Dire Dawa Administration Health Bureau

Call Directions

Dire Dawa Administration Health Bureau Government Organization

🏆  ዋንጫውን እናነሳዋለን🏆ነገ ዕሁድ/  22/02/2019 ዓ.ም ከረፋዱ 3:00 በሳቢያን እግር ኳስ ሜዳ የጤና እግር ኳስ ቡድናችን ከወጋገን ባንክ የጤና እግር ኳስ ቡድን ጋር የዋንጫ ጨዋታ...
31/10/2026

🏆 ዋንጫውን እናነሳዋለን🏆

ነገ ዕሁድ/ 22/02/2019 ዓ.ም ከረፋዱ 3:00 በሳቢያን እግር ኳስ ሜዳ የጤና እግር ኳስ ቡድናችን ከወጋገን ባንክ የጤና እግር ኳስ ቡድን ጋር የዋንጫ ጨዋታ ያደርጋል በመሆኑም የቢሮ፣ የተቋማት አመራሮችና ሠራተኞች እንዲሁም የቡድናችን ደጋፊዎች በስፍራው በሰዓቱ በመገኘት ቡድናችንን እንድንደግፍ ጥሪ እናቀርባለን።
ድል ለቡድናችን
ጤና ይችላል የዋንጫ ይበላል
የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኮሙዩኒኬሽን
21/02/2019 ዓ.ም

የድሬዳዋ ጤና ቢሮ የወባ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ሥራዎች አፈፃፀም ላይ ግምገማ አካሄደ።የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ በወባ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ሥራዎች ዙሪያ በተለይም በ Case a...
30/10/2026

የድሬዳዋ ጤና ቢሮ የወባ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ሥራዎች አፈፃፀም ላይ ግምገማ አካሄደ።

የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ በወባ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ሥራዎች ዙሪያ በተለይም በ Case and Foci Investigation፣ በFocal Test and Treat (FTAT) እንዲሁም የወባ በሽታ መረጃ ጥራት ላይ ያተኮረ የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ኬዝ ቲም የግምገማ መድረክ አካሂዷል።

በመድረኩ የወባ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እስካሁን የተከናወኑ አበይት ተግባራትና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች በጥልቀት የተገመገሙ ሲሆን፣ በቀጣይ የተሻለና ውጤታማ ሥራ ለማከናወን የሚያስችሉ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።

በውይይቱ ላይ እንደተገለጸው፤ Focal Test and Treat (FTAT) በወባ በሽታ የተያዘ ግለሰብ (Index case) በአንድ የጤና ተቋም ወይም ማኅበረሰብ ውስጥ ሲገኝ፣ በግለሰቡ መኖሪያ ቤትና በአቅራቢያው በሚገኙ ጎረቤቶች ዙሪያ በ70 ሜትር ሬዲየስ ውስጥ ፈጣን የወባ ምርመራ (RDT) ማካሄድ ወሳኝ መሆኑ ተነስቷል።

በዚህም በሽታው የተገኘባቸውን ወዲያውኑ በማከም፣ የክትትል ሥራዎችን በማድረግ እንዲሁም ምልክት ሳይታይባቸው በሽታውን የሚያስተላልፉ ሰዎችን (Asymptomatic reservoirs) በመለየት ወባን ከአንድ አካባቢ ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት ትልቅ ድርሻ እንዳለው አፅንኦት ተሰጥቶበታል።

በተጨማሪም የወባ ስርጭትን በዘላቂነት ለመቀነስ የማኅበረሰቡን ንቅናቄ ማጠናከር፣ በየደረጃው ያሉ ባለድርሻ አካላትንና የባለሙያዎችን ቅንጅት ማሳደግ፣ ለትንኝ መራቢያ ምቹ የሆኑ ያቆሩ ውሃዎችን የማፋሰስና የማዳረቅ ሥራዎችን ማከናወን እንዲሁም የግልና የአካባቢ ንፅህናን መጠበቅ በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶባቸው የሚሠሩ ዋና ዋና ጉዳዮች መሆናቸው ተመላክቷል።

