Gozamin woreda communication affairs

Call Directions Contact the organization

Gozamin woreda communication affairs ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ ለሁሉም እናደርሳለን

ከ46 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የጎዛምን ወረዳ ገቢዎች ጽህፈት ቤት ገለፀ። ****ጥቅምት 26/2019 ዓ.ም  (ጎዛምን ኮሙኒኬሽን) በምስራቅ ጎጃም ዞን የጎዛምን ወረዳ ገቢዎች ጽ/...
05/11/2026

ከ46 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የጎዛምን ወረዳ ገቢዎች ጽህፈት ቤት ገለፀ።
****
ጥቅምት 26/2019 ዓ.ም (ጎዛምን ኮሙኒኬሽን) በምስራቅ ጎጃም ዞን የጎዛምን ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት በ2019 በጀት አመት እንደ ወረዳ ይሰበሰባል ተብሎ ከታቀደው 260 ሚሊየን 414 ሺህ 415 ብር ውስጥ ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ 46 ሚሊየን 321ሺህ 04 ብር በመሰብሰብ የእቅዱን 17 ነጥብ 78 በመቶ ማሳካት መቻሉን የጽ/ቤቱ የግብር ትምህርት ኮሙዩኒኬሽን ዋና የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ የሽዋስ ደምሌ ገልፀዋል ።

ገቢው የተሰበሰበው ከንግድ፣ከእርሻ ስራ ገቢ ግብር ፣ከመሬት መጠቀሚያ ግብር፣ ከባለሃብቶች ፣ከሮያሊቲ እና ከልዩ ልዩ የገቢ አርዕስቶች መሆኑን አቶ የሽዋስ ተናግረዋል ።

አቶ የሽዋስ አያይዘውም የገቢ አፈፃፀሙ ከእቅዱ አንፃር ሲታይ ዝቅተኛ መሆኑን በመጠቆም ለዚህም የፀጥታው ችግር እና የአጋር አካላት የትኩረት ማነስ በምክንያትነት እንደሚጠቀሱ አስረድተዋል።

በመጨረሻም እንደ ተቋም የታቀደውን የገቢ እቅድ ለማሳካት ግብር ከፋዮች የተጣለባቸውን ግብር በወቅቱ እንዲከፍሉ እና አጋር አካላት በየተቋሙ ተሸንሽኖ የተሰጣቸውን ዕቅድ በላቀ ትጋትና ተነሳሽነት መፈፀም ያለባቸው መሆኑን አቶ የሽዋስ አሳስበዋል።

🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊

ለበለጠ መረጃ የጎዛምን ወረዳ ኮሙዩኒኬሽንን ይወዳጁ
‎ቲክቶክ : tiktok.com/
‎ቴሌግራም :https://t.me/+vc67i3kF481hZmM0
‎ዩቲዩብ :https://youtube.com/?si=q5oxnXn3EmC4ABrq

በወረዳ የተጀመሩ የልማት ኢንሼቲቮችን በውጤታማነት ለመፈፀም የገቢ አማራጮችን ማስፋት እንደሚገባ ተገለፀ። ****ጥቅምት 25/2019 ዓ.ም  (ጎዛምን ኮሙዩኒኬሽን) በምስራቅ ጎጃም ዞን በጎዛ...
04/11/2026

በወረዳ የተጀመሩ የልማት ኢንሼቲቮችን በውጤታማነት ለመፈፀም የገቢ አማራጮችን ማስፋት እንደሚገባ ተገለፀ።
****
ጥቅምት 25/2019 ዓ.ም (ጎዛምን ኮሙዩኒኬሽን) በምስራቅ ጎጃም ዞን በጎዛምን ወረዳ በ2019 በጀት ዓመት የሚተገበሩ የልማት ኢንሼቲቮች አስመልክቶ የእቅድ ትወውቅ እና የምክክር መድረክ ተካሂዷል።

