Southwest Ethiopia Police Commission

Call Directions Website

Southwest Ethiopia Police Commission “በጀግንነት መጠበቅ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል!!”
(2)

ከአድማ ብተና እና ከቪ አይ ፒ ሻለቃዎች ተሸላሚዎች በፎቶ
02/11/2026

ከአድማ ብተና እና ከቪ አይ ፒ ሻለቃዎች ተሸላሚዎች በፎቶ

ዋና ኢንስፔክተር በዛብህ በላይነህ ልዩ ተሸላሚ በፎቶ
02/11/2026

ዋና ኢንስፔክተር በዛብህ በላይነህ ልዩ ተሸላሚ በፎቶ

የካፋ ዞን ፖሊስ መምሪያ፣ቤንች ሸኮ  ዞን ፖሊስ መምሪያ እና ሸካ ዞን ፖሊስ መምሪያዎች የዋንጫ ተሸላሚዎች በፎቶ።
02/11/2026

የካፋ ዞን ፖሊስ መምሪያ፣ቤንች ሸኮ ዞን ፖሊስ መምሪያ እና ሸካ ዞን ፖሊስ መምሪያዎች የዋንጫ ተሸላሚዎች በፎቶ።

የከፍተኛ ማዕረግ ተሸላሚዎች በፎቶ
02/11/2026

የከፍተኛ ማዕረግ ተሸላሚዎች በፎቶ

ከረዳት ሳጅን  እስከ ዋናሳጅን ተሸላሚዎች በፎቶ
02/11/2026

ከረዳት ሳጅን እስከ ዋናሳጅን ተሸላሚዎች በፎቶ

የተለያዪ አስተዋፆ ላደረጉ አመራሮች የሰርተፍኬት ተሸላሚዎች በፎቶ
02/11/2026

የተለያዪ አስተዋፆ ላደረጉ አመራሮች የሰርተፍኬት ተሸላሚዎች በፎቶ

02/11/2026
02/11/2026
ተግባራትን የፖሊስን ክብር በሚያስጠብቅ መንገድ ማከናወን እንደሚገባ የክልሉ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አንድነት አሸናፊ አሳሰቡሁሉንም ተግባራት የፖሊስን ክብር በሚያስጠብቅ መንገድ ማከናወ...
02/11/2026

ተግባራትን የፖሊስን ክብር በሚያስጠብቅ መንገድ ማከናወን እንደሚገባ የክልሉ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አንድነት አሸናፊ አሳሰቡ

ሁሉንም ተግባራት የፖሊስን ክብር በሚያስጠብቅ መንገድ ማከናወን እንደሚገባ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አንድነት አሸናፊ ተናግረዋል።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የ2019 በጀት ዓመት 2ኛ ዙር የ100 ቀናት እቅድ ላይ ውይይት እየተደረገ ነው።

የመድረኩን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ካሣ በሁሉም ዘርፎች እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎች ይገመገማሉ ብለዋል።

የፖሊስ ሪፎርምን ተግባራዊ ለማድረግ በተዘጋጁ ሰነዶች ላይ ውይይት እንደሚደረግ ገልጸዋል።

የክልሉ ፖሊሽ ፋውንዴሽን እንደሚቋቋምና እስካሁን የነበሩ ችግሮች ተቀርፈው ወደ ስራ እንደሚገባ አስታውቀዋል።

የፖሊስ ሠራዊት አመራሮችና አባላት ለሀገራዊ ተልዕክዎች ዝግጁ በመሆን ባለፈው ዓመት የተከናወነው 7ተኛ ጠቅላላ ምርጫ በሠላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ ማድረጋቸውን አንስተዋል።

በዚህ መድረክ በ2018 በጀት ዓመት የላቀ የሥራ ውጤት ላስመዘገቡ የፖሊስ ሠራዊት አመራሮችና አባላት እውቅና እና ሽልማት እንደሚበረከት ኮሚሽነር ዶክተር ካሣ ተናግረዋል።

ለክልሉ ሠላም መከበር ዋጋ ለከፈሉ አካላት እውቅና መስጠት ለተሻለ ስራ እንደሚያነሳሳ ገልጸው፤ እውቅናው የማዕረግ እድገትን፣ ሽልማትን እና የእርከን ደረጃ እድገትን ያካትታል ብለዋል።

የክልሉ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አንድነት አሸናፊ በበኩላቸው፤ ባለፉት አምስት ዓመታት በተሰሩ ስራዎች ሰላማዊና ለሁሉም ዘርፍ ስራዎች ምቹ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል።

ለዚህ ውጤታማነት ክልሉ ያበቁ የፖሊስ ሠራዊት አባላትንና አመራሮችን አመስግነዋል።

እንደ ሀገርም እንደ ክልልም በርካታ ህዝባዊ ኹነቶች በሰላማዊ መንገድ እንዲከናወኑ በማድረግና የፀጥታ ችግሮችን በመፍታት ፖሊስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከቱን ተናግረዋል።

የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ አካላት እውቅና መስጠትና ክፍተቶችንም ማረም ይገባል ሲሉ ተደምጠዋል።

ጥቃቅን ወንጀሎች እና ህዝብ ላይ ስጋት የሚፈጥሩ አካላት እንዳሉ ታውቆ ማስተካከያ እንዲደረግ አሳስበው፤ በትራፊክ ቁጥጥር ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮች መፈታት እንዳለባቸው አመልክተዋል።

ህገ-ወጥ ንግድ፣ ኮንትሮባንድና የጦር መሣሪያ ዝውውር ላይ በተደረጉ የቁጥጥር ስራዎች ውጤት ቢመዘገብም ተጨማሪ ስራዎችን ማከናወን ይገባል ነው ያሉት።

በተለይም በጦር መሣሪያና በነዳጅ ዝውውር ላይ በሙያ ሥነ-ምግባር መሠረት መስራት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።

የፖሊስን ክብር በሚያስጠብቅ መንገድ መንቀሳቀስና ጠንካራ ስራ መስራት እንደሚገባ ያሳሰቡት አቶ አንድነት፤ የስልጠና አሰጣጥን ማጠናከርና የአቅም ግንባታ ተግባራትን ለማከናወን እንደሚሰራ ተናግረዋል።

አዳዲስና ብቁ ዜጎች ወደ ፖሊስ ተቋም እንዲቀላቀሉ ማድረግና የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማሻሻል እንደሚያስፈልግ ነው የገለጹት።

በመድረኩ የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር የህግና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች አማካሪ አቶ ዳግም ዳንኤል፣ የኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች፣ የዞኞችና የወረዳዎች ፖሊስ አዛዦች እንዲሁም አመራሮች ተገኝተዋል። bonga fm

Address

ሸታ
Bonga

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Southwest Ethiopia Police Commission posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category