Gofa Zone Government Communication Affairs Department

Call Directions Website Contact the organization

Gofa Zone Government Communication Affairs Department ይህ የጎፋ ዞን መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ትክክለኛ የፌስቡክ ገጽ ነው።
(1)

08/11/2026

ባለፉት 30 ቀናት የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚነት በተጨባጭ ሊያረጋግጡ የሚችሉ ተስፋ ሰጪ ተግባራት ተከናውነዋል" የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት

አመራሩ ለቀጣይ ተልዕኮዎች ራሱን ማዘጋጀት እንዳለበት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ በላይነህ ባህሩ ገለፁ።የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ በላይነህ ባህሩ እና የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤ...
08/11/2026

አመራሩ ለቀጣይ ተልዕኮዎች ራሱን ማዘጋጀት እንዳለበት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ በላይነህ ባህሩ ገለፁ።

የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ በላይነህ ባህሩ እና የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ጥላሁን ጌታቸው ለዞን አጠቃላይ አመራሮች በቀጣይ አቅጣጫዎችና ተደማሪ ተልዕኮዎች ዙሪያ የኦረቴሽን ሰጥተዋል።

በመድረኩ ከ100 ቀናት ዕቅድ ውስጥ የአንድ ወር የመንግስትና ፓርቲ ስራዎች አፈፃፀም ቀርቦ ግብረ-መልስ ተሰጥቷል።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ በላይነህ ባህሩ በውይይቱ እንደገለፁት ባለፉት 30 ቀናት አፈጻጸም የተገኙ ስኬቶችን በማስቀጠል ጉድለቶችን በማረም ምርጥ ተሞክሮዎችን ይበልጥ በማስፋት በቀጣይ ቀሪ የ70 ቀናት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መረባረብ እንደሚገባ ገልፀዋል።

አመራሩ የሚገጥሙትን ማነቆዎችና ችግሮችን በዕውቀት በመጋፈጥ በመፍጠር፣ በመፍጠን እና በመዝለል ችግሮችን በዘላቂነት መፍታት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበው "በቂ ምክንያቶቾ ውጤት አይሆኑም" ብለዋል።

የአስተሳሰብና የተግባር አንድነትን ለማምጣት ውጤታማ የህዝብና የባለድርሻ አካላት ግንኙነት ማጎልበት እንደሚገባም ተጠቁሟል።

ዋና አስተዳዳሪው አክለውም በየአካባቢው ያሉ እምቅ ፀጋዎችን በአግባቡ በመጠቀምና ሀብት በመፍጠር ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ቀዳሚ አጀንዳ ሊሆን ይገባልም ብለዋል።

የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ጥላሁን ጌታቸው እንደገለፁት አገልግሎት አሰጣጥ እና የህዝብ ቅሬታዎችን ህዝቡን ባሳተፈ መንገድ የማረም ጉዳይም በቀጣይ ቀሪ የ70 ቀናት ዕቅድ ውስጥ ልዩ ትኩረት ከሚሰጥባቸው ተግባራት መካከል ዋነኛዎቹ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

በጥንካሬ የተለዩ ተግባራትን አጠናክሮ መቀጠልና ክፍተቶችን በማረም በቀጣይ በታቀዱ የመንግስትና የፓርቲ ዕቅዶች ዙሪያ ልዩ ትኩረት በመስጠት መተግበር እንደሚገባ ኃላፊው አሳስበዋል።

በዋናነት የትምህርት፣ የመንገድ፣ የሰላምና ፀጥታ፣ በጤና፣ በገቢ፣ በግብርና፤ የስራ እድል ፈጠራ፣ የአገልግሎት አሰጣጥን እና ሌሎች አጠቃላይ ተግባራት በቀሪ 70 ቀናት የታቀዱ ተግባራትን በቁርጠኝነት ማሳካት እንደሚገባ በመድረኩ በአጽንኦት ተገልጿል።

በመጨረሻም ለቀጣይ 15 ቀናት ስልጠና ለሚገቡ አመራሮች ኦረንቴሽን ተሰጥቶ መድረኩ ተጠቃሏል።

በዞናችን የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ጉልበትን መሰረት ካደረገ የአስተራረስ ዘዴ በሂደት የቴክኖሎጂ ፈጣን ተለዋዋጭነት ታሳቢ ያደረገ የግብርናና የማኑፋክቸሪንግ ...
07/11/2026

በዞናችን የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል

ጉልበትን መሰረት ካደረገ የአስተራረስ ዘዴ በሂደት የቴክኖሎጂ ፈጣን ተለዋዋጭነት ታሳቢ ያደረገ የግብርናና የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ መሰረትን የመጣል፣ ቴክኖሎጂ እና ዕውቀት በማጣመር የአገልግሎት ዘርፍ ኢኮኖሚን የመገንባት፣ የቴክኖሎጂና የኢኖቬሽን ተወዳዳሪነትን የማሳደግ ስራዎች የመደመር መንግስት ትኩረት ከሚሰራባቸው ስራዎች መካከል ይገኙበታል፡፡

ለግብርና እድገት የተመቸ ታታሪ አርሶ አደር አና እምቅ ፀጋ ይዘን ከድህነት ለመላቀቅም ሆነ በኢንዱስትሪ ልማት የዳበረ ኢኮኖሚ ለመገንባት መነሻ መሰረቱ ግብርና እንደሆነ አያጠያይቅም።

በመሆኑም ግብርናችን በምንገኝበት አሁናዊ ሁኔታ የዞናችን ብሎም የክልላችን እድገት ብቻ ሳይሆን መፃኢ እድልም የሚወስን ጉዳይ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል።

የግብርና ልማት የህዝባችን የማደግ፣ የመልማትና የመለወጥ ማሻት የሚወስን በመሆኑ በዘርፉ ባሉ ችግሮችና መንስኤዎች ዙሪያ የጠራ መግባባት ፈጥሮ መሰረታዊ ለውጥ የሚያመጣ እንቅስቃሴ ማድረግ አንገብጋቢ ጉዳይ ሆኖ ይገኛል።

በእያንዳንዱ የአርሶ አደሩ ማሳ ላይ የምርት ጭማሪ ማምጣት ከተቻለ በእርግጥም መሰረታዊ ችግሮችን እንደሚቀርፍልን አያጠያይቅም።

ከሁሉ በፊት የምግብ ዋስትና ጥያቄን በአስተማማኝ ደረጃ ይመልሳል። የምግብ አቅርቦት ጉዳይ የየትኛውም ዜጋ አሳሳቢ ችግር እንደዳይሆን ይልቁንም ለኑሮ መሰረታዊ የሆነው የምግብ አቅርቦት አስተማማኝ ማድረግ ያስችላል።

ከዚህም አልፎ ከተመረተው ምርት ለሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪ በግብዓትነት በመጠቀም ኢንዱስትሪያችን በአስተማማኝ የጥሬ ዕቃ አቅርቦት የሚደገፍ ይሆናል።

የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት በአጭር ጊዜ ውስጥ በምግብ ዋስትና ራሳችንን እንደምንችል ጥሩ ማሳያ ነው።

በሌማት ትሩፋት በእንቁላል፣ በዶሮ፣ በወተት ሀብት ልማት፣ በአትክልትና ፍራፍሬ፣ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር እየታየ ያለው ለውጥ ከተረጂነትና ተረጂነት ከፈጠረብን መጥፎ አመለካከት ለመውጣት ተስፋ የሚጣልበት ነው።

በዋና ዋና ሰብሎች የታየው የክላስተር ልማት በምግብ ዋስትና ራስን ከመቻል፣ ከተረጅነት ወደ ምርታማነት የሚያሻግር እና የጀመርነውን የምግብ ሉዓላዊነት የማረጋገጥ ጉዞ እውን መሆን ማሳያ ነው።

አርሶ አደሩ ሁሉንም ዓይነት የመስኖ ውሃ አማራጮች ተጠቅሞ እንዲያለማ የዞኑ ግብርና መምሪያ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ተግባራዊ ለማድረግ አመራሮችና ባለሙያዎች ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ ላይ ናቸው።

በአጠቃላይ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በስፋት እየተሰራ ይገኛል። የግብርና መካናይዜሽን ለማስፋፋት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ነው። ከተበጣጠሰ ማሳ ለሜካናይዜሽን ምቹ ወደ ሆነው ክላስተር ማሳ እየተቀየረ ነው።

ከገባንበት የእርዳታ ጠባቂነት ማጥ ለመውጣት የምንችለው በራሳችን ጥረት እንጂ በሌላ ሀይል በሚደረግልን ድጋፍ ወይም ዳረጎት እንዳለሆነ ተገንዝበን ርብርብ ማድረግ ይኖርብናል።

የእርዳታ ጠባቂነት አመለካከትን አውልቆ ለመጣል ታሪክ ለመስራት ቁርጠኝነትና ትጋት ይጠበቅብናል። ይህንኑ አጠናክረን መቀጠል ከምንጠብቀው ግብ ያደርሰናል።

አቶ ጥላሁን ጌታቸው
የጎፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊና
የመንግስት ዋና ተጠሪና

