Gurage Zone Culture and Tourism

Directions Website Contact the organization

Gurage Zone Culture and Tourism የጉራጌ ዞን ባህላዊ እሴቶት ፣ ታሪካዊ እና ተፈጥሮአዊ የቱሪስት መስህቦች ይቃኙበታል።

የጉራጌ ሕዝብ መገለጫ የሆነው ጀፎረ በመጠበቅና በማልማታችን አካባቢያችን ለኑሮ ምቹና ማራኪ ሆኖልናል፦በጌታ ወረዳ የበኬ መንደር ነዋሪዎችጥቅምት 30/2019(ወልቂጤ)ጀፎረ የጉራጌ ሕዝብ ከትው...
09/11/2026

የጉራጌ ሕዝብ መገለጫ የሆነው ጀፎረ በመጠበቅና በማልማታችን አካባቢያችን ለኑሮ ምቹና ማራኪ ሆኖልናል፦በጌታ ወረዳ የበኬ መንደር ነዋሪዎች

ጥቅምት 30/2019(ወልቂጤ)

ጀፎረ የጉራጌ ሕዝብ ከትውልድ ወደ ትውልድ እያስተላለፈ ካቆያቸው ውብ ባህላዊ እሴቶች መካከል ተጠቃሽ ነው።

በአንድነት፣ በመተጋገዝና በትብብር ላይ የተመሠረተው ጀፎረ ሰዎች የአንዱን ችግር እንደራሳቸው በመመልከት በጋራ መፍትሔ የሚፈልጉበት፣ ለጋራ ጥቅምም በአንድነት የሚተጉበት የማኅበራዊ አኗኗር መገለጫ መሆኑ ይነገራል።

ይህ እሴት የጉራጌ ሕዝብ የመተሳሰብ፣ የመደጋገፍና የአብሮነት መሠረት ከመሆኑም በላይ በዘመናዊ ማኅበረሰብ ግንባታ ውስጥም ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።

ጀፎረ ሰዎችን በጋራ ዓላማ የሚያስተሳስር፣ የመተጋገዝ ባህልን የሚያጠናክርና ለትውልድ መልካም አርዓያ የሚሆን የጉራጌ ሕዝብ ውድ ባህላዊ ሀብት ነው።

በዘመናት ዑደት ውስጥ ከነግርማ ሞገሱ የተሻገረ የጉራጌ መንደሮች ባህላዊ ጎዳና፣ የትውፊታዊ ትዕይንቶች መድረክ ሲሆን የሀገር በቀል ዕውቀትና ጥበብ ማሳያ ምዕተ- ዓመታት የተሻገረ የትውልድ ቅርስም ነው ጀፎረ!

በአባቶች ጥበብ የተሰራ ጀፎረ ከሥራ ወዳዱ የጉራጌ ጥንተ-ማኅበረሰብ ዘንድ በንግድ እንቅስቃሴ ሂደት ተወጥኖ ከወትሮ እስከ ዘንድሮ ዘልቋል።

ጀፎረ ውበትና ጌጥ ብቻ አይደለም። ትውፊታዊ መልክና ግልጋሎቱ ፈርጀ-ብዙ ነው። በዘፈቀደ የሚሰመር ሳይሆን የራሱ የአሰማመርና የልኬት ስልት እንዳለው ይነገራል።

እናም ጀፎረ ተራ ጎዳና ሳይሆን የአካባቢው ተወላጆች ከልጅነት እስከ ዕውቀት ማንነት የሚቀረጽበት የሕይወት ጎዳና ነው።

በጉራጌ ዞን በጌታ ወረዳ ሰነንና ቆረፍቻ ቀበሌ የሚገኘው ውቡ "የበኬ ጀፎረ" ለዘመናት በአካባቢው ማህበረሰብ ተጠብቆ ለአካባቢው ማህበረሰብም ግልጋሎት እየሰጠ ያለ ውብ ጀፎረ ነው።