በዕለቱ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ወርቅነህ እንደግ እንደ ወረዳ የተለያዩ የልማት ኢንሼቲቮችን በመተግበር በኩል በተለይም በሌማት ቱሩፋት፣ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት፣በሞሰብ አንድ ማዕከል አገልግሎት፣ በገጠር ኮሪደር ልማት፣ በአረንጓዴ አሻራ ፣በተማሪዎች የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም፣በፅዱ ጤና ተቋም ፈጠራ እና በዲጅታላይዜሽን ዘርፍ ተስፋ ሰጭ ጅምሮች እንዳሉ ገልፀዋል።

ኃላፊው አያይዘውም ኢኒሼቲቮችን በውጤታማነት ለመተግበር እንደ ወረዳ በርካታ ምቹ ሁኔታዋች እንዳሉ ጠቅሰው በየደረጃው ያለው አመራርና ባለሙያ ለኢኒሼቲቮች መተግበር በቁርጠኝነትና በታታሪነት መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በመድረኩ በመደመር መንግስት እሳቤ የተነደፉ በወረዳው የሚተገበሩ የልማት ኢንሼቲቮችን አስመልክቶ የተዘጋጀ ሰነድ በወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፓለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ በአቶ እንዳዘዘ ጓዴ ቀርቦ በተሳታፊዋች ውይይት ተደርጎበታል።

የልማት ኢንሼቲቮች የአንድን ሀገር ኢኮኖሚ እድገትን ለማፋጠን፣ የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል፣የድህነት መጠንን ለመቀነስ ፣የስራ እድል ለመፍጠር እና የሀገርን የልማት አቅም ለማሳደግ የሚተገበሩ የልማት ፕሮግራሞች፣ፕሮጀክቶችና ልዩ ልዩ የልማት እርምጃዋች መሆናቸውን አቶ እንዳዘዘ አስገንዝበዋል።

አቶ እንዳዘዘ አክለውም በወረዳው የተጀመሩ የመንግስት የልማት ኢኒሼቲቮች በተቀመጠላቸው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት በውጤታማነት ለመፈፀም የገቢ አማራጮችን ማስፋትና ጠንካራ የድጋፍና ክትትል ስርዓት መዘርጋት እንዳለበት ገልፀዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ለኢንሼቲቮች ውጤታማነት በትኩረት እንደሚሰሩ ገልፀው በተግባር ሂደት እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን አንስተዋል።

በውይይት መድረኩ የወረዳው አመራሮች፣ የልማት ኢንሼቲቮችን በመተግበር በኩል ተዋናይ የሆኑ የተቋማት የስራ ቡድን መሪዋችና ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል።

🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊

ለበለጠ መረጃ የጎዛምን ወረዳ ኮሙዩኒኬሽንን ይወዳጁ
‎ቲክቶክ : tiktok.com/
‎ቴሌግራም :https://t.me/+vc67i3kF481hZmM0
‎ዩቲዩብ :https://youtube.com/?si=q5oxnXn3EmC4ABrq

በተሻሻለው ሀገር አቀፍ የሴቶች የልማት ህብረት አደረጃጀትና አሰራር መመሪያ ዙሪያ ለወረዳና ለቀበሌ የጥምረት ኮሚቴዋች ስልጠና ተሰጠ።***ጥቅምት 24/2019 ዓ.ም (ጎዛምን ኮሙዩኒኬሽን) በ...
03/11/2026

በተሻሻለው ሀገር አቀፍ የሴቶች የልማት ህብረት አደረጃጀትና አሰራር መመሪያ ዙሪያ ለወረዳና ለቀበሌ የጥምረት ኮሚቴዋች ስልጠና ተሰጠ።
***
ጥቅምት 24/2019 ዓ.ም (ጎዛምን ኮሙዩኒኬሽን) በምስራቅ ጎጃም ዞን የጎዛምን ወረዳ ሴቶች ፣ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት በተሻሻለው ሀገር አቀፍ የሴቶች የልማት ህብረት አደረጃጀትና አሰራር መመሪያ ዙሪያ ለወረዳና ለቀበሌ የጥምረት ኮሚቴዋች ስልጠና ሰጠ።

በመድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጎዛምን ወረዳ ሴቶች ፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሪት ውዴ ደምል ስልጠናው የጥምረት ኮሚቴ አባላት ስለ ተሻሻለው የአደረጃጀትና የአሰራር መመሪያ ወጥ የሆነ ግንዛቤ እንዲጨብጡ ለማድረግ የተዘጋጀ ስልጠና እንደሆነ ገልፀዋል።

በዕለቱ የተሻሻለው የሴቶች የልማት ህብረት አደረጃጀትና አሰራር መመሪያ በተቋሙ የሴቶች ግንዛቤ ፣ ንቅናቄ እና ማስፋፊያ ቡድን መሪ በሆኑት በአቶ ብርሀኑ ውቤ ቀርቦ በተሳታፊዋች ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።

ከስያሜ አንፃር ከዚህ በፊት የሴቶች የልማት ቡድን ይባል የነበረው በተሻሻለው መመሪያ የሴቶ የልማት ህብረት በሚል እንደተቀየረ እንዲሁም አንድ ለአሞስት ይባል የነበረው ትስስር አንድ ለአስር በሚል እንደተተካ አቶ ብርሀኑ አስገንዝበዋል።

ከእድሜ አንፃር ከዚህ በፊት በአደረጃጀቱ የሚታቀፉ ከ20 እስከ 60 የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሴቶች የነበረ እንደሆነና በአዲሱ መመሪያ ግን ከ18 ዓመት በላይ ያሉ ሁሉም ሴቶች እና ከ15 ዓመት በላይ የሆኑ ከትምህርት ገበታ ውጭ ያሉ ሴቶች በሴቶች የልማት ህብረት አደረጃጀት እንደሚካተቱ ተገልጿል።

የወረዳው ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ የኔጌታ ወርቁ የሴቶች የልማት ህብረት የጤና ልማት ተግባራትን ውጤታማ ለማድረግ የማይተካ ሚና እንዳለው በመጠቆም የጤና ባለሙያዋች የልማት ህብረቱን በመደገፍና በማጠናከር በኩል በትኩረት መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል።

የጥምረት ኮሚቴዎች በቀጣይ በአጭር ጊዜ በየቀበሌው ያሉትን የሴቶች የልማት ህብረቶች በአዲስ መልክ መልሰው እንዲያደራጁ፣ እንዲያጠናክሩ እና የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት እንዲያረጋግጡ ወ/ሮ ውዴ አሳስበዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዋች በበኩላቸው የሴቶች የልማት ህብረት አደረጃጀትን ከማደራጀት ጀምሮ የድጋፍና ክትትል ተግባሩ ለጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ብቻ የተተወ ስለሆነ በቀጣይ ቀበሌ ላይ ያሉ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ለተግባሩ ትኩረት ሰጥተው መስራት አለባቸው ብለዋል።

🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊

ለበለጠ መረጃ የጎዛምን ወረዳ ኮሙዩኒኬሽንን ይወዳጁ
‎ቲክቶክ : tiktok.com/
‎ቴሌግራም :https://t.me/+vc67i3kF481hZmM0
‎ዩቲዩብ :https://youtube.com/?si=q5oxnXn3EmC4ABrq

ህብረተሰቡን በላቀ ደረጃ በማሳተፍ የጤና አገልግሎት ጥራትን ማሻሻል እንደሚገባ ተገለፀ።***ጥቅምት 23/2019 ዓ.ም (ጎዛምን ኮሙዩኒኬሽን) በምስራቅ ጎጃም ዞን የጎዛምን ወረዳ ጤና ጽ/ቤት...
02/11/2026

ህብረተሰቡን በላቀ ደረጃ በማሳተፍ የጤና አገልግሎት ጥራትን ማሻሻል እንደሚገባ ተገለፀ።
***
ጥቅምት 23/2019 ዓ.ም (ጎዛምን ኮሙዩኒኬሽን) በምስራቅ ጎጃም ዞን የጎዛምን ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የ1ኛ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ አካሂዷል።

በመድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አለሙ ውበት እንደ ወረዳ በጤናው ዘርፍ በርካታ ውጤታማ ስራዋች እየተሰሩ መሆኑን ጠቅሰው ለእነዚህ ተግባራት ውጤታማነት በየደረጃው ያሉ የጤና ባለሙያዋች እያበረከቱ ላለው አስተዋፅኦ ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል።