ጥቅምት 28/2019 ዓ.ም

በራስ አቅም ላይ የተመሠረተ ጠንካራ የማኅበራዊ ዋስትና ሥርዓት በመገንባት፣ ተጋላጭ ዜጎችን በዘላቂነት በማቋቋምና ወደ አምራችነት በማሸጋገር ተረጂነትን ለመቀነስ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን የ...
07/11/2026

በራስ አቅም ላይ የተመሠረተ ጠንካራ የማኅበራዊ ዋስትና ሥርዓት በመገንባት፣ ተጋላጭ ዜጎችን በዘላቂነት በማቋቋምና ወደ አምራችነት በማሸጋገር ተረጂነትን ለመቀነስ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ በላይነህ ባህሩ ገልጸዋል።

የኢኮኖሚ ዕድገት ምንጮችን በማስፋት፣ ዘርፈ ብዙ የንግድና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎችን በመፍጠር፣ ኢኖቬሽንንና አምራች ኢንዱስትሪዎችን በመሳብ ለዞናዊና ለተቋማዊ ሽግግር ቁልፍ መሠረት እንዲሆኑ መሥራት እንደሚገባም አመልክተዋል።

ከተሞች የካፒታል ክምችት ዋነኛ ምንጭ፣ የአገልግሎት ዘርፍ ማፋጠኛ፣ የኢኖቬሽን ማዕከል፣ የሥራ ዕድል ፈጣሪና ለኢንቨስትመንት መሳቢያ የኢኮኖሚ ሞተሮች መሆናቸውን ጠቅሰዋል፣

የኮሪደር ልማትና የከተሞች ዳግም ግንባታ ፕሮጀክቶች በመዋቅራዊ መሠረታቸው እንዲሁም መሬት ላይ ባረጋገጡት ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጦች ረገድ ያላቸውን ፋይዳ አጉልተው አጠናክሮ ማስቀጠሉ አያጠያይቅም በማለት በሁሉም ማዕከል እንደሚሰራ አሳውቀዋል።

በዚህ መልኩ ዞናችንም በመደመር መንግሥት እሳቤ እየተመራ ከተሞችን ከነበሩበት የጉስቁልና ማዕከልነት በማውጣት ለነዋሪዎቻቸው ምቹ፣ ዘመናዊና ተወዳዳሪ የቢዝነስ ማዕከላት ለማድረግ በቆራጥነት መሥራት እንደሚገባም አሳስበዋል።

በሌላ በኩል ሙስናና ክራይ ሰብሳቢነትን ለመዋጋት በተለመደ ውግዘትና በወረቀት ላይ በሰፈሩ የቅጣት ማስፈራሪያ ብቻ መታገል በቂ እንዳልሆነ ጠቁመው፣ ያለምንም ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ቅድመ ሁኔታን ባለማስቀመጥ ሕግን በማስከበር ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ እሰራለን ያሉት አስተዳዳሪው በጸረ ሙስናና ሌብነት ያላቸው ወጥ አቋም አሳውቀዋል።

በተመሳሳይ በዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ በግብርና ሜካናይዜሽንና የፈጠራ ሥራዎችን በማስፋፋት ወጣቶችንና ሴቶችን በልማቱ በማቀናጀት፣ የግሉ ዘርፍ ከማኅበራዊ ኃላፊነት ባለፈ የኢኮኖሚው ዋነኛ ሞተርና መሪ እንዲሆን ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር እንደሚያስፈልግ ገልጸው ዕቅዶችን በየጊዜው በመከለስ እና እሴት በመጨመር የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት እንደሚሠራም አረጋግጠዋል።

የደን ጥበቃና አረንጓዴ ልማት የውበትና የመዝናኛ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፣ የዞናችን የማምረት አቅምና የሥራ ዕድል ፈጠራ በቀጥታ የሚወስኑ የማክሮ ኢኮኖሚ አንቀሳቃሾች መሆናቸውን በመጥቀስ፣ ለዘርፉ ሰፊ ትኩረት እንደተሰጠው አስረድተዋል።

አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርም ተራ የዛፍ ተከላ ዘመቻ ሳይሆን፣ ዞናችንን ወደ አረንጓዴና በአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ ለማሸጋገር የተነደፈ ለውጥ አምጪና ዘርፈ ብዙ መርሃ ግብር መሆኑን በመገንዘብ በተግባር መደጋገፍ እንደሚገባም ጠቁመዋል።

በዞናችን ህዝቦች ለዓመታት ጥያቄ የሆኑ በመንገድ እጦት የተዘጉ ቀበሌያት ማህበራዊ አገ/ት በቀላሉ እንዲያገኙ፣ ምርታቸውን እንዲያወጡ፣ የተዘጉ የመስኖ ቦዮች እንዲከፈቱ፣ አዳዲስ እንዲገነቡ፣ የተጓተቱ የግንባታ ፕሮጀክቶች እንዲጠናቀቁ ችግሮች ለይተን ወደ ትግበራ ገብተናል። በ100 ቀናት እቅዳችንም ተጨባጭ ውጤት ለማስመዝገብ እየሰራን እንገኛለን።

በዚህም መሠረት የጎፋ ዞን ሰላሟ የተጠበቀ፣ ሥርዓቷ የተስተካከለና ተቋማቷ ለሕግ የሚገዙባት ተምሳሌት የሆነ ዞን ለመገንባት በተሰጣቸው ኃላፊነትና አደራ መሠረት በጋራ እንደሚተጉ ገልጸዋል።

ዋና አስተዳዳሪው ሁሉም የዞኑ ተወላጆች በዞናዊ ጉዳዮች ላይ በእኩልነትና በንቃት መሳተፍ ለልማት ዘላቂነት መሠረት መሆኑን ጠቁመው፣ ሁሉንም አካታች ያደረገ የጋራ ሀሳብና ተሳትፎ ማጎልበት እንደሚገባ በተደጋጋሚ አሳስበዋል።

በአጠቃላይ በግብርና፣ በሥራ ፈጠራ፣ በትምህርት፣ በራስ አቅም ተረጂነትን በመቀነስ፣ በጸጥታ፣ በሕግ የበላይነትና በጸረ ክራይ ሰብሳቢነት ዘርፎች ተጨባጭ ውጤት ለማስመዝገብ ከወትሮው በበለጠ በማቀድ፣ በፍጥነትና በቁርጠኝነት እንደሚሠሩ ከመደመር መንግስት ምስረታ ማግስት በተፈጠር መድረኮች ሁሉ ክቡር በላይነህ ባህሩ አሳውቀዋል።

“በሁሉም መስክ ተጨባጭ አመርቂ ውጤት” !!!

ክቡር አቶ በላይነህ ባህሩ
የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ

07/11/2026

ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራትና የስፖርታዊ አብሮነትን ይበልጥ ለማጠናከር እየሠራ እንደሚገኝ የጎፋ ዞን ባህልና ስፖርት መምሪያ ገለጸ።

መምሪያው 3ኛ ዙር የፈታ ካፕ የጓደኛሞች ስፖርታዊ ውድድርን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

የግብርና ትራንስፎርሜሽንን ማረጋገጥ ማለት...
07/11/2026

የግብርና ትራንስፎርሜሽንን ማረጋገጥ ማለት...

"በፓርቲያችን ብልፅግና ከተያዙ ግቦች አንዱ  አካቶ ትግበራና  በሴቶች ተሳትፎና አመራር ሰጭነት ውጤት ማስመዝገብ ነው።"‎‎አቶ ጥላሁን ጌታቸው‎‎ሣውላ፦ጥቅምት 28/2019 ዓ/ም‎‎የጎፋ ዞን...
07/11/2026

"በፓርቲያችን ብልፅግና ከተያዙ ግቦች አንዱ አካቶ ትግበራና በሴቶች ተሳትፎና አመራር ሰጭነት ውጤት ማስመዝገብ ነው።"
‎
‎አቶ ጥላሁን ጌታቸው
‎
‎ሣውላ፦ጥቅምት 28/2019 ዓ/ም
‎
‎የጎፋ ዞን ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ የ2018 ዓ/ም የሴቶች ልማት ህብረትና የአካቶ ትግበራ ስትሪንግ ኮሚቴ የዕቅድ አፈፃፀምና ቀጣይ አቅጣጫ ላይ የውይይት መድረክ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በሣውላ ከተማ አካሄደ።
‎
‎የጎፋ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪና ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጥላሁን ጌታቸው በመድረኩ እንደተናገሩት ሴቶችን በቅድሚያ በተገቢው ማደራጀት ቀጥሎ የአስተሳሰብ ደረጃቸውን ከፍ ለማድረግ የግንዛቤ ስራ በትኩረትና በአጽንኦት መተግበርና መፈፀም ያስፈልጋል ብለዋል።
‎
‎አክለውም በፓርቲያችን ብልፅግና ከተያዙ ግቦች መካከል አንዱ አካቶ ትግበራና በሴቶች ተሳትፎና አመራር ሰጭነት ውጤት ማስመዝገብ ነው ስሉም ተደምጠዋል።
‎
‎የጎፋ ዞን ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ፀጋነሽ እንግዳ በበኩላቸው የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በሚያቅዱ ዕቅዶቻቸው ውስጥ በማካተት በማቀድ ይህንን ተግባር የሚፈፅም አካል በመወከል ተፈፃሚነቱን መከታተል ይኖርባቸዋል በማለት ተናግረዋል።
‎
‎ወ/ሮ ፀጋነሽ አያይዘው በ2018 በጀት ዓመት የተተገበሩ ጠንካራ ጎኖችን በአዲሱ በጀት ዓመት በመድገም ሳይተገበሩ የቀሩትን የዕቅድ አካል በማድረግ በሴቶች ተጠቃሚነትና ግንዛቤያቸውን በሚቀይርና ራሳቸውን ከጥቃት በሚያድን መልኩ ለመተግበር እንሰራለን ብለዋል።
‎
‎በመድረኩ የ2018 በጀት አፈፃፀም ዕቅድ እንዲሁም ተቋማትን በአካቶ አተገባበርና በሴቶች ድጋፍ ላይ ምን እንደሚሰራ የሚለካ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
‎
‎በመጨረሻም ለመምሪያ ማኔጅመንት አባላት የድጋፋዊ ክትትል እና የቀጣይ ተግባር አቅጣጫ በመስጠትና በማስቀመጥ መድረኩ ተጠናቋል።

"ግብርናችንን ከዝናብ ጥገኝነት እና ከኋላ ቀር አመራረት ዘይቤ በማላቀቅ የገጠር ትራንፎርሜሽንን ለማረጋገጥ በትኩረት እንሠራለን!" ክቡር ርዕሰ-መስተዳድር ዶ/ር ተስፋዬ በልጂጌየደቡብ ኢትዮጵ...
07/11/2026

"ግብርናችንን ከዝናብ ጥገኝነት እና ከኋላ ቀር አመራረት ዘይቤ በማላቀቅ የገጠር ትራንፎርሜሽንን ለማረጋገጥ በትኩረት እንሠራለን!" ክቡር ርዕሰ-መስተዳድር ዶ/ር ተስፋዬ በልጂጌ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የ2019 ክልላዊ የበጋ መስኖ ልማት ንቅናቄ መድረክ መካሄዱ ተጠቁሟል።



የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የ2019 ክልላዊ የበጋ መስኖ ልማት ንቅናቄ መድረክ "የውኃ ፀጋችንን አሟጠን በመጠቀም ከዝናብ ጥገኝነት የተላቀቀ ግብርናን ዕውን ለማድረግ እንሠራለን!" በሚል መሪ ቃል በአርባ ምንጭ ከተማ ተካሂዷል።

የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር ክቡር ዶ/ር ተስፋዬ በልጂጌ የንቅናቄ መድረኩን በከፈቱበት ወቅት እንደገለፁት በመደመር መንግሥት እሳቤ ግብርናችንን ከዝናብ ጥገኝነት እና ከኋላ ቀር የአመራረት ዘይቤ በማላቀቅ የገጠር ትራንስፎርሜሽንን ለማረጋገጥ በትኩረት ሊሠራ ይገባል።

የክልሉን ኅብረተሰብ የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል ለግብርና ልማት በተለይም ለመስኖ ልማት ቀዳሚ ትኩረት መስጠት ተገቢ መሆኑን ያነሱት ክቡር ርዕሰ-መስተዳድሩ ሁሉንም የውኃ ፀጋዎችንና የመስኖ አማራጮችን በመጠቀም ሥር ነቀል ለውጥ ማስመዝገብ ይጠበቃል ብለዋል።

መስኖን የምንጠቀመው በዓመት አስከ ሦስት ጊዜ በማምረት ምርታማነትን በከፍተኛ ደረጃ ማሻሻል የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽንን ያረጋግጣል ያሉት ክቡር ርዕሰ-መስተዳድሩ በኩታ ገጠም አመራረት፣ በሜካናይዜሽን እና በመስኖ ልማት ብልፅግናን ማረጋገጥ ከግብርና ልማት አካላት እንደሚጠበቅ አስገንዝበዋል።

የምናመርትበትን መንገድን በማዘመን፣ የተሻሻሉ ቴክኖሎጂዎችና የአሠራር ዘዴዎችን በመጠቀም፣ ምርትን በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመር ምርታማነትን በማሳደግ የግብይት ሁኔታውን በማሳለጥ የአርሶ አደሩን ህይወት በመሠረታዊነት ስንለውጥ ግብርናችን ይሸጋገራል ያሉት ክቡር ርዕሰ-መስተዳድሩ ከውኃ የተላቀቀ ግብርና ዕውን ማድረግ እና የክላስተር እርሻና ሜካናይዜሽንን በማስፋት የመስኖ ልማት ዕቅድ ትግበራው ይፈፀማል ብለዋል።