በወረዳው የሰነንና ቆረፎቻ ቀበሌ የበኬ መንደር ነዋሪ ከሆኑት አቶ ታደሰ ደምስስ እና አቶ ኢብራሂም ሀይደር በበኩላቸው፤ ጀፎረን ከቀደምት ጥበበኛ አባቶች የወረስነው እና ዛሬም የምንኖርበት ታላቅ ቅርሳችን ነው ብለውታል።

ጀፎረ ትንሹም፣ ትልቁም የማኅበረሰብ ክፍል ያለምንም ልዩነት በእኩልነትና በጋራ የመጠቀም መብት የሰጠ በመሆኑም የፍትህና የእኩልነት ምልክት ነው።

የዳኝነት ሥርዓቶች የሚከወኑበት፣ ውይይትና ምክክር የሚደረግበት ፣ የተጣሉ ነዋሪዎች የሚታረቁበት በመሆኑም የጥል ማስወገጃ፣ የሰላም ማንበሪያ ሥፍራ ነው ሲሉ ገልጸውታል።

ስለሆነም ጀፎረ ከህይወታችን የተቆራኘ በመሆኑ በቂ እንክብካቤና ጥበቃ እያደረግንለት የምንገኘው ሲሉ አብራርተዋል።

በአሁኑ ሰዓት እየተሰራ ያለው የገጠር ኮሪደር ልማት ሥራ ባህልን ከማስጠበቅ ባለፈ ንጹህና ጽዱ አካባቢን ለማጠናከር ያለው ፋይዳ ጉልህ በመሆኑ ሥራው እንዲፋጠን የበኩላቸውን እየተወጡ መሆኑን ተናግረዋል።

ሰፈራችን እንዳማረ ጎዳችንም በምግብ የተሟላ መሆን አለበት በሚል እሳቤ ተግባሩ ከሌማት ትሩፋት ጋር አስተሳስረው እየሰሩበት ይገኛል።

ሁሉም አርሶአደሮች በየ ቤታቸው ዝርያቸው የተሻሻሉ ከብቶ፣ዶሮ፣ማር እንዲሁም በተቀናጀ ግብርና ፍራፍሬ፣ የጓሮ አትክልትና ሌሎችም አቀናጅተው እየሰሩ መሆኑ ተናግረዋል።

ህገ-ወጥ የሆኑ አጥሮችን አፍርሶ በማስተካከል፣ የምንጣሮና የቁጥቋጦ ስራ በማከናወን ወጥ የእንጨት አጥር ማጠራቸው አመላክተዋል።

የገጠር ኮሪደር ልማት ስራው ለአከባቢያቸው ልዩ ገጽታ እንዳላበሰው ገልፀው ስራው ተጨማሪ እድል ይዞ በመምጣቱ ቀጣይም የበኩላቸውን ለመወጣት እንደሚጥሩም ገልፀዋል።

በየጊዜው ጀፎረን በማጽዳትና በማስዋብ አካባቢው ለመኖሪያነት ምቹ አድርጎላቸዋል።

ዛሬ ጀፎረን በመጠበቅና በማልማት የተጀመረው ልምድ እሴት ሆኖ ለትውልድ እንዲተላለፍ ሁሉም ኃላፊነቱ መወጣት ይኖርበታል።

🖍️ Gurage zone government communication affairs

የጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ አርሽያ አህመድ የስራ ርክክብ አደረጉጥቅምት 28/2019(ወልቂጤ)የጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ አርሽያ አህመድ ከቀድሞው ከ...
07/11/2026

የጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ አርሽያ አህመድ የስራ ርክክብ አደረጉ

ጥቅምት 28/2019(ወልቂጤ)

የጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ አርሽያ አህመድ ከቀድሞው ከመምሪያው ኃላፊ ወይዘሮ መሰረት አመርጋ የስራ ርክክብ አድርገዋል።

የጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ አርሽያ አህመድ እንዳሉት በዞኑ በባህልና ቱሪዝም ዘርፍ የተጀመሩ ስራዎችን በላቀ መልኩ ለማስቀጠል ይሰራል።

የዞኑ ማህበረሰብ ጎልተው ያልወጡ ሰፊ የባህል እሴቶች ያሉት መሆኑን ገልፀው ለዚህም በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

