04/11/2026
የባሕርዳር ከተማ ምክርቤት የ2019 በጀት ዓመት 16 ቢሊዮን 289 ሚሊዮን 212 ሺህ 513 ብር መርምሮ አጽድቋል።
ጥቅምት 24/2019 ዓ.ም (ባሕር ዳር ከተማ ኮሙዩኒኬሽን)፦ የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 4ኛ ዙር፣ 14ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፣ በ33ኛ መደበኛ ጉባኤው የቀረበውን ዕቅድና 16 ቢሊዮን 289 ሚሊዮን 212 ሺህ 513 ብር የበጀት መጠን መርምሮ አጽድቋል።
የባሕር ዳር ከተማ ከንቲባ አቶ ጎሹ እንዳላማው እንደተናገሩት በ2019 በጀት ዓመት ባሕርዳር ከተማን የበለጠ ውብ፣ጽዱ፣ አረንጓዴ ለነዋሪዎች እና ለጎብኝዎቿ የምትመች ተመራጭ ከተማ ለማድረግ በመንግሥት፣ በህብረተሰብ ተሳትፎ እና በአጋር አካላት ዘርፈ ብዙ ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚሰራ ተናግረዋል።
ክቡር ከንቲባ እንደገለጹት በከተማዋ የሰላም፣ የልማትና የመልካም አስተዳድር ስራዎች በላቀ ስኬት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ማሕበረሰቡን ያሳተፈ የልማት ተግባር ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ አሳስበዋል።
በጉባኤው የዕለት ውሎ፤ የባሕርዳር ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት መምሪያ ሀላፊ አቶ ቶማስ ታምሩ የ2019 በጀት ዓመት መሪ እቅድ አቅርበዋል። በተመሳሳይ የባሕርዳር ከተማ ገንዘብ መምሪያ ሀላፊ ወ/ሮ አጸደ ምንዋጋው በመንግስት፣በህብረተሰብ ተሳትፎ እና በአጋር አካላት የሚከናወኑ ፕሮጀክቶችን አቅርበዋል።
ባሕርዳር ከተማ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን