Gurage Zone Government Communication Affairs Department

Directions Website Contact the organization

Gurage Zone Government Communication Affairs Department We work hard to build an informed society by providing hot and hard news, articles and documentary films!

የጉራጌ ሕዝብ መገለጫ የሆነው ጀፎረ በመጠበቅና በማልማታችን አካባቢያችን ለኑሮ ምቹና ማራኪ ሆኖልናል፦በጌታ ወረዳ የበኬ መንደር ነዋሪዎችጥቅምት 30/2019(ወልቂጤ)ጀፎረ የጉራጌ ሕዝብ ከትው...
09/11/2026

የጉራጌ ሕዝብ መገለጫ የሆነው ጀፎረ በመጠበቅና በማልማታችን አካባቢያችን ለኑሮ ምቹና ማራኪ ሆኖልናል፦በጌታ ወረዳ የበኬ መንደር ነዋሪዎች

ጥቅምት 30/2019(ወልቂጤ)

ጀፎረ የጉራጌ ሕዝብ ከትውልድ ወደ ትውልድ እያስተላለፈ ካቆያቸው ውብ ባህላዊ እሴቶች መካከል ተጠቃሽ ነው።

በአንድነት፣ በመተጋገዝና በትብብር ላይ የተመሠረተው ጀፎረ ሰዎች የአንዱን ችግር እንደራሳቸው በመመልከት በጋራ መፍትሔ የሚፈልጉበት፣ ለጋራ ጥቅምም በአንድነት የሚተጉበት የማኅበራዊ አኗኗር መገለጫ መሆኑ ይነገራል።

ይህ እሴት የጉራጌ ሕዝብ የመተሳሰብ፣ የመደጋገፍና የአብሮነት መሠረት ከመሆኑም በላይ በዘመናዊ ማኅበረሰብ ግንባታ ውስጥም ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።

ጀፎረ ሰዎችን በጋራ ዓላማ የሚያስተሳስር፣ የመተጋገዝ ባህልን የሚያጠናክርና ለትውልድ መልካም አርዓያ የሚሆን የጉራጌ ሕዝብ ውድ ባህላዊ ሀብት ነው።

በዘመናት ዑደት ውስጥ ከነግርማ ሞገሱ የተሻገረ የጉራጌ መንደሮች ባህላዊ ጎዳና፣ የትውፊታዊ ትዕይንቶች መድረክ ሲሆን የሀገር በቀል ዕውቀትና ጥበብ ማሳያ ምዕተ- ዓመታት የተሻገረ የትውልድ ቅርስም ነው ጀፎረ!

በአባቶች ጥበብ የተሰራ ጀፎረ ከሥራ ወዳዱ የጉራጌ ጥንተ-ማኅበረሰብ ዘንድ በንግድ እንቅስቃሴ ሂደት ተወጥኖ ከወትሮ እስከ ዘንድሮ ዘልቋል።

ጀፎረ ውበትና ጌጥ ብቻ አይደለም። ትውፊታዊ መልክና ግልጋሎቱ ፈርጀ-ብዙ ነው። በዘፈቀደ የሚሰመር ሳይሆን የራሱ የአሰማመርና የልኬት ስልት እንዳለው ይነገራል።

እናም ጀፎረ ተራ ጎዳና ሳይሆን የአካባቢው ተወላጆች ከልጅነት እስከ ዕውቀት ማንነት የሚቀረጽበት የሕይወት ጎዳና ነው።

በጉራጌ ዞን በጌታ ወረዳ ሰነንና ቆረፍቻ ቀበሌ የሚገኘው ውቡ "የበኬ ጀፎረ" ለዘመናት በአካባቢው ማህበረሰብ ተጠብቆ ለአካባቢው ማህበረሰብም ግልጋሎት እየሰጠ ያለ ውብ ጀፎረ ነው።

በወረዳው የሰነንና ቆረፎቻ ቀበሌ የበኬ መንደር ነዋሪ ከሆኑት አቶ ታደሰ ደምስስ እና አቶ ኢብራሂም ሀይደር በበኩላቸው፤ ጀፎረን ከቀደምት ጥበበኛ አባቶች የወረስነው እና ዛሬም የምንኖርበት ታላቅ ቅርሳችን ነው ብለውታል።

ጀፎረ ትንሹም፣ ትልቁም የማኅበረሰብ ክፍል ያለምንም ልዩነት በእኩልነትና በጋራ የመጠቀም መብት የሰጠ በመሆኑም የፍትህና የእኩልነት ምልክት ነው።

የዳኝነት ሥርዓቶች የሚከወኑበት፣ ውይይትና ምክክር የሚደረግበት ፣ የተጣሉ ነዋሪዎች የሚታረቁበት በመሆኑም የጥል ማስወገጃ፣ የሰላም ማንበሪያ ሥፍራ ነው ሲሉ ገልጸውታል።

ስለሆነም ጀፎረ ከህይወታችን የተቆራኘ በመሆኑ በቂ እንክብካቤና ጥበቃ እያደረግንለት የምንገኘው ሲሉ አብራርተዋል።

በአሁኑ ሰዓት እየተሰራ ያለው የገጠር ኮሪደር ልማት ሥራ ባህልን ከማስጠበቅ ባለፈ ንጹህና ጽዱ አካባቢን ለማጠናከር ያለው ፋይዳ ጉልህ በመሆኑ ሥራው እንዲፋጠን የበኩላቸውን እየተወጡ መሆኑን ተናግረዋል።

ሰፈራችን እንዳማረ ጎዳችንም በምግብ የተሟላ መሆን አለበት በሚል እሳቤ ተግባሩ ከሌማት ትሩፋት ጋር አስተሳስረው እየሰሩበት ይገኛል።

ሁሉም አርሶአደሮች በየ ቤታቸው ዝርያቸው የተሻሻሉ ከብቶ፣ዶሮ፣ማር እንዲሁም በተቀናጀ ግብርና ፍራፍሬ፣ የጓሮ አትክልትና ሌሎችም አቀናጅተው እየሰሩ መሆኑ ተናግረዋል።

ህገ-ወጥ የሆኑ አጥሮችን አፍርሶ በማስተካከል፣ የምንጣሮና የቁጥቋጦ ስራ በማከናወን ወጥ የእንጨት አጥር ማጠራቸው አመላክተዋል።

የገጠር ኮሪደር ልማት ስራው ለአከባቢያቸው ልዩ ገጽታ እንዳላበሰው ገልፀው ስራው ተጨማሪ እድል ይዞ በመምጣቱ ቀጣይም የበኩላቸውን ለመወጣት እንደሚጥሩም ገልፀዋል።

በየጊዜው ጀፎረን በማጽዳትና በማስዋብ አካባቢው ለመኖሪያነት ምቹ አድርጎላቸዋል።

ዛሬ ጀፎረን በመጠበቅና በማልማት የተጀመረው ልምድ እሴት ሆኖ ለትውልድ እንዲተላለፍ ሁሉም ኃላፊነቱ መወጣት ይኖርበታል።

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ከ6 ሚልዮን 517 ሺህ ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የአንድ ከተማ አንድ ፕሮጀክት አካል የሆነው የዳርቻ ዝግባቦቶ ማዘጋጃ ቤት የቢሮ ግንባታ ተመርቆ ለአገልግሎት ...
09/11/2026

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ከ6 ሚልዮን 517 ሺህ ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የአንድ ከተማ አንድ ፕሮጀክት አካል የሆነው የዳርቻ ዝግባቦቶ ማዘጋጃ ቤት የቢሮ ግንባታ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ።

ጥቅምት 30/2019 ዓ.ም(ወልቂጤ) በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ከ6 ሚልዮን 517 ሺህ ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የአንድ ከተማ አንድ ፕሮጀክት አካል የሆነው የዳርቻ ዝግባቦቶ ማዘጋጃ ቤት የቢሮ ግንባታ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ።

የቢሮ ግንባታው መጠናቀቅ በከተማው ለህብረተሰቡ ነጻና ፍትሃዊ አገልግሎት በመስጠት ተጠቃሚ ለማድረግ ፋይዳው ከፍተኛ መሆኑንም ተመላክቷል።

የጉራጌ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ምክትልና የማስፈጸም ዘርፍ ኃላፊ አቶ ክንፈ ሀብቴ እንዳሉት በዞኑ የሚገኙ ከተሞች ጉራጌን በሚመጥን መልኩ በማሳደግ ህዝቡን ተጠቃሚ ለማድረግ መስራት ይገባል።

ዳርቻ ዝግባቦቶ በዞኑ እውቅና ከተሰጣቸው 40 ከተሞች አንዱ ነው ያሉት አቶ ክንፈ በ2017 ዓ.ም የማዘጋጃ ቤት እውቅና ካገኘ ወዲህ በከተማው ማህበረሰቡና መንግስት በቅንጅት የተሰሩ የልማት ስራዎች አበረታች ናቸው።

በከተማው የተጀማመሩ የልማት ስራዎችን በማጠናከር ከተማዋ ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግ የበለጠ መስራት እንደሚገባም ገልጸዋል።

ታዳጊ ከተማዋ በሚፈለገው ልክ እንድታድግ በፕላን መሰረት መምራት እንደሚገባ አውስተው ከዚህም ባለፈ መንግስት ነዋሪውና ባለሀብቱ በማስተባበር ህዝቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ስራዎችን መስራት ይገባል ብለዋል።

በ2018 በዞኑ በአንድ ከተማ አንድ ፕሮጀክት 37 ፕሮጀክቶችን መገንባት መቻሉን የገለጹት ኃላፊው የዝግባቦቶ ዳርቻ ከተማ ግንባታ የዚሁ አንድ አካል መሆኑንም ተናግረዋል።

በ2019 በጀት አመት በዞኑ በ33 ከተሞች በ4 መቶ 61 ሚሊዮን 260 ሺህ ብር 43 ፕሮጀክት ለመገንባት መታቀዱንም አንስተው እነዚህ ፕሮጀክቶችን ለማሳካት ማህበረሰቡና ባለሀብቱ በማሳተፍ ርብርብ ማድረግ ይጠበቅብናል ብለዋል።

ከተሞች ለነዋሪዎች ምቹ፣ ሳቢና ተስማሚ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ሁሉም የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንዳለበትም አስገንዝበዋል።

የእዣ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተጠምቀ በርጋ በበኩላቸው፥ የዳርቻ ዝግባቦቶ ማዘጋጃ ቤት የቢሮ ግንባታ የቢሮ አገልግሎት ከመስጠቱ ባለፈ የማህበረሰብ የጋራ ጥረት፣ የመንግስት ቁርጠኝነትና የማዘጋጃ ቤቱ የልማት ምልክት ነው ብለዋል።

ይህ ቢሮ ለስራ አስፈጻሚዎች ምቹ የስራ ቦታ ከመፍጠር በተጨማሪ ለህዝቡ ፈጣን፣ ፍትሃዊና ተገቢውን ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ፋይዳው ከፍተኛ መሆኑንም አመላክተዋል።

አዲስ ተገንብቶ የተመረቀው የቢሮ ግንባታ በመጠበቅ በተገቢው መጠቀምና ለህዝብ ጥቅም ማዋል እንደሚገባም አንስተው በዚህ ግንባታ ላይ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

የእዣ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌታቸው አየለ እንደገለጹት በወረዳው የአንድ ከተማ አንድ ፕሮጀክት አካል የሆነው የዳርቻ ዝግባቦቶ የቢሮ ግንባታ በ6 ሚልዮን 517 ሺህ 510 ብር ወጪ መገንባቱንም ገልጸዋል።

ይህ የቢሮ ግንባታ በ2መቶ 10ካ.ሜ ላይ ያረፈ ሲሆን ለዚህ ግንባታ ከነጋዴው ከአርሶ አደር፣ ከነዋሪው ሀብት በመሰብሰብ መገንባቱን ጠቅሰው፤ በቀጣይም የከተማው ልማት ይበልጥ ለማረጋገጥ ስራዎች እንደሚሰራም አመላክተዋል።

ነዋሪዎችን በማሳተፍ ከ8ኪ.ሜ በላይ የጠጠር መንገድ ግንባታና ከ5መቶ ሜትር በላይ የመንገድ አካፋዮች ማልማት ተችሏል ነው ያሉት።

የዳርቻ ዝግባቦቶ ማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ታፈሰ ሳርሄ ማዘጋጃ ቤቱ ከተመሰረተ 2 አመታት እንዳስቆጠረ ጠቁመው፤ በዛሬው እለት ለማህበረሰቡ ተገቢውን አገልግሎት መስጠት የሚያስችል የቢሮ ግንባታ በማጠናቀቅ ማስመረቅ ተችሏል ብለዋል።

የቢሮ ግንባታ መጠናቀቅ ለህብረተሰቡ በነጻነት የሚፈልገውን አገልግሎት ለመስጠት ፋይዳው ከፍተኛ መሆኑን ያነሱት ስራ አስኪያጁ ይህ ማዘጋጃ ቤት ለማሳደግ ማህበረሰቡና መንግስት በመቀናጀት በቢሮ ግንባታ ላይ የተጀማመሩ ስራዎችን ይበልጥ ማስቀጠል እንደሚገባም ገልጸዋል።

ማዕድን በብዝኃዘርፍ የልማት ምልከታችን አንዱ ቁልፍ ዘርፍ ሆኖ ይቀጥላል።  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) #ኢትዮጵያ  #ትልቅሀገር  #ትልቅሕዝብ  #ታላቅርዕይ
09/11/2026

ማዕድን በብዝኃዘርፍ የልማት ምልከታችን አንዱ ቁልፍ ዘርፍ ሆኖ ይቀጥላል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ

የᎀሕር አክሊል ወረዳ ወባጀ ቤት አስራ አርበተኛ ማራ አስራ አርበተኘ ዘበን አምሳ ሑዌተነ መደበኛ ወባጀ ወሰክት ቈሺም።ጥርቅምት 30/2019 ዘበር (ወርቕጥየ) የᎀሕር አክሊል ወረዳ ወባጀ ቤ...
09/11/2026

የᎀሕር አክሊል ወረዳ ወባጀ ቤት አስራ አርበተኛ ማራ አስራ አርበተኘ ዘበን አምሳ ሑዌተነ መደበኛ ወባጀ ወሰክት ቈሺም።

ጥርቅምት 30/2019 ዘበር (ወርቕጥየ)

የᎀሕር አክሊል ወረዳ ወባጀ ቤት አስራ አርበተኘ ማራ አስራ አርበተኘ ዘበን አምሳም ሑዌተነ ወባጀ ወሰክት ቀረሺም።

ዮረዳዌ ወባጀ ቤት የኸልቅ አፈ የትኸበድሙ ጅላሉ ሸምሱ የማኛም አሰላናህሙም ነሁቸር ባሰለሙᎇ ግዝየ የቤሙኸማ ዮባጀ ቤት ቂጫ ቦጣ፣ ቦትኺታቴም ቦሰክት የኸልቅና የዲሞክራሲ፣የኬር፣ዮገሬት ያነኸማ በልማት ይጠቀምኸማ ዮባጀ ቤት ሜራ ልዕየኤ የኸነኸማ በነሁቸሮህና ያስተላለፈም ትኸን በኧካ ወባጀ ብንም ወረዳዌ ሸመነ በ2019 ቅርጥ ዘበን የቾችዮ ሜና ተምኳከርም ያፀድቋኸማ አበአጥ ጅላሉ ኦደሙም።

እንጓድም ᎇበባጀ ቤትዌ የትልያይሙ ወባጀ ነሸም ይጮቺኸማ አትምላከትሙም ወባጀዌ የኧረሺኸማ እትሔሙም።

ቦባጀ ቤትዌ የᎀሕር አክሊል ወረዳ የትኸተረ ቡር አራባሪና የዋጋ ይስወስቡቦ ሸመነ አላፊ አበቃጥ ምትኩ ገብሬ ፣ የወረዳዌ ወባጀ ቤት የኸልቅ አፍ የትኸበድሙ ጅላሉ ሸምሱ፣የᎀሕር አክሊል ወረዳ የዝፓና ሸመነ አላፊ አበአጥ አሰፋ ወልዴ ፣ ዮረዳዌ ያስተባብረም ዳነ፣ዮረዳዌ የእንም ሸመነ ቤት ዳነ፣ የቀበሌ ዳነ፣ ዮረዳዌ ወባጀ ሸመነ ኸልቅ፣ እንጎድም ይትምለከትኖ ኸልቅ ቦባጀዌ ተረከቦም።

መረጃዌ ያሰናነ የᎀሕር አክሊል ወረዳ የመንግስት አትራህቦት ሸመነው።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብሔረሰቦች ምክር ቤት 21ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ከህዳር 1 ቀን ጀምሮ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር አስታወቀ።ጥቅምት 30/2...
09/11/2026

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብሔረሰቦች ምክር ቤት 21ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ከህዳር 1 ቀን ጀምሮ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር አስታወቀ።

ጥቅምት 30/2019 ዓ.ም(ወልቂጤ) የምክር ቤቱ መግለጫ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል።

21ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል‹‹ በብዝኃነት የደመቀች በምክክር የፀናች ስልጡን ኢትዮጵያ› በሚል መሪ ሀሳብ ይከበራል፡፡

በዓሉ በክልላችን በሁሉም መዋቅሮች እና በ7ቱም የክልሉ ክላስተር ማዕከላት በተለያዩ ሁነቶች ከህደር-1 ጀምሮ በደማቅ ሁኔታ የሚከበር ይሆናል፡፡

በመሆኑም በዓሉን ለማክበር ሰፊ ዝግጅት ሲደረግ ቆይቷል፡፡ መነሻ ዕቅድ የማዘገጀት፣ አብይ ኮሚቴ ማቋቋምና ማፅደቅ፣ህገ-መንግስት አሰተምህሮ ላይ የአስልጠኞች ስልጠና መስጠት እና ከሁሉም ዞንና ልዩ ወረዳ እንዲሁም ከባለድርሻ ተቋማት ጋር የበዓሉን አከባባር በተመለከተ ተግባቦት መፍጠር ተችሏል፡፡

ህዳር 29 ቀን 1987 ዓ.ም የኢፌዲሪ ሕገ መንግስት የፀደቀበት ታሪካዊ ቀን ነው፡፡በአገራችን ታሪክ ብዝሃነትን በማስተናገድ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ሕገ መንግሥታዊ ዋስትና የተረጋገጠበት እለት ነው፡፡ በመሆኑም ህዳር 29 ቀን “የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን!” ሆኖ በተለያዩ ዝግጅቶች ሲከበር ቆይቷል፡፡

ዓላማውም ብዝሃነትን በማስተናገድም ሆነ ዲሞክራሲያዊ አገራዊ አንድነትን ከማረጋገጥ አንፃር የበዓሉ መከበር የሚኖረው ፋይዳ ከፍ ያለ በመሆኑ ነው፡፡

በዓሉ መከበሩ ለብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ባህላቸውን እንዲያስተዋውቁ እኩል እድል የፈጠረ፣ ለፍትህ፣ ነፃነትና ለዲሞክራሲ ስርዓት መከበርና መረጋገጥ በጋራ ጠንክረው እንዲሰሩ፣ በወንድማማችነት ላይ የተመሰረተ ሕብረብሄራዊ አንድነት እንዲጠናከር እና ሥር እንዲሰድ፣ የፌዴራል ሥርዓታችን፣ የብዝሃነት አያያዝና የዲሞክራሲ ባህል ግንባታ እንዲጎለብት እና እንዲጠናከር እንዲሁም የሕገ መንግስት አስተምሮ ሥራዎች መሰረት የጣለ ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል፡፡

በየደረጃው የሚከናወኑ የበዓሉ ሁነቶች አካታች፣ ሕዝባዊ፣ የተቀናጁና የበዓሉን መልዕክት የሚያስተላልፉ እንዲሆኑ ሁላችንም የበኩላችንን ድርሻ መወጣት ይጠበቅብናል።