መስኖን በጊዜ የለንም መንፈስ፣ በታታሪነትና በመሰጠት መፈፀም እንደሚገባ ክቡር ርዕሰ-መስተዳድሩ አንስተው በተያዘው በጀት ዓመት ቀደም ሲል ከነበረው በአራት አጥፍ አሳድጎ መፈፀም እንደሚጠበቅ አሳስበዋል።

የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ ክቡር ዶ/ር ካርታ ካስኬ በበኩላቸው የግብርና ተግባራት የሥራ ዕድል የሚፈጥሩ፣ የምግብ ዋስትናን የሚያረጋግጡ፣ የወጪ ምርቶችን የሚያሳድግ እና የገቢ ምርቶችን የሚሸፍኑ፣ የኢንዱስትሪ ግብዓት የሚያቀርቡ እንዲሁም የኅብረተሰቡን ኑሮ በማሻሻል የቤተሰብ ብልፅግናን የሚያረጋግጡ ሊሆኑ ይገባል።

መስኖ ለክልሉ አርሶና አርብቶ አደሮች የምርታማነት መሠረት መሆኑን የገለፁት ክቡር የቢሮ ኃላፊው በበጀት ዓመቱ በሁለት ዙር በመስኖ ልማት የተቀመጡ የምርታማነት ግቦችን ለማሳካት የሚከናወነው ሥራ በጥብቅ ዲሲፕሊን እንደሚመራ አስገንዝበዋል።

አክለውም የበጋ መስኖ ስንዴ ልማትን በልዩ ትኩረት መፈፀም አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመው አሠራሩ በቁልፍ ተግባርነት ወስዶ ሊያስፈፅመው እንደሚገባ አስምረውበታል።

በመድረኩ የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የተፈጥሮ ሀብት ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አድማሱ አወቀ የ2018 የበጋ መስኖ ልማት አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2019 ቀጣይ ዕቅድና ወቅታዊ የግብርና ልማት ተግባራትን የሚመለከት ሰነድ አቅርበዋል።

አቶ አድማሱ ባቀረቡት ዕቅድ በተያዘው በጀት ዓመት በበጋ መስኖ በሁለት ዙር በክልሉ ከ186 ሺህ ሔክታር በማልማት ከ47.5 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ለማሳካት በዝርዝር መታቀዱ ተመልክቷል።

ከዚህ ውስጥ ከ8000 ሔክታር መሬት በላይ በስንዴ እንደሚሸፈን መታቀዱን አቶ አድማሱ አብራርተዋል። ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም በመሸፈን ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገርም በኦሞ ወንዝ ላይ ትኩረቱን ያሳረፈ የመስኖ ልማት ሥራ በትኩረት እንደሚፈፀም አቶ አድማሱ አስረድተዋል።

አቶ አድማሱ አክለውም በሰብል፣ በአሰንስሳትና በተፈጥሮ ሀብት ልማት እንዲሁም በቡና ልማት፣ አደጋ ስጋት ሥራ አመራርና ምግብ ዋስትና፣ የኅብረት ሥራ ልማት እና የግብርና ግብዓትና ገጠር ፋይናንስ አቅርቦት እና ሌሎች
የትኩረት መስኮችንም በበጀት ዓመቱ በትኩረት የሚፈፀሙ ተግባራትን እንደሆኑ አብራርተዋል።

በቀረበው ሰነድ ላይ የመድረኩ ተሳታፊዎች የውኃ አማራጮች በመለየት፣ መሥራት እንደሚገባ አዳዲስ የተገነቡ የመስኖ ፕሮጀክቶችን ወደ ሥራ ስለማስገባት፣ በመስኖ ልማት ከአርሶ አደሩ ጋር የጋራ መግባባት ላይ ስለመድረስ እና ባለሙያው በመደመር መንግስት እሳቤ መስኖን ለማሳካት ዝግጁ እንዲሆን ከማድረግ አኳያ አስተያየት በመስጠት ከራሳቸው ተጨባጭ ሁኔታ አኳያ ሁሉንም የውኃ አማራጮች በመጠቀም ለመስኖ ቀዳሚ ትኩረት በመስጠት ለመሥራት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