በመድረኩ ሌላው ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ የወባ መረጃ ጥራት (Data Quality) ሲሆን፤ የወባ በሽታ ስርጭትንና የወረርሽኝ አዝማሚያዎችን በትክክል ለመከታተል፣ የሕክምና ግብዓቶች ፍላጎትን አስቀድሞ ለመተንበይ እና ውሳኔዎችን በጥናት ላይ ተመሠረተ አስተማማኝ መረጃ ለመወሰን ለነገ የሚባል ሥራ አለመሆኑ የተገለፀ ሲሆን የጤና ተቋማት ኃላፊዎችና የHIT ባለሙያዎች መረጃውን ወደ DHIS2 መረጃ ቋት ከመላካቸው በፊት ትክክለኛነቱንና ወቅታዊነቱን ጠብቆ እንዲዘጋጅ ጥብቅ አቅጣጫ ተሰጥቷል።

በዚህ የግምገማ መድረክ ላይ የጤና ኤክስቴንሽን ሱፐርቫይዘሮች፣ የHIT ባለሙያዎች፣ የአስተዳደሩ ጤና ተቋማት የማህበረሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር (PHEM) ባለሙያዎች እና ከቢሮው የተውጣጡ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኮሙዩኒኬሽን
20/02/2019 ዓ.ም

የአፍላ ወጣቶችና የወጣቶችን ጤናና ደህንነት ለማረጋገጥ ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተገለጸ።7ኛው ብሔራዊ የአፍላ ወጣቶችና የወጣቶች ጤና ጉባኤ “የተለያዩ ነባራ...
30/10/2026

የአፍላ ወጣቶችና የወጣቶችን ጤናና ደህንነት ለማረጋገጥ ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተገለጸ።

7ኛው ብሔራዊ የአፍላ ወጣቶችና የወጣቶች ጤና ጉባኤ “የተለያዩ ነባራዊ ሁኔታዎች ለጋራ የወጣቶች ራዕይ” በሚል መሪ ቃል በድሬዳዋ ከተማ በደማቅ ሁኔታ ተካሂዷል።

በጉባኤው የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዩሱፍ መሐመድ የወጣቶችን ጤና ለማሻሻል የተለያዩ የባለድርሻ አካላት ቅንጅት ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው ወጣቶች የነገ መሪዎች ብቻ ሳይሆኑ የዛሬም ሀብት በመሆናቸው ጤናቸው መጠበቅና ተገቢውን እንክብካቤ ማግኘት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

ያለዕድሜ ጋብቻና እርግዝና፤ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ፤ በጾታ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎች፤ የአእምሮ ጤና ችግሮች፤ የምግብ እጥረት፤ የትራፊክ አደጋና የጾታዊ ጥቃት የወጣቶችን ጤና ከሚፈታተኑ ችግሮች መካከል እንደሚጠቀሱ ጠቁመዋል።

ዶ/ር ዩሱፍ አያይዘውም ወጣቶች ላይ የሚከሰቱ ችግሮችን ለመፍታትም የጤና ሚኒስቴር፤ የከተማ አስተዳደሮች፤ የጤና ተቋማት፤ የሃይማኖት አባቶችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መሥራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ወጣቶችም ችግሮቻቸውን በመለየት፤ በውይይት በመሳተፍና ቤተሰብና ማኅበረሰቡን በማንቀሳቀስ ለጤናቸው ጥበቃ የራሳቸውን ድርሻ እንዲወጡ ዶ/ር ዩሱፍ ጥሪ አቅርበዋል።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስቴር ድኤታ አማካሪ ፕሮፌሰር ስለሺ ጋሩማ በበኩላቸው የወጣቶችን ጤና ማሻሻል ሀገራቸውን የሚወዱ፤ መልካም ሥነ ምግባር ያላቸው፤ አምራችና የሀገራቸውን ኃላፊነት መረከብ የሚችሉ ዜጎችን ለመገንባት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