የበዓሉ ዝግጅትና አከባበር ውጤታማ እንዲሆን የመንግሥት ተቋማት፣ የሕዝብ ተወካዮች፣ የሲቪል ማኅበራት፣ የሴቶችና የወጣቶች ማኅበራት፣ የባህልና የኪነ-ጥበብ ተወካዮች፣ የሚዲያ ተቋማትና ሌሎች አጋር አካላት በቅንጅትና በትብብር እንዲሰሩ ምክር ቤቱ ጥሪ አቅርቧል።

09/11/2026

ሳምንታዊ አበይት ዜናዎች በፎቶ

  ሳምንታዊ አበይት  ዜናዎችጥቅምት 30/2019 ዓ.ም(ወልቂጤ)  የወልቂጤ ጤና ጣቢያ ከሀገር አልፎ በአፍሪካ ምርጥ ጤና ጣቢያ እንዲሆን በትኩረት ይሰራል ሲሉ ዶ/ር አብድልቋድር ገልገሎ ገለ...
09/11/2026

ሳምንታዊ አበይት ዜናዎች

ጥቅምት 30/2019 ዓ.ም(ወልቂጤ)

የወልቂጤ ጤና ጣቢያ ከሀገር አልፎ በአፍሪካ ምርጥ ጤና ጣቢያ እንዲሆን በትኩረት ይሰራል ሲሉ ዶ/ር አብድልቋድር ገልገሎ ገለጹ።

የኢትዮጵያ መድሃኒትና የህክምና መሳሪያዎች አቅርቦት ባለስልጣን ዋና ኃላፊ ክቡር ዶ/ር አብድልቋድር ገልገሎ ጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ በመገኘት የወልቂጤ ጤና ጣቢያን ጉብኝት አድርገዋል።

የፍትህ ተቋማት ቅንጅታዊ አሰራር የህብረተሰቡን ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው ሲሉ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መብራቴ ወልደማርያም ገለጹ።

የጉራጌ ዞን የፍትህ ማሻሻያ አብይ ኮሚቴ የ2019 ዓ.ም የ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም የግምገማ መድረክ በወልቂጤ ከተማ አካሂዷል።

የዞናችን ህዝብ አቅምና የመልማት ፍላጎት እንደ እድል በመጠቀም ፓርቲው ያስቀመጣቸው ግቦች በአጭር ጊዜ እንዲሳኩ አመራሩ በቁርጠኝነት መስራት ይኖርበታል ሲሉ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ክብሩ ፈቀደ አስታወቁ።

ጽህፈት ቤቱ የ2019 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ አመት የፓርቲ ስራዎች አፈጻጸም የግምገማና በቀጣይ አቅጣጫ ዙሪያ የውይይት መድረክ በወልቂጤ ከተማ አካሂዷል።

በመንግስት ሀብትና ንብረት ላይ ብክነቶች እና የአሰራር ጥሰቶች እንዳይፈጠሩ የኦዲት ግኝት አስመላሽ ግብረሀይል ጠንካራ ስራ እንደሚጠበቅበት የጉራጌ ዞን ምክር ቤት አስታወቀ፡፡

የጉራጌ ዞን ምክር ቤት የ2019 በጀት አመት የኦዲት ግኝት አስመላሽ ግብረሀይል የንቅናቄ መድረክ በወልቂጤ ከተማ አካሄደ።

ዞናችን በስፖርት ዘርፍ ያለው አቅምና ጸጋን በአግባቡ በመጠቀም ማህበረሰቡን ሊመጥን የሚችል ውጤት እንዲመጣ በትኩረት ይሰራል ሲሉ አቶ መብራቴ ወ/ማርያም አስታወቁ።

የጉራጌ ዞን የስፖርት ምክር ቤት የ2018 በጀት አመት የስራ አፈጻጸም እና የ2019 እቅድ ላይ ውይይት ተካሂዷል።

በዞኑ ህዝቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ በመጀመሪያው መቶ ቀናት የተያዙ እቅዶች ሙሉ በሙሉ ለማሳካት ቅንጅታዊ አሰራርና የድጋፋዊ ክትትል ስራን ማጠናከር ይገባል ሲሉ አቶ አበራ ወንድሙ አስታወቁ።

የጉራጌ ዞን አስተዳደር የ2019 በጀት አመት የመጀመሪያ ዙር የ100 ቀናት እቅድ አፈፃፀም በወልቂጤ ከተማ ገመገመ።

ዜጎች በመንግስት ተቋማት ላይ እምነት እንዲኖራቸው ተቋማት በአሰራርና መመሪያ መሰረት ለተገልጋዩ ማህበረሰብ ቀልጣፋና ተገቢውን አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ ገለጸ።

በዞኑ የሚገኙ የግንባታ ፕሮጀክቶች በጥራት እና በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ ውስጥ በማጠናቀቅ ተገቢው አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ በትኩረት ሊሰራ ይገባል ሲል የጉራጌ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ አስታወቀ።

መምሪያው በጉራጌ ዞን ከ3 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር በላይ በሚሆን ወጪ በተለያዩ መዋቅሮች እየተገነቡ የሚገኙ የ60 የካፒታል ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ገመገመ።