ለመድረኩ በቀረበው ክልላዊ የመስኖ ልማት እና ዋና ዋና የትኩረት መስኮች የተቀረፁ የዕቅድ ግቦች ለማሳካት እንደሚረባረቡም ተሳታፊዎች አረጋግጠዋል።

በመስኖ ልማትና በቀጣይ ሊተኮርባቸው በሚገቡ የግብርና ልማት አጀንዳዎች ላይ አቅጣጫ ተቀምጦ የሥራ መመሪያ ተሰጥቷል።

የ2019 የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ዕቅድ የግብ ስምምነት ሰነድም በቢሮውና በዞኖች መካከል ተፈርሟል።

በንቅናቄ መድረኩ ክቡር ርዕሰ-መስተዳድር ተስፋዬ በልጂጌ (ዶ/ር)፣ የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ ካርታ ካስኬ (ዶ/ር) እና የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ገዛኸኝ ጋሞን ጨምሮ የክልሉ መንግሥት ከፍተኛ አመራሮች፣ የዞንና የሪጂዮ-ፖሊስ ከተማ አስተዳዳሪዎችና ከንቲባዎች፣ ግብርና መምሪያ ኃላፊዎች፣ የግብርና ማኔጅመንት አባላት እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መሳተፋቸው ተዘግቧል።

ጠበቆች ገንዘብን ሳይሆን ሰብዓዊነትን በማስቀደም የተበደሉ ዜጎችን መብት ለማስከበር መረባረብ እንዳለባቸው ተጠቆመጥቅምት 28/2019 ዓ.ም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጠበቆች ማህበር ''የተደራጀ...
07/11/2026

ጠበቆች ገንዘብን ሳይሆን ሰብዓዊነትን በማስቀደም የተበደሉ ዜጎችን መብት ለማስከበር መረባረብ እንዳለባቸው ተጠቆመ

ጥቅምት 28/2019 ዓ.ም

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጠበቆች ማህበር ''የተደራጀ የጥብቅና ሙያ፣ ለተጠናከረ የፍትህ ሥርዓት'' በሚል መሪ ቃል ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን በወላይታ ሶዶ ከተማ አካሂዷል።

በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙሉቀን ታደሰ እንደገለጹት፣ ቢሮው የፍትህ ተቋማትን ሪፎርም ተግባራዊነትን ለማረጋገጥ የፍትህ መዋቅሮችን በማሻሻል እንዲሁም በጠበቆች ሙያዊ ሥነ-ምግባር ላይ አበክሮ እየሠራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

ጥብቅና አገልግሎት እንጂ ንግድ አይደለም ያሉት ኃላፊው፣ ጠበቆች ከገንዘብ በላይ ሰብዓዊነትን በማስቀደም በፍትህ እጦት የተጎዱና የተበደሉ የማህበረሰብ ክፍሎችን መብት ለማስከበር መረባረብ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ከአሠራር ጋር ተያይዘው የሚታዩ ጥሰቶችን በማረም የጠበቆች ማህበሩን ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስ በክልሉ ከሚፀኙ ከዩኒቨርሲቲዎችና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመናበብና በመቀናጀት እንደሚሠራም አቶ ሙሉቀን ገልጸዋል።

በተጨማሪም፣ የተሻለ አቅም የገነቡና ልምድ ያካበቱ የዞን ጠበቆች ማህበራት ልምድና እውቀታቸውን በመለዋወጥ ለተሻለ ውጤት መቀናጀት እንዳለባቸው አክለዋል።

የቢሮው ምክትል ኃላፊና የሕግ ጉዳዮች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ካሳሁን ፍልፍሉ በበኩላቸው በቢሮው ፣ የጥብቅና ሙያ በፍትህ ሥርዓቱ ውስጥ ያለውን ወሳኝ ሚና በማጉላት፣ በአዳዲስ ሕጎችና ደንቦች ዙሪያ ክትትልና ለጠበቆች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች እንደሚከናወኑ ተናግረዋል።

በማህበሩ ስብሰባዎች የማይሳተፉና በማህበሩ መመሪያዎችና ደንቦች መሠረት የማይሠሩ አካላትን በጥብቅ በመቆጣጠር የማረም ሥራ እንደሚሠራም ምክትል ኃላፊው አስታውቀዋል።

የክልሉ ጠበቆች ማህበር ፕሬዚዳንት ጠበቃ ተከተል ላቤና፣ ማህበሩ በጠበቆች አስተዳደር ሕግ መሠረት የተቋቋመ ተቋም መሆኑን ጠቁመው፣ በክልሉ የሚገኙ ሁሉም ጠበቆች የማህበሩን ደንብና መመሪያ የመከተል ግዴታ እንዳለባቸው ገልጸዋል።