በመንግስት ልዩ ትኩረት የተሰጠው የቱሪዝም ዘርፉ ለዞኑ የኢኮኖሚ አቅም ሆኖ እንዲያገለግል ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራም ተናግረዋል።

ኃላፊዋ ከዚህ ቀደም መምሪያውን ሲመሩ ለነበሩት ለወይዘሮ መሰረት በማመስገን በቀጣይ በተሰጧቸው የስራ ኃላፍትና መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው ተመኝተውላቸዋል።

ወይዘሮ መሰረት አመርጋ በበኩላቸው በተቋሙ በነበራቸው ቆይታ አብሯቸው ለሰሩና ድጋፍ ላደረጉላቸው አካላት በሙሉ በማመስገን በቀጣይም ዞኑ በዘርፉ ለሚሰራቸው ስራዎች ለማገዝ ዝግጁ መሆናቸውን አብራርተዋል።
🖍️ Gurage zone government communication affairs

05/11/2026
05/11/2026
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የድጋፍና ክትትል ቡድን በጉራጌ ዞን በመገኘት የ2019 ዓ.ም የ1ኛ ሩብ ዓመት ድጋፍና ክትትል አደረገ። ጥቅምት 26/2019 ዓ.ምየማዕከላዊ ኢ...
05/11/2026

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የድጋፍና ክትትል ቡድን በጉራጌ ዞን በመገኘት የ2019 ዓ.ም የ1ኛ ሩብ ዓመት ድጋፍና ክትትል አደረገ።

ጥቅምት 26/2019 ዓ.ም

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ያሰማሯቸዉ የድጋፍና ክትትል ቡድን በጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ የ2019 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት የሥራ እንቅስቃሴ ላይ የተመሰረተ የድጋፍና ክትትል ምልከታ አካሂዷል።

04/11/2026

በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ለወልቂጤ ከተማ ልማትና ዕድገት የሚደረገው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው፦ወይዘሮ ስሜነሽ ግርማ

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት በከተማዋ የሆቴልና የቱሪዝም ዘርፍ እንዲስፋፋ፣ የከተማዋ የባህልና ቱሪዝም ሀብቶች ተጠብቀው ለኢኮኖሚያዊ ዕድገት እንዲውሉ እንዲሁም ከተማዋ ያላትን የቱሪዝም አቅም በማሳደግ የጎብኚዎች መዳረሻ እንድትሆን የተለያዩ የልማትና የማስተዋወቅ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል።

የሆቴልና የቱሪዝም ዘርፍ ለከተማዋ የኢኮኖሚ ዕድገት፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ለገቢ ማሳደግና ለከተማዋ ገጽታ ግንባታ የላቀ ሚና አለው።

ዘርፉ በተለይም ለሆቴሎች፣ ለምግብ ቤቶች፣ ለትራንስፖርት፣ ለባህላዊ ምርቶችና ለሌሎች ተያያዥ የንግድ እንቅስቃሴዎች መስፋፋት አስፈላጊ ድርሻ ይኖረዋል።

ጽሕፈት ቤቱ በዘርፉ የሚንቀሳቀሱ ባለሀብቶችንና አገልግሎት ሰጪዎችን በማበረታታት፣ የአገልግሎት ጥራትን በማሻሻል፣ የባህል እሴቶችን በመጠበቅና የከተማዋን የቱሪዝም ሀብቶች በማስተዋወቅ ዘርፉ የበለጠ ውጤታማ እንዲሆን ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ነው።

ወይዘሮ ስሜነሽ ግርማ እንደገለጹት፣ የሆቴልና የቱሪዝም ዘርፍ ዕድገት የመንግሥትን ብቻ ጥረት የሚጠይቅ ሳይሆን የግሉ ዘርፍ፣ የአካባቢው ማኅበረሰብና ሁሉም የልማት አጋሮች የጋራ ተሳትፎን የሚሻ እንደሆ ተናግረዋል።

በዚህ ረገድ በወልቂጤ ከተማ ያለውን የቱሪዝም አቅምና ተጨባጭ የኢንቨስትመንት ዕድሎች በመመልከት የግሉ ዘርፍ በሎጅ፣ በዘመናዊ ሆቴሎችና በተለያዩ የቱሪዝም መስህቦች ልማት ላይ ኢንቨስት እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

ይህም የጎብኚዎችን ቆይታ ለማራዘም፣ የአገልግሎት አቅምን ለማሳደግና ከተማዋን ተመራጭ የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ የራሱን አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለዋል።

ወልቂጤ ከተማ በባህል፣ በታሪክና በተፈጥሮ ሀብቶች ያላትን አቅም ወደ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ለመቀየር በሎጅና በሆቴል ግንባታ፣ በመዝናኛ ማዕከላት፣ በባህላዊ መዝናኛና በቱሪስት ማረፊያዎች ላይ የሚደረግ ኢንቨስትመንት ወሳኝ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ባለሀብቶች በዘርፉ የሚያከናውኑት ኢንቨስትመንት የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባለፈ የአካባቢውን ምርቶችና አገልግሎቶች ገበያ እንዲያገኙ ያግዛል ብለዋል።

በተጨማሪም የግሉ ዘርፍ በዚህ የኢንቨስትመንት አቅጣጫ እንዲሳተፍ በማስተባበርና በትብብር መሥራት አስፈላጊ መሆኑን ያመለከቱት ኃላፊዋ፣ የከተማዋን የቱሪዝም እምቅ አቅም በማስተዋወቅ፣ የኢንቨስትመንት ዕድሎችን በማሳየትና ለባለሀብቶች ምቹ የሆነ የትብብር ሁኔታ በመፍጠር ዘርፉን ለማስፋፋት ጽሕፈት ቤቱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሠራ ገልጸዋል።

በመሆኑም የቱሪዝም ሀብቶችን መጠበቅ፣ የከተማዋን ጽዳትና ውበት ማስጠበቅ፣ ለጎብኚዎች ተስማሚ አገልግሎት ማቅረብና አዳዲስ የቱሪዝም አቅሞችን ማልማት የሁሉም ድርሻ መሆን እንዳለበት አሳስበዋል።

በመጨረሻም የወልቂጤ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት የከተማዋን የባህልና ቱሪዝም ሀብቶች ለዕድገት በማዋል፣ ከግሉ ዘርፍ ጋር በትብብር በመሥራትና የሆቴልና ቱሪዝም አገልግሎቶችን በማሻሻል ከተማዋን ለነዋሪዎችና ለጎብኚዎች ምቹ፣ ማራኪና የኢኮኖሚ ዕድገት ተምሳሌት ለማድረግ የሚያደርገውን ጥረት እንደሚያጠናክር ተናግረዋል።

ወልቂጤ ከተማን በባህልና ቱሪዝም ሀብቷ እናሳድግ፤ በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ የኢኮኖሚ ዕድገትን በጋራ እናፋጥን!

 #ጊችን ፏፏቴበማዕከላዊ ኢትዮጵያ በጉራጌ ዞን እኖር ኤነር መገር ወረዳ በርካታ ተፈጥሮአዊ፣ ሰው ሰራሽ ታሪካዊና ሃይማኖታዊ መስህቦች መገኛ ባለቤት ነች።በወረዳው ከሚገኙ ድንቅ የተፈጥሮ መስ...
04/11/2026

#ጊችን ፏፏቴ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ በጉራጌ ዞን እኖር ኤነር መገር ወረዳ በርካታ ተፈጥሮአዊ፣ ሰው ሰራሽ ታሪካዊና ሃይማኖታዊ መስህቦች መገኛ ባለቤት ነች።

በወረዳው ከሚገኙ ድንቅ የተፈጥሮ መስህቦች ስፍራዎች ውስጥ አንዱ የሆነውን #ጊችን ፏፏቴ ነው።

ፏፏቴው ልዩ ከሚያደርጉት መካከል፡-ፏፏቴው በተፈጥሮ ድንጋይ የተከበበ መሆኑንና በፏፏቴው ዙሪያ የሚገኙ የተፈጥሮ ደኖች ለፏፏቴዉ ልዩ ድምቀት የሰጡ መሆናቸው፡፡

ፏፏቴው በተፈጥሮ ደን የተከበበ መሆኑና በደኑ ውስጥ ደግሞ የተለያዩ ዕድሜ ጠገብ የሆኑ አገር በቀል ዛፎች ይገኙበታል፡፡

ፏፏቴው የወረደው ውሀ ታች መሬት ላይ ተንሳፎ ሲታይ እጅግ ማራኪ ገፅታ አለው፡፡

ይህንን ውብ ስፍራ እንድትጎበኙ ግብዣችን ነው ::

📌 የእኖር ኤነር መገር ወረዳ መንግስት ኮምኒኬሽን

ፏን ፏፏቴን ይጎብኙ 🙏በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ውስጥ ጥቂት ፏፏቴዎች የሚገኙ ሲሆን ከነዚህ ፏፏቴዎች መካከል በማራኪነቱና በግዝፈቱ ግንባር ቀደም ...
04/11/2026

ፏን ፏፏቴን ይጎብኙ 🙏

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ውስጥ ጥቂት ፏፏቴዎች የሚገኙ ሲሆን ከነዚህ ፏፏቴዎች መካከል በማራኪነቱና በግዝፈቱ ግንባር ቀደም የሆነው ፏን ፏፏቴ ነው።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
እኛም ይህንን ተፈጥሮዊ ፏፏቴ በወፍ በረር በምናብ በአጭሩ የምናስቃኛቹ ይሆናል መልካም ቅኝት ይሁንላቹ፦

ይህ ፏፏቴ በወረዳው ጠይባና ዋቦን ቀበሌ ወሠን ላይ ይገኛል።

የፏን ፏፏቴ ከቆቼ ተራራ ቁልቁል እየተምዘገዘገ ሲውርድ ለስተዋለው ነፍስን በሀሴት ይሞላል ።
ፏፏቴው ጥርት ያለና ድምቀት ያለው ነው ድምጹ ግርማ ሞገስ ያለው ከመሆኑ በተጨማሪ ቁልቁል እየተመዘገዘገ ሲወርድ የሚፈጥረው ጢስ መሠል ነገር ሌላው የፏፏቴው ማራኪ ገጽታ ነው።

ይህ ፏፏቴ ርዝመቱ በግምት 45 ሜትር ይሆናል።
ታዲያ ይህ ፏፏቴ ከማራኪነቱና ግርማ ሞገሱ ጋር ሊያገኙት የሚችሉት በክረምት ወራት ውስጥ ነው።
በበጋ ወራት የውኃው መጠን ስለሚቀንስ በአንጻራዊነት ድምቀቱ እንደሚቀንስ የአካባቢው ነዋሪዎች ይገልጻሉ።

መረጃውን ያገኘነው ከገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳው ባህል ቱሪዝም ጽ/ቤት ነው።

‎ቱሪዝም የኢኮኖሚያችን አንዱ ምሰሶ እንደመሆኑ፣ የሀገራዊ ዕድገታችንን የወደፊት አቅጣጫ እየቀረጸ ያለ ዘርፍ መሆኑን እያስመሰከረ ነው!ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)  #ኢትዮጵያ  ...
01/11/2026

‎ቱሪዝም የኢኮኖሚያችን አንዱ ምሰሶ እንደመሆኑ፣ የሀገራዊ ዕድገታችንን የወደፊት አቅጣጫ እየቀረጸ ያለ ዘርፍ መሆኑን እያስመሰከረ ነው!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ

Address

Gurage
Wolkite
GOVERNMENTORGANIZATION

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
19:00 - 19:00
Tuesday 09:00 - 18:30
19:00 - 20:00
Wednesday 09:00 - 18:30
19:00 - 19:00
Thursday 09:00 - 18:30
19:00 - 20:00
Friday 09:00 - 18:30
19:00 - 20:00
Saturday 03:00 - 02:45

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gurage Zone Culture and Tourism posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Gurage Zone Culture and Tourism:

Shortcuts

Share

Nearby government services