Amhara RoadTransport and Logistics Bureau

Directions

Amhara RoadTransport and Logistics Bureau Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Amhara RoadTransport and Logistics Bureau, Government Organization, Bahir Dar.

🌼 እንኳን ለመስቀል በዓል አደረሳችሁ! 🌼መስቀል የአንድነት፣ የተስፋ፣ የመተሳሰብና የሰላም በዓል ነው።መላው ህዝባችንን የሚያገናኙ የመንገድ እና የመጓጓዣ አውታሮችን በማልማት፣ የተሳለጠና ደ...
27/09/2026

🌼 እንኳን ለመስቀል በዓል አደረሳችሁ! 🌼

መስቀል የአንድነት፣ የተስፋ፣ የመተሳሰብና የሰላም በዓል ነው።

መላው ህዝባችንን የሚያገናኙ የመንገድ እና የመጓጓዣ አውታሮችን በማልማት፣ የተሳለጠና ደህንነቱ የተጠበቀ ትራንስፖርትን በማረጋገጥ እንዲሁም የሎጂስቲክስ ትስስራችንን በማጠናከር፣ የክልላችንን የልማት ጉዞ በጋራ እናፋጥን።

በዚህ የደስታ፣ የአንድነትና የተስፋ በዓል፣ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንዲሁም ለሁላችንም የሰላም፣ የጤና፣ የብልጽግናና የስኬት ዘመን እንዲሆን እመኛለሁ።

እንኳን ለመስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

ጋሻው አወቀ (ዶ/ር)
የአማራ ክልል መንገድ፣ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ቢሮ ኃላፊ

ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን በማስወገድ ለፕሮጀክቶች የጠራ አፈጻጸም የበኩላችንን እንወጣለን።****በአብክመ መንገድ፣ ትራንስፖርትና ሎጅስቲክ ቢሮ የገጠር ትስስር ለምግብ ዋስትና ፕሮግራም ለወረዳ...
25/09/2026

ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን በማስወገድ ለፕሮጀክቶች የጠራ አፈጻጸም የበኩላችንን እንወጣለን።
****
በአብክመ መንገድ፣ ትራንስፖርትና ሎጅስቲክ ቢሮ የገጠር ትስስር ለምግብ ዋስትና ፕሮግራም ለወረዳ አመራሮች፣ ባለሙያዎችና ለሚመለከታቸው አካላት የሚሰጠው ሙያዊ ስልጠና ቀጥሏል።

በስልጠናው የተሳተፉት ከስነምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የመጡት አቶ ይልቃል ወርቅነህ፣ ለፕሮጀክቶች የተመደቡ በጀቶች በአግባቡ ለታለመላቸው ዓላማ እየዋሉ መሆናቸውን መከታተልና በሂደቱ የሚከሰቱ ብልሹ አሰራሮችን መመርመር የሚመለከታቸው አካላት ዋና ተግባር መሆኑን ገልጸዋል።

ከማቴሪያል ግዥ ጀምሮ እስከ ርክክብ ድረስ ያሉ የፕሮጀክት ሂደቶች በአግባቡ መፈጸማቸውን መቆጣጠር፣ ከሙስና ጋር በተያያዙ ችግሮች ላይ ምርመራ ማድረግና ተገቢውን ውሳኔ ማስቀመጥ የሚጠይቅ ሂደት መሆኑንም አስረድተዋል።

አቶ ይልቃል አክለውም፣ ማንኛውም ስራ ከተጠያቂነት የማይነጣጠል መሆኑን በመገንዘብ፣ ፕሮጀክቶች በታቀደላቸው በጀት፣ የሰው ኃይል፣ ጊዜና ሌሎች አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎች መሠረት እንዲፈጸሙ እያንዳንዱ ባለድርሻ የበኩሉን ግዴታ መወጣት እንዳለበት አሳስበዋል።
ከሰልጣኞቹ መካከል የሰሜን ሜጫ ወረዳ መንገድ፣ ትራንስፖርትና ሎጅስቲክ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ስማቸው ላቀ፣ ፕሮግራሙ ወደ ወረዳው ከገባ ጀምሮ ለህዝቡ የነበሩ በርካታ የዘመናት ችግሮችን በመፍታት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ፕሮግራሙ ጠቃሚና አስተማሪ መሆኑን ጠቁመው፣ የፕሮግራሙን ውጤታማነት የሚያደናቅፉ ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን በመቃወም የበኩላቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።

ፕሮጀክቶችን በአግባቡ በማጠናቀቅ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት እናረጋግጣለን።****በአብክመ መንገድ፣ ትራንስፖርትና ሎጅስቲክ ቢሮ የገጠር ትስስር ለምግብ ዋስትና ፕሮግራም የታቀዱ የመንገድ ፕሮጀ...
25/09/2026

ፕሮጀክቶችን በአግባቡ በማጠናቀቅ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት እናረጋግጣለን።
****
በአብክመ መንገድ፣ ትራንስፖርትና ሎጅስቲክ ቢሮ የገጠር ትስስር ለምግብ ዋስትና ፕሮግራም የታቀዱ የመንገድ ፕሮጀክቶችን በታለመለት በጀትና የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ለማስፈጸም በእቅድ መመራትና ጠንካራ ክትትል ማድረግ ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ።

የፕሮግራሙ የእቅድ ክትትልና ግምገማ ባለሙያ አቶ አክሎግ ስዩም፣ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው እቅድ፣ በጀትና የጊዜ ሰሌዳ መሠረት እንዲፈጸሙ በተከታታይ መከታተል እንደሚገባ ገልጸዋል።
በቀጣይም በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎችን የመንገድ ተጠቃሚ ለማድረግ፣ የፕሮጀክቶችን ፊዚካል አፈጻጸም በመከታተል፣ የመረጃ አሰባሰብ ስልቶችን በማጠናከርና የችግሮችን አቀራረብና አፈታት አቅም በማሳደግ የሚጠበቀውን ውጤት ማስመዝገብ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በተጨማሪም የሪፖርት አያያዝና አቀራረብን በማጠናከር ለህዝብ ጥያቄዎች ወቅታዊና ተገቢ ምላሽ መስጠት እንደሚጠበቅ አቶ አክሎግ ጠቁመዋል።

በተለይም የፕሮጀክቶች አፈጻጸም ወቅታዊ እንዲሆን ተቋራጮችና አማካሪዎች በውላቸው መሠረት በወቅቱ ስራ እንዲጀምሩና እንዲፈጽሙ በየደረጃው የሚመለከታቸው አካላት ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ እንዳለባቸው በአፅንኦት አሳስበዋል።

ፕሮጀክቶችን በጥራት፣ በወቅቱና በታቀደው በጀት በማጠናቀቅ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት እናረጋግጣለን!






#ልማት

የገጠር ትስስር ለምግብ ዋስትና ፕሮግራም ለጎጃም ክላስተር አመራሮችና ባለሙያዎች የሙያዊ ስልጠና ተሰጠ፡፡****ባህር ዳር፣ መስከረም 14  2019 ዓ.ም — በአብክመ መንገድ፣ ትራንስፖርትና ...
25/09/2026

የገጠር ትስስር ለምግብ ዋስትና ፕሮግራም ለጎጃም ክላስተር አመራሮችና ባለሙያዎች የሙያዊ ስልጠና ተሰጠ፡፡
****
ባህር ዳር፣ መስከረም 14 2019 ዓ.ም — በአብክመ መንገድ፣ ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ቢሮ የገጠር ትስስር ለምግብ ዋስትና ፕሮግራም ለጎጃም ክላስተር የወረዳ አመራሮች፣ ባለሙያዎችና ለሚመለከታቸው አካላት ሙያዊ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

ስልጠናው በፕሮግራሙ የሚከናወኑ ፕሮጀክቶችን በተወሰነላቸው በጀትና የጊዜ ሰሌዳ መሠረት በጥራት ለማከናወን፣ የማሽነሪ አጠቃቀምና አስተዳደርን ለማሻሻል እንዲሁም በአፈጻጸም ሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመለየት ተገቢ መፍትሄ ለመስጠት የሚያግዙ ሙያዊ ጉዳዮችን ያካተተ ነው።

የፕሮግራሙ ማናጀር አቶ ኤርሚያስ መኳንንት በመክፈቻ ንግግራቸው ፕሮግራሙ ባለፉት ሁለት ዓመታት በርካታ አማካሪዎችንና ተቋራጮችን በማሳተፍ ፕሮጀክቶችን በተፈለገው መልኩ እያከናወነ መሆኑንና አበረታች ውጤቶችም መመዝገባቸውን ገልጸዋል።

አቶ ኤርሚያስ አክለውም ስልጠናው ፕሮጀክቶች በተወሰነላቸው በጀት፣ የጊዜ ሰሌዳና የጥራት መስፈርት መሠረት እንዲፈጸሙ ከማገዝ ባለፈ በአፈጻጸም ሂደት የሚከሰቱ ችግሮችን በወቅቱ በመለየት ለመፍታት አስፈላጊ አቅም እንደሚፈጥር ተናግረዋል።

ስልጠናውን እየሰጡ ያሉት ከከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሲኒየር መሐንዲስ አቶ ሚካኤል አምደ ሲሆኑ፣ የስልጠናው ሰነድ የፕሮግራሙን ወቅታዊ የአፈጻጸም ደረጃ፣ የቦታ መረጣ ሂደት፣ የውሳኔ አሰጣጥ አሠራርና የሪፖርት አዘገጃጀትን ጨምሮ ሌሎች ተያያዥ ሙያዊ ጉዳዮችን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል።

አቶ ሚካኤል እንደገለጹት፣ የገጠር ትስስር ለምግብ ዋስትና ፕሮግራም በቀጣይ ዓመታት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን የመንገድ ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ ሲሆን፣ ከተጠቃሚዎቹ ውስጥ 50 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች እንደሚሆኑ ገልጸዋል።

ለፕሮግራሙ ስኬታማ አፈጻጸም የሁሉም ባለድርሻ አካላት ቁርጠኝነትና ሙያዊ ኃላፊነት ወሳኝ መሆኑንም አቶ ሚካኤል አስገንዝበዋል። በተጨማሪም በፕሮግራሙ የሚገኙ መልካም ተሞክሮዎች ለሌሎች አካባቢዎችና ሀገራት ሊሰፉ በሚችሉበት መልኩ ሙያዊ አቅምን ማጠናከር እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ከስልጠናው ተሳታፊዎች መካከል በሰጡት አስተያየት ስልጠናው ልምድና ብቃት ባላቸው ባለሙያዎች መሰጠቱ በፕሮግራሙ የተካተቱ ተግባራትን በተሻለ አግባብ ለመፈጸም ጠቃሚ እንደሆነ ገልጸዋል።

ተሳታፊዎቹ መንገድ ለጤና፣ ለትምህርት፣ ለግብርናና ለሌሎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች የሚኖረውን ወሳኝ ሚና በመገንዘብ ተግባራቱን በቁርጠኝነት ለመፈጸም የሚያግዝ አቅም እንደጨመረላቸው ገልጸዋል።

በተጨማሪም ስልጠናው ቀጣይነት እንዲኖረው፣ የልምድ ልውውጥ እንዲጠናከርና በፕሮግራሙ የሚከናወኑ ተግባራት ያሉበትን ደረጃ በየጊዜው ለመፈተሽ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠር ጠይቀዋል።

18/09/2026

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
መንገድ፣ ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ቢሮ
🌟 እንኳን አደረሳችሁ! 🌟
በክልላችን የመንገድ፣ የትራንስፖርትና የሎጀስቲክስ ዘርፎች ልማትና ተደራሽነትን ለማሻሻል ከምንሠራው የዕለት ተዕለት ጥረት ጎን ለጎን፣ የአብሮነት፣ የመተሳሰብና የተስፋ መንፈሳችንን እንድናድስ የሚያደርጉ በዓላትን በደስታ እናከብራለን።
በዚህ ልዩ የደስታ አጋጣሚ፣ ለመላው የክልላችን ሕዝብ፣ ለተቋማት እና ለአጋር አካላት ከልብ የመነጨ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታችንን እናቀርባለን።
በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነትና የተስፋ ይሁንላችሁ። መጪው ዘመንም ለሁላችን የተሻለ እድገትና ብልጽግናን ያምጣ።
መልካም በዓል!
እንኳን አደረሳችሁ!
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
መንገድ፣ ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ቢ

"መሠረተ ልማትን የኢኮኖሚ ማሳለጫ ሞተር አድርጎ መምራት ይገባል" ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)***********በአማራ ክልል የመሠረተ ልማት ዝርጋታ የሚያከናውኑ ባለድርሻ ...
17/09/2026

"መሠረተ ልማትን የኢኮኖሚ ማሳለጫ ሞተር አድርጎ መምራት ይገባል" ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)
***********
በአማራ ክልል የመሠረተ ልማት ዝርጋታ የሚያከናውኑ ባለድርሻ ተቋማት በ2018 በጀት ዓመት የጋራ የዕቅድ ግምገማ እና በ2019 በጀት ዓመት የዕቅድ ትውውቅ ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል።

የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) በዚህ ወቅት እንደተናገሩት መሠረተ ልማት የማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ልማት መሠረት ነው። የመሠረተ ልማት ዘርፍ አገልግሎትን የሚያሳልጥ የዛሬ የልማት አሳላጭ የነገ ደግሞ አስቻይ የልማት ዕድል መሠረት ነው ብለዋል።

መሠረተ ልማት መንግሥት ለሕዝብ ቃል ኪዳን የገባቸውን ጉዳዮች ወደ ተጨባጭ አገልግሎት የሚቀይርበት መሳሪያ መኾኑንም ተናግረዋል።

በበጀት ዓመቱ የሚበረታታ የመሠረተ ልማት አፈጻጸም መመዝገቡንም ገልጸዋል። በመንገድ ጥገና፣ በድልድይ ግንባታዎች ሰፊ ሥራዎች መሠራታቸውንም አንስተዋል። በመጠጥ ውኃም ሽፋኑን መሻሻል ተችሏል ነው ያሉት።

በኤሌክትሪክ ኃይልም በሰብስቴሽን ግንባታዎች፣ በማስተላለፊያ መሥመሮች፣ በመልሶ ጥገና እና በተደራሽነት አበረታች ተግባራት መሠራታቸውን አንስተዋል።

በቴሌ አገልግሎትም በርካታ አዳዲስ ጣብያዎች እንዲከፈቱ በማድረግ እና የኔትወርክ ተደራሽነትን በማስፋፋት በኩል ሰፊ ሥራዎች ተከናውነዋል ነው ያሉት። ይህም ስማርት ከተሞችን የመፍጠር እና ለመጭው ጊዜ የዲጂታል ፋይናንስ ሥርዓት ዝግጁነትን ታሳቢ ተደርገው የተከናወኑ ውጤታማ ተግባራት መኾናቸውን አብራርተዋል።

በመሥኖ ልማት ፕሮጀክቶች የጥናት እና ዲዛይን ሥራዎችም የተሻለ አፈጻጸም ተመዝግቧል ነው ያሉት። በግንባታ ፕሮጀክቶችም ክትትል እና ቁጥጥር በማድረግ ከ7 በላይ ቆመው የነበሩ የግንባታ ፕሮጀክቶችን ወደ ሥራ ማሥገባት ተችሏል ነው ያሉት።

በበጀት ዓመቱ በተሻለ ደረጃ የተከናወኑ የመሠረተ ልማት አፈጻጸሞችን በማበረታታት፣ ክፍተት የታየበትን አፈጻጸም ደግሞ መፈተሽ እና በቆራጥነት ለማስተካከል መሥራት ያስፈልጋል ነው ያሉት።

በወረቀት ላይ ብቻ ያለ ዕቅድ ሕዝቡን አይጠቅምም ያሉት ምክትል ርእሰ መሥተዳድሩ ሕዝቡ ዕቅድ ብቻ ሳይኾን ውጤትም እንዲያይ እና ተጨባጭ ጥቅም እንዲያገኝ መሥራት አለብን" ነው ያሉት።

በ2019 በጀት ዓመት የመሠረተ ልማት ዘርፍ "ከዕቅድ ወደ ተግባር፣ የቆሙትን ፕሮጀክቶች ወደ ሥራ ማስገባት፣ ከዘገዩ ፕሮጀክቶች ወደ ፍጥነት፣ ከቃል ኪዳን ወደ ተጨባጭ ውጤት" የሚሉ መርሆዎችን በመከተል መሥራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል። ሰላም እና ልማትን አጀንዳነት በመያዝ በቁርጠኝነት መምራት እንደሚገባም አሳስበዋል።

"መሠረተ ልማትን የኢኮኖሚ ማሳለጫ ሞተር አድርጎ መምራት ይገባል" ብለዋል። መንገድን፣ መሥኖን፣ ኤሌክትሪክን፣ እና ሌሎችንም መሠረተ ልማቶች ለኢኮኖሚው ማሳለጫ አድርጎ በትኩረት መሥራት እንደሚገባም አሳስበዋል።

በበጀት ዓመቱ ለእያንዳንዱ ፕሮጀክት ባለቤት በመስጠት፣ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ተከታትሎ በመፍታት፣ ተጠያቂነትን በማረጋገጥ መምራት እንደሚያስፈልግም አስገንዝበዋል።

በዚህም ግልጽ እና አንድ ዓላማ በመያዝ በበጀት ዓመቱ ፕሮጀክቶች ከወረቀት ወደ መሬት፣ ወደ ማጠናቀቅ እና ወደ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚሸጋገሩበት ዓመት መኾን አለበት ብለዋል። ይህም ከሁሉም የመሠረተ ልማትን ከሚመሩ ተቋማት የሚጠበቅ ስለመኾኑም አሳስበዋል።

#አሚኮ #አማራክልል #ኢትዮጵያ

የኤሌክትሪክ ትራንስፖርት የኢንቨስትመንት ዕድሎች እንዲስፋፉ ሊሰራ እንደሚገባ ተገለጸ**** ከኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በተጨማሪ በኃይል መሙያ መሠረተ ልማት፣ በዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ በአምራች ኢ...
15/09/2026

የኤሌክትሪክ ትራንስፖርት የኢንቨስትመንት ዕድሎች እንዲስፋፉ ሊሰራ እንደሚገባ ተገለጸ
****
ከኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በተጨማሪ በኃይል መሙያ መሠረተ ልማት፣ በዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ በአምራች ኢንዱስትሪ፣ በጥገናና በክህሎት ልማት ላይ የኢንቨስትመንት ዕድሎችን ማስፋት እንደሚገባ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዶ/ር አለሙ ስሜ ገለጹ።

ሚኒስትሩ ይህን የገለጹት በሳይንስ ሙዚየም በተካሄደው የኖርዲክ–አፍሪካ ጉባኤ ላይ በመገኘት መልዕክታቸውን ባስተላለፉበት ወቅት ነው።

ወደ ኤሌክትሪክ ትራንስፖርት ሽግግሩ ተሽከርካሪዎችን ማብዛት ብቻ ሳይሆን የኃይል መሙያ መሠረተ ልማት፣ ዲጂታል ሥርዓት፣ አምራች ኢንዱስትሪ፣ ጥገናና የሰው ኃይል ክህሎትን በማሳደግ የተሟላ ሥነ-ምህዳር መፍጠር እንደሚጠይቅ አመልክተዋል።

ይህን ለማሳካት የመንግሥት ሀብት ብቻ በቂ ባለመሆኑ፣ ከልማት አጋሮች፣ ከንግድ ባንኮች፣ ከባለሀብቶችና ከኢንዱስትሪ ባለቤቶች ጋር ጠንካራ ትብብር መፍጠር እንደሚገባም ጠቁመዋል።

ሽግግሩ ሴቶችን፣ ወጣቶችንና አካል ጉዳተኞችን ያካተተ እና ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆን እንዳለበት የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ትኩረቱም በኤሌክትሪክ የሚሰሩ የብዙኃን ትራንስፖርትና በተቀናጀ ትራንስፖርት ላይ መሆን እንዳለበት አብራርተዋል።

በተጨማሪም ዘላቂ የኤሌክትሪክ ትራንስፖርት ለመገንባት ከዩኒቨርሲቲዎች፣ ከጥናት ማዕከላትና ከኢንዱስትሪዎች ጋር በመተባበር መሐንዲሶችን፣ ቴክኒሻኖችን፣ ተመራማሪዎችንና የፖሊሲ ባለሙያዎችን ማፍራት ላይ በአፅንኦት መሰራት እንደሚገባ ዶ/ር አለሙ ገልጸዋል።

መረጃው የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ነው

እንኳን ለ2019 ዓ.ም አዲስ አመት አደረሳችሁ! አዲስ ዓመት አዲስ ተስፋን፣ ፍቅርንና አብሮነትን ሰንቀን ወደ አዲስ የሥራና የልማት ምዕራፍ የምንሸጋገርበት ወቅት ነው። ቢሯችን  የመንገድ፣ ...
10/09/2026

እንኳን ለ2019 ዓ.ም አዲስ አመት አደረሳችሁ!