ማህበሩ ሕግና መመሪያን ተከትለው ለሚሠሩ ጠበቆች ድጋፍና ጥበቃ እንደሚያደርግ፣ የሥነ-ምግባር ጥሰት በሚፈጽሙ ጠበቆች ላይ ደግሞ ተገቢው የዲሲፕሊን እርምጃ እንደሚወሰድ ፕሬዚዳንቱ አስታውቀዋል።

የጉባኤው ተሳታፊዎች የክልሉ ፍትህ ቢሮ ማህበሩን ለማጠናከር ላደረገው አስተዋፅዖ በማመስገን በተለያዩ የሕግና የሙያ ጉዳዮች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠናዎች እንዲዘጋጁ ጠይቀዋል።

በጉባኤው የጠበቆችን ሙያዊ ሥነ-ምግባር በተመለከተ የተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ፣ የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርትና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን በጋራ ለመሥራት በተለዩ ጉዳዮች የክልሉ ፍትህ ቢሮና የጠበቆች ማህበር የግብ ስምምነት በመፈራረም ጉባኤው ተጠናቅቋል።

የክልሉ መሬት አስተዳደር ቢሮ በኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ የገጠር መሬት መረጃ ሥርዓትን ለማስጀመር የሚያስችል ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ ጥቅምት 28/2019 ዓ.ም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መሬት አስተ...
07/11/2026

የክልሉ መሬት አስተዳደር ቢሮ በኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ የገጠር መሬት መረጃ ሥርዓትን ለማስጀመር የሚያስችል ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

ጥቅምት 28/2019 ዓ.ም

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መሬት አስተዳደር ቢሮ በኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ የ2ኛ ደረጃ የመሬት ልኬት በመጠናቀቁ የገጠር መሬት መረጃ ሥርዓትን ለማስጀመር የሚያስችል ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።

የገጠር መሬት መረጃ ሥርዓትን ለማስጀመር እንዲያስችል
ድጋፍ የተደረጉት ዴስክቶኘ፣ ፎቶኮፒ ማሽንና ዩፒኤስ ሲሆኑ የመሬት አስተዳደር ተግባርን በተገቢው መልኩ ማሳለጥ እንዲችሉ በጥንቃቄ ሊያዙ እንደሚገባም ተመላክቷል።

የቢሮሉ ኃላፊ አቶ ተፈሪ አባተ በርክክቡ ወቅት እንደገለፁት ቁሳቁሶቹ ዘመናዊ ከመሆናቸዉ የተነሳ የመሬት መረጃ ሥርዓትን ለማሳለጥ የጎላ ድርሻ እንዳላቸው ጠቁመው ፤ ከዚህ አኳያ በጥንቃቄ ሊያዙ እንደሚገባ አሳስበዋል።

አካባቢዉ ቡና አብቃይ መሆኑ ይታወቃል ያሉት ኃላፊዉ በወረዳዉ ያሉ አርሶአደሮች የመሬት ይዞታቸዉን በመጠቀምና ከዲጂታል(ፋይዳ) መታወቂያ ጋር በማስተሳሰር ከአበዳሪ የፋይናንስ ተቋማት የገንዘብ፣ የግብርና ግብዓት ብሎም ማሽነሪ በብድር በመዉሰድ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በትኩረት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

በዋናነትም ቁሳቁሶቹ ልኬቱ የተጠናቀቀዉን መሬት ወደ አንድ ቋት ለማስገባት የሚያግዙ በመሆናቸዉ የመሬት መረጃ ሥርዓቱ በጥራት መከናወን አለበት ሲሉ ቢሮ ኃላፊው አሳስበዋል።

በቀጣይም የመሬት አስተዳደር ሥርዓቱን ሊያዘምኑ የሚያስችሉ ድጋፎች ተጠናክረዉ እንደሚቀጥሉ አቶ ተፈሪ አስረድተዋል ።

የቢሮዉ ምክትልና የመሬት አጠቃቀምና የጂኦ ስፓሻል ዘርፍ ኃላፊ ዮሴፍ ማሩ (ዶ/ር) ከዓለም ባንክ የተገኙት ቁሳቁሶች የተሻለ ሥራን ለማከናወን ስለሚያስችሉ የመሬት መረጃ ሥርዓቱን በአግባቡ በማከናወን አርሶ አደሮች ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ሁኔታ ማመቻቸት እንደሚገባ ማስገንዘባቸውን የቢሮው ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።

Address

Felege Niway

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gofa Zone Government Communication Affairs Department posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Gofa Zone Government Communication Affairs Department:

Shortcuts

Share