምፒክ ውድድሩ ለሀገሬ ጥሩ ውጤት ለማምጣት ከፈጣሪ ጋር በቂ ዝግጅት እያደረኩ እገኛለው ሲሉ ገልፀዋል ።

"ለጀግና አትሌታችን መልካም እድልእንመኛለን "

ዘገባው:- የአማራ ክልል ማረ/ቤት ኮሚሽን ህ/ግንኙነት
ለበለጠ መረጃ
​🔗 እኛን ይከተሉ / Follow Us:
​📘 pageANRS Prison CommissionR/
​🎵 TikTok Account: https://www.tiktok.com/.prison.office.com
​✈️ Telegram Channel: https://t.me/AmharaPrisonOffice_12
​▶️ YouTube Channel: https://youtube.com/

የደባርቅ universitiy እና የዞን መምሪያ ኃላፊዎች እና  የማኔጅመንት አባላት በሰሜን ጎንደር ዞን ማረሚያ ቤት መምሪያ የሥራ ጉብኝት አደረጉ​ደባርቅ — ጥቅምት 14 ቀን 2019 ዓ.ም​...
24/10/2026

የደባርቅ universitiy እና የዞን መምሪያ ኃላፊዎች እና የማኔጅመንት አባላት በሰሜን ጎንደር ዞን ማረሚያ ቤት መምሪያ የሥራ ጉብኝት አደረጉ
​ደባርቅ — ጥቅምት 14 ቀን 2019 ዓ.ም
​በዛሬው ዕለት የደባርቅ universitiy ከፍተኛ ማኔጅመንት አባላት እና ልዩ ልዩ የዞን መምሪያ የሥራ ኃላፊዎች በሰሜን ጎንደር ዞን ማረሚያ ቤት መምሪያ በመገኘት በግቢው ውስጥ የሚገኙ አገልግሎቶችን እና የተቋሙን አጠቃላይ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
​በጉብኝታቸው ወቅት የማኔጅመንት አባላቱ በሁለቱም የወንዶች እና የሴቶች ህግ ታራሚዎች የመኝታ ክፍሎች በአካል በመግባት የታራሚዎችን የመኖሪያ ሁኔታ እና የሚያጋጥሙ ተጨባጭ ችግሮችን በቅርበት ተመልክተዋል።
​የስራ ጉብኝቱን አስመልከተው የሰሜን ጎንደር ዞን ማረሚያ ቤት መምሪያ ኃላፊ የሆኑት ዋ/ር አበበ አዳነ ለልዑካኑ በሰጡት ገለፃ፤ “የታራሚዎችን አያያዝ ለማሻሻልና የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ የማረሚያ ቤቱ ጥረት ብቻውን በቂ ባለመሆኑ፣ የችግሩን አጣዳፊነት ተረድታችሁ ሁሉም አካላት አስፈላጊውን ድጋፍና ትብብር ልታደርጉልን ይገባል” ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
​በጉብኝቱ የተሳተፉት የደባርቅ universitiy ማኔጅመንት አባላት በበኩላቸው፤ በተቋሙ ያለውን ችግርና ፍላጎት በግንባር በመገኘት በግልጽ ለመረዳት መቻላቸውን ገልጸው፣ የሚጠበቅባቸውንና የሚቻላቸውን ድጋፍ ሁሉ ለማድረግ ሙሉ ቃል ገብተዋል።
​በተመሳሳይ መልኩ የሌሎች ዞን መምሪያ ማኔጅመንት አባላት ተቋሙ የሚያከናውናቸውን ሰብአዊና የእርምት ሥራዎች በማጠናከር ረገድ ከማረሚያ ቤት መምሪያው ጋር በቅንጅትና በጋራ ለመሥራት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
​ይህ የጋራ ጉብኝት ተቋማቱ በማረሚያ ቤቱ የሚታዩ መሠረታዊ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታትና የሰብአዊ መብት አያያዝን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያደርጉትን የተቀናጀ ጥረት የሚያጠናክር መሆኑ ተገልጿል።


19/10/2026
የምዕራብ ጎጃም ዞን ማረሚያ ቤት መምሪያ የልማት ስራዎችን በማስፋፋትና ትምህርት በመስጠት የሕግ ታራሚዎችን ሁለንተናዊ ሰብዕና እየገነባ ይገኛል።​ጥቅምት 2/2019 ዓ.ም ፍኖተ ሠላም (ምዕ...
12/10/2026

የምዕራብ ጎጃም ዞን ማረሚያ ቤት መምሪያ የልማት ስራዎችን በማስፋፋትና ትምህርት በመስጠት የሕግ ታራሚዎችን ሁለንተናዊ ሰብዕና እየገነባ ይገኛል።