አቶ አለሙ አክለውም ባለሙያዎች በላቀ የህዝብ ወገንተኝነት በዘርፉ የሚታዩ ውስን የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ማረም እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በመድረኩ በወረዳው በሩብ ዓመቱ በጤናው ዘርፍ የተከናወኑ ዝርዝር ተግባራት አፈፃፀም ሪፖርት እንዲሁም የድጋፍ ጉብኝት ግብረ መልስ ቀርቦ በተሳታፊዋች ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።

የወረዳው የህዝብ ግንኙነትና አደረጃጀት ዋና አማካሪ የሆኑት አቶ ወርቅነህ እንደግ እንደ ወረዳ የጤና ዘርፍ ኢንሼቲቮችን ከመተግበር አንፃር መልካም ጅምሮች መኖራቸውን ገልፀው በቀጣይ ህብረተሰቡ የጤና መድህን ተጠቃሚ እንዲሆን በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

የወረዳው ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ የኔጌታ ወርቁ በሩብ ዓመቱ በእናቶችና ህፃናት ጤና አጠባበቅ ፣በጤና ግብዓት አቅርቦት እንዲሁም የጤና አገልግሎቶችን ተደራሽነት በማስፋት በኩል አበረታች ስራዋች መሰራታቸውን ገልፀዋል።

አቶ የኔጌታ አክለውም በቀጣይ የጤና መሠረተ ልማቶችን በማጠናከር በኩል፣ ሞዴል ቀበሌ በመፍጠር በኩል ፣ የጤና የመረጃ ጥራት ላይ ያሉ ችግሮችን እንዲሁም ተቋማትን ወደ ተሻለ ተቀራራቢ አፈፃፀም በማምጣት በኩል ያሉ ውስንነቶችን ለማረም በትኩረት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዋች በበኩላቸው እንደ ወረዳ የባለሙያዋች የትርፍ ሰዓት ክፍያ በወቅቱ እንዲከፈል እና በጤና ጣቢያ ደረጃ ያሉ ክፍት የስራ መደቦች በሰው ሀይል እንዲሟሉ ጥያቄ አቅርበዋል።

በመጨረሻም የጤና ጽ/ቤት ፣ ጤና ጣቢያ እና ጤና ኬላ ትስስርን የበለጠ ማጠናከር እንደሚገባ እንዲሁም ህብረተሰቡን በላቀ ደረጃ በማሳተፍ የጤና ተቋማትን ውስጣዊና ውጫዊ ገፅታ መገንባትና የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ አቅጣጫ ተቀምጦ መድረኩ ተጠናቋል።

🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊

ለበለጠ መረጃ የጎዛምን ወረዳ ኮሙዩኒኬሽንን ይወዳጁ
‎ቲክቶክ : tiktok.com/
‎ቴሌግራም :https://t.me/+vc67i3kF481hZmM0
‎ዩቲዩብ :https://youtube.com/?si=q5oxnXn3EmC4ABrq

የጎዛምን ወረዳ ሚሊሻ ጽ/ቤት ለ9ኛ ዙር ሲያሰለጥናቸው የቆዩ ሠላም አስከባሪዎችን አስመረቀ።***ጥቅምት 23/2019 ዓ.ም (ጎዛምን ኮሙዩኒኬሽን ) በምስራቅ ጎጃም ዞን የጎዛምን  ወረዳ  ሚ...
02/11/2026

የጎዛምን ወረዳ ሚሊሻ ጽ/ቤት ለ9ኛ ዙር ሲያሰለጥናቸው የቆዩ ሠላም አስከባሪዎችን አስመረቀ።
***
ጥቅምት 23/2019 ዓ.ም (ጎዛምን ኮሙዩኒኬሽን ) በምስራቅ ጎጃም ዞን የጎዛምን ወረዳ ሚሊሻ ጽህፈት ቤት ለ9ኛ ዙር ሲያሠለጥናቸው የቆዩ ሠላም አስከባሪዋችን አስመርቋል።

በምረቃ መርሀ ግብሩ ላይ የጎዛምን ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አለሙ ውበትን ጨምሮ ሌሎች የወረዳው የፖለቲካና የፀጥታ አመራሮች እንዲሁም የፀጥታ ተቋማት ባለሙያዋች ተሳትፈዋል።