ወጣቶች የተሻለ የሰላም ሁኔታ፤ ጥራት ያለው ትምህርት፤ በቂ የጤና አገልግሎትና የተሻለ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ እንዲያገኙ ሁሉም አካላት ምቹ ሁኔታ በመፍጠር መብታቸውን ሊደግፉና የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ሊፈቱ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

የብሔራዊ የወጣቶች ጤና ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ዶክተር ገመቹ አቡ ወጣቶች የጋራ ራዕያቸውን ለማሳካት በተለያዩ ዘርፎች የሚንቀሳቀሱ ወጣቶች በቅንጅት፤ በቁርጠኝነትና በጽናት መሥራት እንዳለባቸው ገልፀዋል።

በመድረኩ የፌዴራል የትምህርት ሚኒስቴር ተወካይ አቶ ብርሃኑ ተስፋዬ በበኩላቸው የጾታና የሥነ-ተዋልዶ ጤና ትምህርትን በትምህርት ሥርዓቱ ውስጥ በማካተትና በተግባር በመተግበር የወጣቶችን ዕውቀትና ግንዛቤ ለማሳደግ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በቅንጅት መሥራት እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል።

በመድረኩ የእንድስትሪ ልማት ኮርፕሬሽን እና የዩኒሴፍ ተወካዬች የአፍላ ወጣቶችና ወጣቶች ጤና ለማስጠበቅ የበኩላቸውን እንደሚሠሩ ቃል ገብተዋል።

በመድረኩ ለአፍላ ወጣቶችና ወጣቶች ጤና እንዲሁም የጤና ካውንስል ጉባኤ እንዲሳካ አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላት የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዩሱፍ ሠኢድ ስጦታ ተበርክተውላቸዋል።

ለሁለት ቀናት የቆየው 7ኛው ብሔራዊ የአፍላ ወጣቶችና የወጣቶች ጤና ጉባኤ በፓናል ውይይት ተጠናቋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኮሙዩኒኬሽን
20/02/2019 ዓ.ም

7ተኛው  የኢትዮጵያ አፍላ ወጣቶችና ወጣቶች የጤና ካውንስል ጉባኤ በአስተዳደሩ በተለያዩ ኩነቶች እየተከበረ ይገኛል።የጤና ሚኒስቴር ከድሬደዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር የተለያዩ  '...
29/10/2026

7ተኛው የኢትዮጵያ አፍላ ወጣቶችና ወጣቶች የጤና ካውንስል ጉባኤ በአስተዳደሩ በተለያዩ ኩነቶች እየተከበረ ይገኛል።

የጤና ሚኒስቴር ከድሬደዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር የተለያዩ ''ነባራዊ ሁኔታዎች ለጋራ ወጣቶች ራእይ" በሚል መሪ ቃል 7ተኛውን የኢትዮጵያ አፍላ ወጣቶችና ወጣቶች የጤና ካውንስል ጉባኤ ተጀመረ።

​በጉባኤው መክፈቻ ላይ የድሬደዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዩሱፍ ሠኢድ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን በንግግራቸው እንኳን ወደ ድሬደዋ ትንሿ ኢትዮጵያ ሰላም መጣችሁ በማለት እንግዶቹ በቆይታቸው መልካም ጊዜ እንደሚያሳልፉ ገለፃ አድርገዋል።

​አቶ ዩሱፍ አያይዘውም የጉባኤውን ቀን ጠቀሜታ በማንሳት ወጣቶች በጤናው ዘርፍ ያላቸውን ተሳትፎ ማጠናከር እና አፍላ ወጣቶችን ያካተተ ጤናማ ትውልድ መገንባት ለነገ የሚባል የማይተላለፍ አደራ መሆኑን በመግለጽ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ጉባኤው በአስተዳደሩ ለ2 ቀናት የሚቆይ ሲሆን በመጀመሪያ ቀን ውሎው በአስተዳደሩ በሚገኘው እንድስትሪ ልማት ኮርፕሬሽን ውስጥ የሚገኘው ክሊኒክ ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን የመልካ ጤና ጣቢያ የአፍላ ወጣቶችና ወጣቶች ጤና ላይ የሚሠሩ ሥራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ማጠቃለያ ላይ ተሳታፊዎች እንደተናገሩት በጉብኝታቸው ደስተኛ መሆናቸውን ጠቅሰው የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ስር የሚገኘው የመልካ ጤና ጣቢያ እየሠጣቸው የሚገኙ የጤና አገልግሎቶች ለሌሎች ክልሎች ልምድ መሆን የሚችል መሆኑን የገለፁ በመግለፅ ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል ምስጋና አቅርበዋል።

በመድረኩ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስቴር ድኤታ አማካሪ ፕሮፌሰር ሰለሺ ጋሩማን ጨምሮ ከተለያዩ ክልል የተወጣጡ ወጣቶች ጉባኤውን ለመታደም ድሬደዋ ተገኝተዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኮሙዩኒኬሽን
19/02/2019 ዓ.ም

የድሬዳዋ አስተዳደር የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን የ2019 በጀት ዓመት የአባላት ምዝገባ እና መዋጮ ንቅናቄ ተካሄደ።​የድሬዳዋ አስተዳደር የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን የ2019 ዓ.ም...
28/10/2026

የድሬዳዋ አስተዳደር የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን የ2019 በጀት ዓመት የአባላት ምዝገባ እና መዋጮ ንቅናቄ ተካሄደ።

​የድሬዳዋ አስተዳደር የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን የ2019 ዓ.ም የአባላት ምዝገባና መዋጮ የንቅናቄ መድረክ መደጋገፍ ባህላችን ጤና መድህን ዋስትናችን በሚል መሪ ቃል ተካሂዷል።

​በንቅናቄ መድረኩ ላይ የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዩሱፍ መሀመድ፤ በብልጽግና ፓርቲ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደረጀ ፀጋዬ፤ የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዩሱፍ ሰኢድ፤ እንዲሁም የአስተዳደሩ ከንቲባ የጤናው ዘርፍ አማካሪ ዶ/ር ጽጌረዳ ክፍሌ እና የኢትዮጵያ ጤና መድህን ምክትል ዳይሬክተር ወ/ሮ ላምሮት አንዷለም ተገኝተዋል። በተጨማሪም በንቅናቄ መድረኩ ላይ የጤና ተቋም ኃላፊዎች እና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል።

በንቅናቄ መድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዩሱፍ መሀመድ እንደተናገሩት የጤና መድህን ስርዓት የአስተዳደራችን ነዋሪ የጤና አገልግሎት ሽፋንና አገልግሎት ተጠቃሚነት ማሣደጉን ጠቁመው አሁን ያለንበትን የ92 በመቶ ሽፋን በማሣደግ 100 ፕርሰንት ሽፋን ለማድረስ እንደሚሠራ በመጥቀስ ከዚህ ጎን ለጎንም የህክምና አገልግሎት ጥራት ማሳደግ ላይ በትኩረት ይሠራል ብለዋል።

በንቅናቄ መድረኩ ላይ የሥራ አቅጣጫ የሰጡት የብልፅግና ፖርቲ ድሬደዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደረጀ ፀጋዬ በበኩላቸው የ2019 ዓ.ም የአስተዳደሩ የማህበረሰብ ዓቀፍ የጤና መድህን የአባላት ምዝገባና የመዋጮ ንቅናቄ ሲከናወን የጠራ እቅድ ይዞ በመነሣት የተለያዩ የአሠራር ስልቶችን በመንደፍና በመከተል መሆን እንደሚገባው ጠቁመው ለዚህ ደሞ በየደረጃው ያለው አመራር ቁርጠኝነት እንደሚፈልግ ገልፀዋል።
አቶ ደረጀ አያይዘውም የጤና መድህኑን አስፈላጊነት ላይ የተጠናከረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በቅንጅት ሊሠሩ እንደሚገባ በመጠቆም የሚሠሩ ስራዎችን ፖርቲው ክትትልና ግምገማ እንደሚያካሂድ አፅንኦት ሠጥተዋል።