የጉራጌ ዞን ብልጽግና ኢንስፔክሽንና ስነ - ምግባር ኮሚሽን የ2019 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በወልቂጤ ከተማ ገምግሟል።

"እኔ እያለሁ አንድም ምርት አይባክንም" በሚል መሪ ቃል ከማእከላዊ ኢትዩጵያ ክልል የተወጣጡ የስራ ኃላፊዎችና በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች በአበሽጌ ወረዳ የምርት አሰባሰብ ስራ አከናውኗል።

በጉራጌ ዞን በእንደጋኝ ወረዳ ደብረጽጌ ቀበሌ በአደይ ፕሮግራም በሴትና በወንድ ወጣቶች እየለማ ያለ የስንዴ ዘር ብዜት ተጎብኝቷል።

በዞኑ እዣ ወረዳ የሚገኙ እናቶች በእደ ጥበብ ስራቸው የአገናን ብቻ ሳይሆን በሀገሪቱ የተለያዩ ገበያዎችን የሚያስጌጡና በፈጠራ ልምዳቸው የሚታወቁ ሲሆኑ በቃጫና ስንደዶ ጥበብም አርአያ እየሆኑ ይገኛሉ።

የወጣቶች የስራ አጥነትን ችግር በመቅረፍ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸው በተጨባጭ ማረጋገጥ እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ስራና ክህሎት መምሪያ አስታወቀ።

በጉራጌ ዞን የግብርና ምርታማነትን በማሳደግ የአርሶአደሩ ተጠቃሚነት በተጨባጭ እየተረጋገጠ መሆኑ ተገለጸ።ጥቅምት 29/2019 ዓ.ም (ወልቂጤ)የጉራጌ ዞን ምክትል አሰተዳዳሪ አቶ አበራ ወንድሙ...
08/11/2026

በጉራጌ ዞን የግብርና ምርታማነትን በማሳደግ የአርሶአደሩ ተጠቃሚነት በተጨባጭ እየተረጋገጠ መሆኑ ተገለጸ።

ጥቅምት 29/2019 ዓ.ም (ወልቂጤ)

የጉራጌ ዞን ምክትል አሰተዳዳሪ አቶ አበራ ወንድሙና የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ፈቀደ በእንደጋኝ ወረዳ በዊሎ ፣ በደብረጽጌና በኤን ቀበሌዎች በኩታ ገጠም በስንዴ ሰብል እየለማ ያለ ማሳ የመስክ ምልከታ አካሄደዋል።

በመስክ ምልከታው የተገኙት የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ሀላፊ አቶ አበራ ወንድሙ እንዳሉት የዘንድሮ አመት የአየር ሁኔታው ለግብርና ስራ እጅግ ፈታኝ እንደነበረ አስታውሰው በተሰራው ጠንካራ ስራ ከሚጠበቀው በላይ ውጤት የመጣበት እንደሆነ አመላክተዋል።

ከተሰራ ሁሉም ነገር ማሳካት ይቻላል ብለው የዞኑ መሬት እንደየባህሪውና እንደየጸጋው ብንጠቀም ብዙ መልካም ነገሮች አሉት ያሉት ብለዋል።

አቶ አበራ አርሶአደሩ ከድህነት ለማውጣትና በሀገሪቱ ብልጽግና ለማረጋገጥ ከመቼውም ጊዜ በላይ አጽኖት ተሰጥቶት እየተሰራ እንደሆነም አብራርተዋል።

ሁሉም ተቀናጅቶ ከሰራ የምግብ ዋስትናችን በዘላቂነት ማረጋገጥ ይቻላል ያሉት ምክትል አስተዳዳሪው የኤክስፖርት ምርት በጥራትና በመጠን ማሳደግ እንደሚገባም አስረድተዋል።

በስንዴ ሰብል በስፋትና በጥራት ብንሰራ ኤክስፖርት የምናደርግበት አቅምና ጸጋው አለን ያሉት አቶ አበራ ከውጪ ወደ ሀገር ውስጥ የምናስገባቸው ሰብሎች እዚሁ ማምረት እንደሚገባም አሳስበዋል።

የግብርና ኢንደስትሪዎች የጥሬ እቃ አቅርቦት በተቀናጀና በተደራጀ መንገድ መስራት ከተቻለ አቅሙ ስላለ ለኢንደስትሪዎች በቂ የሆነ ምርት በጥራትም በመጠንም ቀጣይነት ባለው መንገድ ማቅረብ እንደሚቻልም ተናግረዋል።

በምንሰራቸው የግብርና ስራዎች ለወጣቶች የስራ ዕድል የሚፈጥርና ምርትና ምርታማነት እንዲያድግና እንዲዘምን በተማሩ ወጣቶች መመራት መቻል አለበት ያሉት ሀላፊው በዚህም በዞኑ በሁሉም አካባቢዎች በተሰራው ስራ ወጣት ወንድና ወጣት ሴቶች በስፋት ተጠቃሚ እየሆኑ ይገኛል ብለዋል።