​ጥቅምት 2/2019 ዓ.ም ፍኖተ ሠላም (ምዕራብ ጎጃም)

​የምዕራብ ጎጃም ዞን ማረሚያ ቤት መምሪያ የተሰጠውን የማረም እና የመቅረፅ ተልዕኮ በብቃት ለመወጣት የሚያስችሉ ሁለገብ የልማት ስራዎችን አጠናክሮ እያከናወነ እንደሚገኝ አስታወቀ።

​መምሪያው ካሉት ውስን ሀብቶች መካከል መሬትን አሟጦ በመጠቀም ረገድ አበረታች ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።

በዚህም መሠረት በ1.5 ሄክታር መሬት ላይ ያለማውን የበቆሎ ሰብል ጨምሮ ተጨማሪ ቦታዎችን በማልማት የተለያዩ ቋሚ የፍራፍሬ ተክሎችን፣ የአትክልት ዓይነቶችን እንዲሁም የከብት እርባታ ስራዎችን በሰፊው እያከናወነ ይገኛል።

​በማረሚያ ቤቱ እየተከናወኑ ያሉ እነዚህ የልማት ስራዎች የነዋሪውን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥና የውስጥ ገቢን ለማሻሻል ከማስቻላቸው ባለፈ፤ ለሚከናወኑ የተለያዩ የውስጥ መሠረተ ልማት እና ግንባታ ስራዎች አዎንታዊ አስተዋፅኦ እያበረከቱ መሆኑ ተገልጿል።

​ከዚሁ ጎን ለጎን፣ በማረሚያ ቤቱ ውስጥ የሚካሄደው የእንስሳት እርባታና የግብርና ልማት ስራ የሕግ ታራሚዎች በተግባር የተደገፈ እውቀትና ክህሎት እንዲጨብጡ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።

ታራሚዎች በእነዚህ የልማት ስራዎች ላይ በንቃት በመሳተፍ ጉልበታቸውንና እውቀታቸውን በመጠቀም የተቋሙን አቅም የመገንባት እንዲሁም የራሳቸውን ሰብዕና የማነፅ እድል አግኝተዋል።

​ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ተቋሙ የታራሚዎችን የትምህርት ደረጃ ለማሳደግ በሚያደርገው ጥረት ከዚህ ቀደም ተቋርጦ የነበረውን ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል የመደበኛ ትምህርት የመማር ማስተማር ሂደት እንደገና በመጀመር ስራ ላይ አውሏል።

በተጨማሪም ከንድፈ-ሀሳብ ባለፈ በገበያው ዘንድ ተፈላጊ የሆኑ የሙያና ክህሎት ስልጠናዎች በስፋት እየተሰጡ ይገኛሉ።

​ታራሚዎች የእርምት ጊዜያቸውን አጠናቀው ወደ ህብረተሰቡ በሚቀላቀሉበት ወቅት በቆይታቸው ያዳበሩትን መልካም የስራ ባህል፣ የቀሰሙትን ሙያዊ እውቀትና ክህሎት በመጠቀም ፈጥነው ወደ ስራ በመግባት ራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን በምግብና በኢኮኖሚ ለመደገፍ የሚያስችላቸው ሙሉ ዝግጅት መደረጉ ተመላክቷል።



09/10/2026

ደብረ ማርቆስ ማረሚያ ቤት በለውጥ ሂደት ላይ ያለ ትቋም

የባህር ዳር ከተማ ከተማ አሰ/ ማረሚያ ቤት ለታራሚዎች በሚሰጠው የሙያ ስልጠና ዙሪያ የፓናል ውይይት አካሄደ፡፡ባህር ዳር መስከረም 29/2019 ፦ የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ማረሚያ ቤት ...
09/10/2026

የባህር ዳር ከተማ ከተማ አሰ/ ማረሚያ ቤት ለታራሚዎች በሚሰጠው የሙያ ስልጠና ዙሪያ የፓናል ውይይት አካሄደ፡፡

ባህር ዳር መስከረም 29/2019 ፦
የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ማረሚያ ቤት መምሪያ ለታራሚዎች የሚሰጠውን የሙያ ስልጠና ግንዛቤ ለማሳደግ፣ የስልጠና አሰጣጡን ለማሻሻልና አፈጻጸሙን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ ታላቅ የፓናል ውይይት አካሂዷል።

የውይይቱ ዋና ዓላማ ታራሚዎች በማረሚያ ቤት ቆይታቸው ጠቃሚ እውቀትና ሙያዊ ክህሎት እንዲያገኙ፣ አመለካከታቸውን እንዲቀይሩ፣ በራሳቸው እንዲተማመኑና ከማረሚያ ቤት ከወጡ በኋላ በሕብረተሰቡ ውስጥ ጠቃሚና አምራች ዜጋ ሆነው እንዲኖሩ ማስቻል ነው።

በመድረኩ የሙያ ስልጠናዎች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

መድረኩን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት የማረሚያ ቤቱ ምክትል መምሪያ ኃላፊና የጥበቃ ደህንነት ቡድን መሪ ተወካይ ኮ/ር ደሳለኝ ሲሳይ ሲሆኑ፣ ሰልጣኞች ለስልጠናው ተገቢውን ትኩረት በመስጠት ከቀረቡት ሀሳቦች በተግባር ሊጠቀሙባቸው የሚችሉትን እውቀት እንዲያገኙ አሳስበዋል።

የትምህርትና ስልጠና ቡድን መሪ ኮ/ር ፍርዳወቅ እንዳለው የመነሻ ጽሑፍ በማቅረብ በማረሚያ ቤቱ የሚሰጡ የሙያ ስልጠናዎችንና አፈጻጸማቸውን አብራርተዋል።
በማረሚያ ቤቱ እየተሰጡ ካሉ የስልጠና ዘርፎች መካከል፦
ኮንስትራክሽንና የእደ ጥበብ ስራዎች፤
ብየዳና ማኑፋክቸሪንግ፤
ግንባታና ቴክኒክ፤
ግብርና፣ የእንስሳት እርባታና የዓሣ ምርት እንክብካቤ፤
የእጅ ስራዎች፣ የውበት ሳሎንና የዳቦ ጋጋራ ስራዎች ይገኙበታል።
እነዚህ ስልጠናዎች የታራሚዎችን ክህሎት ለማሳደግ፣ እውቀታቸውን ለማሻሻል፣ የስራ እድል ፈጥረው እንዲኖሩና ከእስር በኋላ በኢኮኖሚያዊና በስነ-ልቦናዊ ጉዳዮች ራሳቸውን ችለው እንዲቆሙ ለማስቻል ያለሙ ናቸው።

ከተሳታፊዎች ገንቢ ሀሳቦችና ጥያቄዎች ቀርበዋል።

በውይይቱ ላይ የተሳተፉ ሰልጣኞች የተሰጣቸውን የሙያ ስልጠና እድል በማድነቅ፣ ያገኙትን እውቀት ተጠቅመው ራሳቸውንና የወደፊት ሕይወታቸውን ለመለወጥ ያላቸውን ዝግጁነት ገልጸዋል።
በተጨማሪም የሙያ ስልጠናዎቹ በብቃት ምዘና (COC) ማረጋገጫ ተደግፈው ታራሚዎች ከማረሚያ ቤት ከወጡ በኋላ በስራ ገበያው ላይ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ሰርተፍኬት እንዲያገኙ፣ የኮምፒዩተር ስልጠና እንዲስፋፋ፣ የመንጃ ፈቃድ ስልጠና እንዲጀመርና ከስልጠና በኋላ የሚመረቱ ምርቶችን ለገበያ ለማቅረብ የፈጠራ ስራዎች በጀት እንዲመደብ የሚሉ ሀሳቦችና ጥያቄዎች ቀርበዋል።

ለተነሱት ሀሳቦች ምላሽ ተሰጥቷል።

የማረምና ማነጽ ቡድን መሪ አቶ ግርማ ጥሩነህ፣ ታራሚዎች ሙያ በመቅሰምና በተሰጣቸው እድል በመጠቀም ራሳቸውን ለለውጥ ማዘጋጀት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
ኮ/ር ደሳለኝ ሲሳይ በበኩላቸው፣ የታራሚዎችን ሙያዊ ክህሎት የማሳደጉ ስራ በዚህ ውይይት ብቻ እንደማይቆም ገልጸው፣ እያንዳንዱ የሂደት መሪ የሙያ ድጋፍና ክትትል መስጠቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
አንዳንድ ጥያቄዎች የበላይ አካላትን ፈቃድና የበጀት ድጋፍ የሚጠይቁ በመሆናቸው፣ በተገቢው ሁኔታ እንደሚታዩ በመጠቆም ውይይቱ ተጠናቋል።