በመድረኩ የኢትዮጵያ ጤና መድህን አገልግሎት በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተሠሩ የሚገኙ ስራዎችና በድጋፉዊ ክትትል የተሠሩ የክፍያ ጥያቄዎች ምርመራ ሪፖርት(Claim Audit Report) ቀርበው ሠፊ ውይይት ተካሂዶባቸዋል።

በውይይቱም በድጋፋዊ ክትትሉ የተመላከቱ ክፍተቶችን ለመድፈን ሀሉም የጤና ተቋማት ጠንካራ አሠራር መዘርጋት እንደሚገባቸውና ህብረተሠቡ የተሻለ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት እንዲያገኝ በትብብር መሥራት እንደሚገባ ተመላክቷል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኮሙዩኒኬሽን
18/02/2019 ዓ.ም

የአስተዳደሩ  የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አዲስ የቦርድ አባላት ከኢትዮጵያ ጤና መድህን አገልግሎት ከመጡ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ትውውቅ አድርገዋል።በትውውቅ መድረኩ ላይ የአስተዳደሩ ከንቲ...
28/10/2026

የአስተዳደሩ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አዲስ የቦርድ አባላት ከኢትዮጵያ ጤና መድህን አገልግሎት ከመጡ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ትውውቅ አድርገዋል።

በትውውቅ መድረኩ ላይ የአስተዳደሩ ከንቲባ አብዱላሂ አደን፤ ምክትል ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር እና የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዩሱፍ መሀመድን ጨምሮ አዲሱ የአስተዳደሩ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን የቦርድ አባላት የተገኙ ሲሆን የኢትዮጵያ ጤና መድህን አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ወ/ሮ ላምሮት አንዷለም ከተመራው ከፍተኛ አመራሮች ጋር ትውውቅና ውይይት ተደርጓል።

በትውውቅ መረሃ-ግብሩ ላይ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አጠቃላይ ሀገራዊ ሥራዎችና በአስተዳደሩ የተከናወኑ ዝርዝር ሥራዎች ቀርበው ውይይት ተካሂዶበታል።

በውይይቱ ላይ የአስተዳደሩ ከንቲባ አብዱላሂ አደን እንደተናገሩት በአስተዳደር ደረጃ የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን የማህበረሰባችን የጤና ዋስትና በመሆኑ እስካሁን የተሠሩ ሥራዎችን በማጠናከር የጤና መድህኑን ጠንካራ መሠረት እንዲይዝ ጠንካራ የአሠራር ሂደቶችን መተግበር ይገባል ብለዋል።

ከንቲባ አብዱላሂ አያይዘውም የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ያለውን ጠቀሜታ ግንዛቤ የመፍጠር ሥራው ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ በመጠቆም በተለይ በአስተዳደር ደረጃ በትንኝ ንክሻ የሚተላለፉ በሽታዎች በህክምና ተቋማት ላይ የሚፈጥሩት ጫና ከፍተኛ በመሆኑ የተጠናከረ ድጋፍ ያሻል ብለዋል።

በትውውቅ መድረኩ ላይ ሃሳባቸውን የሰጡት የኢትዮጵያ ጤና መድህን አገልግሎት ምክትል ዳሪክተር ወ/ሮ ላምሮት አንዷለም በበኩላቸው የድሬደዋ አስተዳደር የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ላይ እየሠራቸው ያሉ ሥራዎች አመርቂ መሆናቸውን ጠቁመው ጠንካራ የሆነ ዘላቂ የፉይናንስ አቅም ለመገንባት በርብርብ መሥራት ይገባል ብለዋል።

በአስተዳደሩ በአሁኑ ወቅት 59,764 አባወራዎች የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ተጠቃሚ መሆናቸው በመድረኩ ተመላክቷል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኮሙዩኒኬሼን
18/02/2019 ዓ.ም

በድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ  የቦረን ጤና ጣቢያ የ2019 ዓ.ም  የ1ኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ገመገመ።በዚ የግምገማ መድረክ የጤና ጣቢያውን በ2019 ዓ.ም በ1ኛ ሩብ ዓመት  ለመተግበ...
25/10/2026

በድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ የቦረን ጤና ጣቢያ የ2019 ዓ.ም የ1ኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ገመገመ።

በዚ የግምገማ መድረክ የጤና ጣቢያውን በ2019 ዓ.ም በ1ኛ ሩብ ዓመት ለመተግበር የታቀዱ ስራዎች አፈፃፀም ቀርቦ ሰፊ ውይይት የተደረገበት ሲሆን በመጀመርያ ሩብ አመት የተመዘገቡ ውጤቶች ማስቀጠል እንደሚገባና በአንፃሩ ደግሞ በወረርሽኝ መልክ የሚነሱ እንደደንጊና ወባ የመሳሰሉ በሽታዎችን ከባለድርሻ አካላት አስቀድሞ መከላከል በሚቻልበት ስራዎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶባቸው መስራት እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።

በተጨማሪም ከመረጃ አያያዝ ፣በእናቶችና ሕፃናት ጤና፣ በሥነ-ምግብ፣ ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎችና በሌሎች መሠረታዊ የጤና አገልግሎቶች ላይ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች አበረታች ቢሆኑም አሁንም ህብረተሰቡ ያሳተፈ ስራ መስራት ይሻል ተብሏል።
በሩብ ዓመቱ የሥራ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ላይ የአሰሊሶ ክላስተር ሥራ አስፈፃሚ አቶ አብዲ አብደላ፣ የወረዳ 2 አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ይልቃል አስረስ እና የወረዳ 2 የማህበራዊ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ሰላም ፍቅሬ የተቋሙ ማናጅመንት አባላትና ሰራተኞች እንዲሁም የማህበረሰብ ተወካዮች ተገኝቷል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኮሙዩኒኬሽን
15/02/2019 ዓ.ም

25/10/2026

⚽️መልካም የድል ዜና⚽️
የጤና እግር ኳስ ቡድናችን ለዋንጫ ለማለፍ ከአቢሲኒያ ባንክ የእግር ኳስ የጤና ቡድን ጋር ባደረገው ጨዋታ አሸናፊ ሆኖል እንኳን ደስ አላችሁ።

ቪዲዮ ከአሹ ቲክቶክ 🙏

በድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ የድልጮራ ሪፈራል ሆስፒታል በሳቢት ኢንጅነሪንግ ሙሉ ወጪ የታደሱ የአእምሮ ህክምና መስጫ ክፍሎች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆኑ።በድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ...
24/10/2026

በድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ የድልጮራ ሪፈራል ሆስፒታል በሳቢት ኢንጅነሪንግ ሙሉ ወጪ የታደሱ የአእምሮ ህክምና መስጫ ክፍሎች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆኑ።

በድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዩሱፍ ሰዒድ የአእምሮ ህክምና መስጫውን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት ያደረጉት ሲሆን ባስተላለፉት መልእክትም የድልጮራ ሪፈራል ሆስፒታል የአእምሮ ህክምና መስጫ ክፍሎች በሳቢት ኢንጅነሪንግ ሙሉ ወጪ ታድሰው መመረቃቸውና ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸው፣ በአስተዳደሩ ያለውን የአእምሮ ጤና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት ለማሻሻል ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል።