በእንደጋኝ ወረዳ በደብረጽጌና ዊሎ ቀበሌዎች በወጣቶችና በሴቶች እንዲሁም በአርሶአደሮች በኩታ ገጠም በስንዴ ሰብል እየተሰሩ ያሉ ውጤታማ ስራዎች በሌሎችም አካባቢዎች ማስፋት እንደሚገባም አብራርተዋል።

የጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሀላፊና ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ደሳለኝ ፈቀደ እንዳሉት በዞኑ የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ እና የወጣቶች የስራ ዕድል ለመፍጠር በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነም አስረድተዋል።

የግብርና ምርቶች ለገበያ ለማቅረብ በአርሶአደሮች እና በወጣቶች በተለያዩ የግብርና ምርቶች ላይ መንግስት ልዩ ትኩረት በመስጠት ሰፋፊ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነም አስረድተዋል።

በዞኑ በዋና ዋና ሰብሎች ላይ በተለይ በበቆሎና በስንዴ፣ በጤፍና ገብስ ሰብሎች ላይ ውጤታማ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነም ያመላከቱት አቶ ደሳለኝ የግብርና ስራችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱም አብራርተዋል።

አብዛኛው የዞኑ አርሶአደሮች የብልጽግና ፓርቲ እንዲሁም የመንግስት አቅጣጫ ተቀብሎ ከመፈጸም አኳያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣ መሆኑና የአርሶአደሩ ምርትና ምርታማነት በተጨባጭ ለውጥ እየመጣ መሆኑም አብራርተዋል።

የእንደጋኝ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ክብሩ ዳርጊቾ እንዳሉት በወረዳው በ2018/2019 የመኸር ወቅት ላይ 8728 ሄክታር መሬት በተለያዩ ሰብሎች ማልማት እንደቻሉም አስረድተው ከዚህ ውስጥም70 በመቶው በስንዴ ሰብል እንደተሸፈነም አስረድተዋል።

ወረዳው ደጋ ከመሆኑ መነሻ ስንዴ ፣ አተር ፣ባቄላ ፣ገብስ የመሳሰሉ ሰብሎች የሚለሙ እንደህነም አብራርተው በዘንድሮ አመት 5 ሺህ 6 መቶ 36 ሄክታር መሬት ማሳ በስንዴ ማልማት እንደተቻለም አስረድተዋል።

ዘንድሮ በቁም ምርት ትመና ላይ በሄክታር ከ60 ኩንታል በላይ ምርት ሊገኝ እንደሚችል ያስረዱት የጽህፈት ቤት ሀላፊ በቀጣይ ተዛዙረው ያዩበት ደብረጽጌ ፣ዊሎና ኤን ቀበሌዎች ላይ የስንዴ ፖቴንሻል መኖሩም አስረድተው በወረዳው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምርጥ ዘር ድርጅት ፣የኤፍሳር ፕሮግራም ፣የአዴይ ፕሮግራምና ሌሎችም ፕሮግራሞች የወጣቶችና የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰሩ እንደሆነም ተናግረዋል።

በጉራጌ ዞን የእኖር ወረዳ ወጣቶች ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ዓላማ በመጠቀም በበጋ በጎ ፈቃድ ስራ የመጠለያ ችግር ላለባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ቤት እየገነቡ ነው!!ጥቅምት 29/2019(ወልቂጤ...
08/11/2026

በጉራጌ ዞን የእኖር ወረዳ ወጣቶች ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ዓላማ በመጠቀም በበጋ በጎ ፈቃድ ስራ የመጠለያ ችግር ላለባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ቤት እየገነቡ ነው!!

ጥቅምት 29/2019(ወልቂጤ)

በእኖር ወረዳ በተለያዩ ቀበሌያት የሚገኙ የመጠለያ ችግር ያለባቸው የማህበረሰብ ክፍሎች በበጎ ፍቃድ አገግሎት ተጠቃሚ እየሆኑ ይገኛሉ።

አስተማማኝ መጠለያ ማግኘት ለአንድ ቤተሰብ ጤና ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንደዚሁም ለተረጋጋ የሥነ-ልቦና ዕድገት ወሳኝ መሠረት ነው።

የመኖሪያ ችግር ውስጥ ለነበሩ ወገኖች ቤት መስራት በጎነት በተግባር የሚገለጽበት፣አንዱ የሰዎችን መሰረታዊ ፍላጎት የሚመልስና በማኅበረሰቡ መካከል ያለውን ፍቅርና አንድነት የሚያጠናክር ታላቅ ሥራ ነው።

በእኖር ወረዳ እገበኝ ቀበሌ ተወላጅ የኧዘአቴ
መንደር ወጣቶችም ይህንኑ የሚያጠናክር የበጎ ፍቃድ ስራ ሰርተዋል።

ወጣቶቹም ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ዓላማ በመጠቀም በበጎ ፈቃደኝነት ከፍተኛ የመጠለያ ችግር ውስጥ ለነበሩት አቶ ቶፊቅ ሙራድ መኖሪያ ቤት ገንብተዋል።

ለዚህ መልካም ተግባር መሳካት የአካባቢው ወጣቶችና ማህበረሰብ የገንዘብ፣ የቁሳቁስና የጉልበት ድጋፍ በማሰባሰብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርገዋል።