በመርሀ ግብሩ ላይ በወረዳው ህግ በማስከበር ሂደት ዉስጥ ለተሰዉ ጓዶች የህሊና ፀሎት ተደርጓል።

የምረቃ መርሀ ግብሩን ንግግር ያደረጉ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አለሙ ውበት ተመራቂዎች የአካባቢን ሰላምና ጸጥታ ለማስጠበቅ እንዲሁም ዘላቂ ሰላም ለመገንባት በህዝብ ወገንተኝነትነ ስሜት በቁርጠኝነት ልትሰሩ ይገባል ብለዋል።

አቶ አለሙ አያይዘውም ህዝባችንን ከደረሰበት መከራና ስቃይ ለማላቀቅ ተመራቂ ሰላም አስከባሪዎች ቆርጠው ወታደራዊ ስልጠና በመውሰዳቸው ትልቅ ክብርና ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።

የወረዳው ሚሊሻ ጽ/ቤት ሀላፊ የሆኑት ኢንስፔክተር ማናየ ላቃቸው በበኩላቸው ስልጠናው ከነሀሴ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ወራት ሲሰጥ የቆየ መሆኑን በመጠቆም ተመራቂዎች በቀጣይ የሚሰጣቸውን የህግ ማስከበርና የግዳጅ ስምሪታቸውን በብቃት፣በታታሪነትና በብቃት መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ኢንስፔክተሩ አክለውም ሚሊሻ እና ሰላም አስከባሪዎች ለህዝብ ሠላም የሚሠሩ ሁነኛ የሠላምና የልማት አርበኞች መሆናቸውን ተናግረዋል።

አዲስ ተመራቂ ሰላም አስከባሪዋች በበኩላቸው በስልጠናው ያገኙትን እውቀትና ክህሎት ተጠቅመው በቀጣይ የሚሰጣቸውን ተልዕኮ በብቃት እንደሚወጡ አረጋግጠዋል።

በመጨረሻም ተመራቂ ሰላም አስከባሪዎች ህዝቡን በታማኝነትና በሀቀኝነት ህግና ስርዓትን አክብረው የሚያገለግሉ መሆኑን የሚያረጋግጥ ባለ ስምንት ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥተው መርሀ ግብሩ ተጠናቋል።

🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊

ለበለጠ መረጃ የጎዛምን ወረዳ ኮሙዩኒኬሽንን ይወዳጁ
‎ቲክቶክ : tiktok.com/
‎ቴሌግራም :https://t.me/+vc67i3kF481hZmM0
‎ዩቲዩብ :https://youtube.com/?si=q5oxnXn3EmC4ABrq

በምስራቅ ጎጃም ዞን ብቸና ከተማ በብቸና አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተገነባው የመማሪያ ክፍል ህንጻ  ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ።ህንፃው ከእነማይ ወረዳና ከብቸና ከተማ አስተዳደ...
02/11/2026

በምስራቅ ጎጃም ዞን ብቸና ከተማ በብቸና አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተገነባው የመማሪያ ክፍል ህንጻ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ።

ህንፃው ከእነማይ ወረዳና ከብቸና ከተማ አስተዳደር አልማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ፣በህብረተሰብ ተሳትፎ ፣ በትምህርት ቤቱ የውስጥ ገቢና ከሌሎች አካላት በተገኘ በጀት የተገነባ ነው።

ግንባታው ከ12 ሚሊየን ብር በላይ ወጭ እንደተደረገበት የተገለፀ ሲሆን፣ ምቹ የመማሪያ ህንጻዎችን መገንባት ለትምህርት ጥራት ያለው ፋይዳው የጎላ ነው ተብሏል።

መረጃው የእነማይ ወረዳ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ነው።

🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊

ለበለጠ መረጃ የጎዛምን ወረዳ ኮሙዩኒኬሽንን ይወዳጁ
‎ቲክቶክ : tiktok.com/
‎ቴሌግራም :https://t.me/+vc67i3kF481hZmM0
‎ዩቲዩብ :https://youtube.com/?si=q5oxnXn3EmC4ABrq