በአጠቃላይ፣ የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ማረሚያ ቤት መምሪያ በታራሚዎች ላይ በሚያከናውነው የሙያ ስልጠናና የማረም ማነጽ ስራ ታራሚዎች የተሻለ እውቀትና ክህሎት እንዲያገኙ፣ ራሳቸውን ችለው እንዲኖሩና ወደ ሕብረተሰቡ ሲመለሱ ጠቃሚ ዜጋ እንዲሆኑ የሚያግዝ መሠረት እየተጣለ መሆኑን ያሳያል።
ሙያ ለሕይወት፤ እውቀት ለለውጥ፤ ስልጠና ለተሻለ ነገ!
_አስተዳደር _ማረሚያቤት_ህ/ግንኙነት_ባለሙያ
#ዘገባው፡-አማራ_ክልል_ማረ/ቤት_ኮሚሽን_ህ/ግንኙነት
🔗 እኛን ይከተሉ / Follow Us:
📘 page: https://www.facebook.com/share/1DACNhDHHR/
🎵 TikTok Account: https://www.tiktok.com/.prison.office.com
✈️ Telegram Channel: https://t.me/AmharaPrisonOffice_12
▶️ YouTube Channel: https://youtube.com/

ወንጀል ያልፈፀሙ ህፃናትን ከአዋቂ ወንጀለኛ ታራሚዎች ጋር ማስተማር የስነ-ልቦና ጉዳት  ያስከትላል ።ኮ/ር ሙሉ አታጓደው ደብረ -ማርቆስ :- መስከረም 28/2019 ዓ/ም በምስራቅ ጎጃም ዞን...
08/10/2026

ወንጀል ያልፈፀሙ ህፃናትን ከአዋቂ ወንጀለኛ ታራሚዎች ጋር ማስተማር የስነ-ልቦና ጉዳት ያስከትላል ።
ኮ/ር ሙሉ አታጓደው

ደብረ -ማርቆስ :- መስከረም 28/2019 ዓ/ም

በምስራቅ ጎጃም ዞን ማረሚያ ቤት መምሪያ ከወላጆቻቸው ጋር በማረሚያ ቤት ውስጥ የሚገኙ ህፃናት ከማረሚያ ቤት ውጭ ባለ ዘመናዊ ትምህርት ቤት ከእድሜ እኩዮቻቸው ጋር እንዲማሩ መደረጉ ተገለፀ።

በምስራቅ ጎጃም ዞን ማረሚያ ቤት መምሪያ በደብረ ማርቆስ ማረሚያ ቤት የህፃናት ፣ወጣት ጥፋተኞች እና ሴት ታራሚዎች እንክብካቤ ባለሙያ የሆኑት ኮማንደር ሙሉ አታጓደው እንደገለፁት ከወላጆቻቸው ጋር በህግ ጥላ ስር የማገኙ ህፃናትን በማረሚያ ቤቱ ውስጥ ከሚገኘው ትምህርት ቤት ወንጀል ያልፈፀሙ ህፃናትን ወንጀል ከፈፀሙ አዋቂ የህግ ታራሚዎች ጋር ማስተማር ለህፃናቱ ከፍተኛ የሆነ የስነ-ልቦና ጫና የሚያሳድርና የሚፈጥር መሆኑን መምሪያው በመረዳት ህፃናቱ ከማረሚያ ቤት ውጭ ከሚገኝ ዘመናዊ ትምህርት ቤት ከእድሜ እኩዮቻቸው ጋር እንዲማሩ ለማድረግ ታምኖበት የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ፈቅዶ እየተማሩ መሆኑን ገልፀዋል።

ኮማንደሯ አክለውም የመምሪያው አመራሮች ለህፃናቶች የቀጣይ ህይወታቸው ብሩ ተስፋ በማሰብና ሞራላቸውን ለመጠበቅ ከውጭ በነፃነት ትምህርት እንዲማሩ በቁርጠኝነት በመወሰን ይህንን እድል በማመቻቸቱ ለህፃናቶቹ ትልቅ እድል አለው ብለዋል ።

በመጨረሻም ለህፃናቱ የነፃ ትምህርት እድል ለፈቀደው ኪዳነ-ምህረት አካዳሚ ፣ ለህፃናቱ የትምህርት ቁሳቁስ እና ዩኒፎርም ድጋፍ ላደረጉት የደብረ ማርቆስ እና የመንቆረር ክፍለ ከተማ ሴቶች እና ህፃናት መስሪያ ቤት ተቋማት ለተደረገላቸው ድጋፍና እገዛ በማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ስም ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።

ምንጭ :- የምስራቅ ጎጃም ዞን ማረሚያ ቤት ህዝብ ግንኙነት
ዘገባው 🖊 የአማራ ክልል ማረ/ቤት ህ/ግንኙነት
ለበለጠ መረጃ
​🔗 እኛን ይከተሉ / Follow Us:
​📘 page: https://www.facebook.com/share/1DACNhDHHR/
​🎵 TikTok Account: https://www.tiktok.com/.prison.office.com
​✈️ Telegram Channel: https://t.me/AmharaPrisonOffice_12
​▶️ YouTube Channel: https://youtube.com/

03/10/2026

Address

Bahir Dar
6000

Telephone

+251582202608

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ANRS Prison Commission posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share