ምክትል ቢሮ ኃላፊው አክለውም የግል ባለሀብቶችና ድርጅቶች በጤናው ዘርፍ በዚህ መልኩ መሳተፋቸው ማህበራዊ ኃላፊነትን ከመወጣት ባለፈ፣ በሆስፒታሉ የሚስተዋሉ የሆስፒታል አልጋዎችና የክፍሎች እጥረትን በመቅረፍ ለታካሚዎች ምቹና የተሻለ የህክምና አካባቢ ለመፍጠር ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑ ገልፀው ሌሎች ባለሃብቶችም የጤናውን ዘርፍ እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል።

የድል ጮራ ሪፈራል ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር በረከት ገብሩ በበኩላቸው በሆስፒታሉ የአእምሮ ህክምና መስጫ ቀደም ሲል ይስተዋሉ የነበሩ በርካታ ችግሮችን የቀረፈና ህክምናውን የሚሰጡ ባለሞያዎችና ታካሚዎችን እንዲሁም ለማህበረሰቡም ዘርፈ-ብዙ ጥቅሞችን አስገኝቷል ያሉ ሲሆን ለሳቢት ኢንጅነሪንግ በሆስፒታሉ ስም አመስግነዋል።

ይህ በጎ ተግባር ላከናወነ ድርጅት ሳቢት ኢንጅነሪንግ ከድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዩሱፍ ሰዒድ የምስጋና ሰርተፌኬት ተበርክቶላቸዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኮሙዩኒኬሽን
14/02/2019 ዓ.ም

በድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ሜዳ ላይ ከመፀዳዳት ነፃ ቀበሌ ለመፍጠረ ያለመ የንቅናቄ መድረክ ተካሄደ።በአስተዳደሩ ጤና ቢሮ የሃይጅንና አካባቢ ጤና አጠባበቅ ክፍል አማካኝነት የገጠር ቀበሌዎ...
24/10/2026

በድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ሜዳ ላይ ከመፀዳዳት ነፃ ቀበሌ ለመፍጠረ ያለመ የንቅናቄ መድረክ ተካሄደ።

በአስተዳደሩ ጤና ቢሮ የሃይጅንና አካባቢ ጤና አጠባበቅ ክፍል አማካኝነት የገጠር ቀበሌዎችን ሜዳ ላይ ከመፀዳዳት ነፃ (Open Defecation Free - ODF) ለማድረግና የህብረተሰቡን የጤና እና የንጽህና አጠባበቅ ለማሻሻል ያለመ የንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል።

በንቅናቄ መድረኩ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዩሱፍ ሰዒድ እንደተናገሩት በተለያዩ ምክንያቶች ቀበሌዎችን ሙሉ በሙሉ ሜዳ ላይ ከመፀዳዳት ነፃ ያላደረጉ የቀበሌ አመራሮች፣የጤና ተቋማት ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት በቀጣይ ህብረተሰቡን በማነቃነቅ ንፁህ አካባቢ፣ ጤናማ ማህበረሰብ" ለመፍጠር የሚደረገውን ርብርብ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ አሳስበዋል።

በድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ የሃይጂንና አካባቢ አጠባበቅ ክፍል አስተባባሪ የሆኑት አቶ አጀበ ከቤ በበኩላቸው ይህንን ንቅናቄ ውጤታማ ማድረግ በማህበረሰቡ ውስጥ በንጽህና ጉድለት ምክንያት የሚከሰቱና ከአፍና ከዓይነ ምድር ንክኪ ጋር የተያያዙ ተላላፊ በሽታዎችን ለመቀነስ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው በመግለፅ በተጨማሪም የሽንት ቤት አጠቃቀምንና የእጅ መታጠብ ባህልን በማሳደግ የገጠር ቀበሌዎችን ለኑሮ ፅዱና ምቹ ያደርጋል ብለዋል።

የንቅናቄው ተሳታፊዎች በበኩላቸው ቀበሌያቸውን ሜዳ ላይ ከመፀዳዳት ነፃ ለማድረግ በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ በመድረኩ ቃል ገብቷል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኮሙዩኒኬሽን
14/02/2019 ዓ.ም

Address

Dire Dawa

Telephone

+251251112330

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dire Dawa Administration Health Bureau posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share