የጎዛምን ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የ1ኛ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ እያካሄደ ነው።***ጥቅምት 23/2019 ዓ.ም (ጎዛምን ኮሙዩኒኬሽን) በምስራቅ ጎጃም ዞን የጎዛምን ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የ...
02/11/2026

የጎዛምን ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የ1ኛ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ እያካሄደ ነው።
***
ጥቅምት 23/2019 ዓ.ም (ጎዛምን ኮሙዩኒኬሽን) በምስራቅ ጎጃም ዞን የጎዛምን ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የ1ኛ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ እያካሄደ ነው።

በዕለቱ በወረዳው በ1ኛው ሩብ ዓመት በጤናው ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራት አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ በተሳታፊዋች ሰፊ ውይይት እንደሚደረግበት ተመላክቷል።

በውይይት መድረኩ የወረዳው አስተባባሪ አመራሮች፣ የጤና ጣቢያዎች የቦርድ ሰብሳቢዋች፣ሲቪክ ማህበራት፣ የወረዳው የጤና ጽ/ቤት ኦፊሰሮች፣ የጤና ጣቢያ ኃላፊዎች ፣ የማህበራዊ ክላስተር ተቋማት አመራሮች፣ የግል ጤና ተቋማት ተወካዮች፣ የቀበሌ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች እና ከጤና ጣቢያ ሦስት የተመረጡ ባለሙያዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊

ለበለጠ መረጃ የጎዛምን ወረዳ ኮሙዩኒኬሽንን ይወዳጁ
‎ቲክቶክ : tiktok.com/
‎ቴሌግራም :https://t.me/+vc67i3kF481hZmM0
‎ዩቲዩብ :https://youtube.com/?si=q5oxnXn3EmC4ABrq

ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የደብረ ብርሃን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልገሎት መርቀው ሥራ አስጀመሩ።ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የደብረ ብርሃን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልገሎትን መርቀው ...
01/11/2026

ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የደብረ ብርሃን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልገሎት መርቀው ሥራ አስጀመሩ።

ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የደብረ ብርሃን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልገሎትን መርቀው ሥራ አስጀምረዋል። በማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓቱ ከርእሰ መሥተዳድሩ በተጨማሪ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

የደብረ ብርሃን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በከተማዋ ፈጣን እና ዘመናዊ አገልግሎት ለመስጠት የተገነባ ነው።
የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎቱ በርካታ ተቋማትን እና በርካታ አገልግሎቶችን በአንድ ጊዜ መስጠት የሚያስችል ነው። በአማራ ክልል ዘመናዊ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላትን እየተገነቡ ለአገልግሎት እየበቁ ነው።

#የመደመርመንግሥት
!

አሚኮ

28/10/2026

በምስራቅ ጎጃም ዞን በጎዛምን ወረዳ የተቀናጀ የግብርና ልማትና የቴክኖሎ ጂ ሽግግር ማእከል ውስጥ እየለማ የ ሚገኝ ቡና

የጎዛምን ወረዳ"ከተረጅነት  ወደ ምርታማነት" የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት በወረዳው  በፈንድቃ እና በአዲስና ጉሊት ቀበሌ በዘርፉ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን አስመልክቶ የመስክና የዴስክ ድጋፎችን...
27/10/2026

የጎዛምን ወረዳ"ከተረጅነት ወደ ምርታማነት" የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት በወረዳው በፈንድቃ እና በአዲስና ጉሊት ቀበሌ በዘርፉ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን አስመልክቶ የመስክና የዴስክ ድጋፎችን አደረጉ።

ጥቅምት 17/2019 ዓ.ም (ጎዛምን ኮሙዩኒኬሽን)

🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊

ለበለጠ መረጃ የጎዛምን ወረዳ ኮሙዩኒኬሽንን ይወዳጁ
‎ቲክቶክ : tiktok.com/
‎ቴሌግራም :https://t.me/+vc67i3kF481hZmM0
‎ዩቲዩብ :https://youtube.com/?si=q5oxnXn3EmC4ABrq

Address

T'is Abay

Telephone

+251587713817

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gozamin woreda communication affairs posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Gozamin woreda communication affairs:

Shortcuts

Share