አቶ ቶፊቅ ለዓመታት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥና ተጎሳቁሎ በነበረ ጎጆ ቤት ውስጥ ከልጆቻቸውና ከቤተሰባቸው ጋር አንድ ላይ ይኖሩም ነበር።

ይኖሩበት የነበረው ያረጀና የተጎሳቆለ ጎጆ ቤት ለብርድ፣ ለዝናብና ለተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች የሚያጋልጣቸው ከመሆኑም በላይ ለሕይወታቸው አስቸጋሪ ደረጃ ላይ ደርሶ እንደነበርም የድጋፉ ተጠቃሚ ይናገራሉ።

አቶ ቶፊቅ ከነበሩበት አስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታና ከቤት መፈራረስ ስጋት ያወጧቸውን ወገኖቻቸው ሁሉ ከልብ አመስግነዋል።

በዚህ መልካም ተግባር ላይ የተገኙት የወረዳው ወጣቶችና ስፓርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ቸሩ ተካ እንዳሉት ይህ ስራ የወጣቱን የአንድነት ማህበራዊ ኃላፊነቱን ያሳየበት በመሆኑ በቀጣይም በአካባቢው የሚገኙ አቅመ ደካሞችንና ተመሳሳይ ችግር ያለባቸውን ወገኖች ለመደገፍ የጀመሩትን የደግነት ጉዞ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል ሲል የወረዳው የመንግስት ኮ/ጉ/ጽ/ቤት ዘግቧል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) በ28ኛው የጤናው ዘርፍ ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች‼ ✅ የመደመር መንግስት  የጤናው ዘርፍ ዘመኑን የ...
08/11/2026

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) በ28ኛው የጤናው ዘርፍ ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች‼

✅ የመደመር መንግስት የጤናው ዘርፍ ዘመኑን የዋጀ እንዲሆን ዘርፈ ብዙ ስራዎችን ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል።

✅ ሀገር አቀፍ የጤና ጉባኤው የጤናውን ዘርፍ ወደፊት የሚያራምዱ፣በሳል ውይይቶች እና የልምድ ልውውጦች ማካሄድ የሚያስችል ነው።

✅ ጉባኤው በመደመር መንግስት ምስረታ ማግስት እንደ አንድ ልብ መካሪ እና እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ በአንድ ገጽ ላይ የምንገኝበት ነው ።

✅ ወቅቱን የዋጀ የጤና ስርዓት ለመገንባት የጋራ ተግባቦት የምንፈጥርበት እና በዘርፉ ያለንን ዝግጁነታችንን የምናረጋግጥበት ነው ።

✅ ተለዋዋጭ እና ኢተገማች በሆነው አለም ዓቀፋዊ ሁኔታ ውስጥ በአሰራር፣በአደረጃጀት፣በሰው ሀይል የተጠናከረ የጤና ስርዓት መገንባት ያስፈልጋል።

✅ ጠንካራ የዘመነ ዲጂታል የጤና ስርዓት መፍጠር በዘርፉ የሚሰጠውን አገልግሎት ማማሻሻል ተገቢ ነው።

✅ የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግና እውን የሚሆነው አካላዊ እና አእምሯዊ ጤንነቱ የተጠበቀ ብቁና ንቁ ዜጋ ሲገነባ ነው።

✅ መንግስት የጤናው ዘርፍ ዘመኑን የዋጀ እንዲሆን እና ሀብረተሰባዊ እርካታን ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል።

✅ ቀደም ሲል ሲሰራበት የነበረውን የጤና ፖሊሲ በማዳበር በሽታን አስቀድሞ ከመከላከል ባሻገር አክሞ በማዳን ላይ እንዲያተኩር የተጀመረው ጥረት ውጤታማ ነው።

✅ ሁሉንም አይነት በሽታዎችን መከላከል እና መቆጣጠር የሚያስችል አቅም እየተፈጠረ ነው።

✅ በክልሉ ባለፉት ሶስት ዓመታት በጤናው ዘርፍ በርካታ ስራዎች ተግባራዊ ተደርጓል።

✅ በክልሉ የኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታሎችን ቁጥር ከአንድ ወደ 3 ከፍ ማድረግ ተችሏል።

✅ በክልሉ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች ቁጥር ከ19 ወደ 25 ከፍ ብሏል።

✅ የጤና ጣቢያዎች ቁጥር ከ219 ወደ 244 አድጓል።

✅ የኮምፕሬንሲቭ ጤና ኬላዎች ከስድስት ወደ 25 ማሳደግ ተችሏል።

✅ በክልሉ ሞዴል የማህበረሰብ መድሀኒት ቤቶች ከ5 ወደ 40 ማሳደግ ተችሏል።

✅ በክልሉ የጤና አገልግሎቶች ተደራሽነት እና ጥራት እየተሻሻለ መጥቷል።

#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ

Address

Wolkite

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gurage Zone Government Communication Affairs Department posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Gurage Zone Government Communication Affairs Department:

Shortcuts

Share