አዲስ ዓመት አዲስ ተስፋን፣ ፍቅርንና አብሮነትን ሰንቀን ወደ አዲስ የሥራና የልማት ምዕራፍ የምንሸጋገርበት ወቅት ነው።

ቢሯችን የመንገድ፣ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍ የክልላችንን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ለማፋጠንና የዜጎችን እንግልት ለመቀነስ የሚሠራ ዋና የልማት ደምስር ነው።

በተጠናቀቀው ዓመት የተመዘገቡ ስኬቶችን በማጠናከርና ጉድለቶችን በማረም፣ በአዲሱ ዓመት አገልግሎታችንን ይበልጥ ዘመናዊ፣ ቀልጣፋ እና አስተማማኝ ለማድረግ በቁጭት እንተጋለን።

በዓላት የደስታ፣ የመጠየቅና የአብሮነት ጊዜያት እንደመሆናቸው መጠን ከፍተኛ የሕዝብና የትራፊክ እንቅስቃሴ ይኖራል። በመሆኑም በበዓሉ ሰሞን ከፍ የሚለውን የትራፊክ እንቅስቃሴ ተከትሎ አሳዛኝ የትራፊክ አደጋዎች እንዳይከሰቱ ሁላችንም ከፍተኛ ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል።

ለአሽከርካሪዎች፣ ከፍጥነት ወሰን በላይ አለማሽከርከር፣ ሳይጠጡ ማሽከርከር፣ ተሽከርካሪን ከማንቀሳቀስ በፊት የቴክኒክ ብቃቱን ማረጋገጥ እና ከልክ በላይ ጭነት አለመጫን የሰው ሕይወትን ይታደጋል።

ለእግረኞችና ለተጓዦች፣ የመንገድ አጠቃቀም ሕጎችን ማክበር፣ ሕገ-ወጥ ታሪፍና የትርፍ ጭነት አገልግሎቶችን አለመጠቀምና አጠራጣሪ ነገሮችን ለትራፊክ ፖሊስ መጠቆም ያስፈልጋል።

በየደረጃው ለዘርፉ ለአስፈጻሚ አካላትና ትራፊክ ፖሊስ የበዓሉን ፍሰት የማስተካከልና ቁጥጥር የማድረግ ሥራን በትጋትና በኃላፊነት በመወጣት የዜጎችን ደህንነት ማስጠበቅ ይኖርብናል።

የእያንዳንዳችን ጥንቃቄና ሕግ ማክበር የራሳችንን፣ የቤተሰባችንን እና የዜጎቻችንን ሕይወት ይታደጋል።

አዲሱ 2019 ዓ.ም ለሁላችንም የሰላም፣ የጤና፣ የስኬት እንዲሁም ከአደጋ የጸዳ የደስታ ዘመን እንዲሆንልን በቅንነት እመኛለሁ!

መልካም አዲስ የ2019 ዓ.ም !

ጋሻው አወቀ (ዶ/ር )
የአማራ ክልል መንገድ፣ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ቢሮ ኃላፊ

"በቀጣዩ የበጀት ዓመት ከመቼውም ጊዜ በላይ ኃላፊነታችንን በመወጣት የተጀመሩትን ስኬቶች የምናጠናክርበት ወቅት ነው"አቶ ታደሰ ይርዳው   ‎የአብክመ መንገድ ፣ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ቢሮ ም...
08/09/2026

"በቀጣዩ የበጀት ዓመት ከመቼውም ጊዜ በላይ ኃላፊነታችንን በመወጣት የተጀመሩትን ስኬቶች የምናጠናክርበት ወቅት ነው"አቶ ታደሰ ይርዳው ‎የአብክመ መንገድ ፣ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ቢሮ ምክትል ኃላፊ

"በትራንስፖርት ዘርፍ የተገኙ ስኬቶችን ማጽናትና የታዩ ጉድለቶችን ማረም የቢሮው ቀዳሚ ተግባር ነው"አቶ ዘውዱ ማለደ የአብክመ መንገድ ፣ ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ቢሮ ምክትል ኃላፊ
08/09/2026

"በትራንስፖርት ዘርፍ የተገኙ ስኬቶችን ማጽናትና የታዩ ጉድለቶችን ማረም የቢሮው ቀዳሚ ተግባር ነው"አቶ ዘውዱ ማለደ የአብክመ መንገድ ፣ ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ቢሮ ምክትል ኃላፊ

Address

Bahir Dar

Opening Hours

Monday 02:30 - 23:30

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara RoadTransport and Logistics Bureau posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share