Amhara Water and Energy Bureau

Call Directions Website Contact the organization

Amhara Water and Energy Bureau The bureau established to provide potable water & energy sustainably to the people of Amhara region.

በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ለሚከናወኑ የልማት ፕሮጀክቶች የሚደረጉ ድጋፎች ይጠናከራሉ - የዓለም ባንክ  የዓለም ባንክ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ለሚከናወኑ የልማት ፕሮጀክቶች እያደረገ ያለውን ...
04/11/2026

በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ለሚከናወኑ የልማት ፕሮጀክቶች የሚደረጉ ድጋፎች ይጠናከራሉ - የዓለም ባንክ

የዓለም ባንክ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ለሚከናወኑ የልማት ፕሮጀክቶች እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳወቀ።

የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) በጽህፈት ቤታቸው የዓለም ባንክ ተወካዮችን ተቀብለው አነጋግረዋል።

ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ ከዓለም ባንክ ጋር የምትሰራቸው ሥራዎች ውጤታማ ናቸው።

በዋን ዋሽ ፕሮግራም አማካኝነት ለሌሎች ሀገራት ተሞክሮ የሚሆን ውጤታማ ሥራ ሰርተናል ያሉት ሚኒስትሩ ይህም ውጤት በመንግሥት ጠንካራ ክትትል የመጣ ነው ብለዋል።

የዓለም ባንክ ተወካዮች ቡድን መሪ ጁሊያን ቪክተር በበኩላቸው፤ ተቋማቸው ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጋር በትብብር የሚሰራቸው ፕሮጀክቶች በጥሩ ሁኔታ እየሄዱ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።

በኢትዮጵያ መንግሥትና በልማት አጋሮች በጋራ የሚደገፈው የአንድ ቋት ብሔራዊ ዋሽ ፕሮግራም በንጹህ የመጠጥ ውሃ እና በሳኒቴሽን ከ10 ሚሊየን በላይ ሰዎች ተጠቃሚ መሆናቸውን አንስተዋል።

በተመሳሳይ በከተሞች የሚገነቡ የፍሳሽ ዝቃጭ ማከሚያ ፕሮጀክቶች በተጠናከረ ክትትል እስከ ሰኔ ወር ድረስ 14 የማከሚያ ጣቢያዎች እንዲጠናቀቁ መስራት እንደሚገባ አንስተዋል።

በውይይቱ የገጠር የውሃ አቅርቦት ዲዛይን ማጠናቀቅ፣ የቀሩ የግንባታ ውሎችን መፈረም እና የፋይናንስ ክፍያን ማፋጠን ትኩረት ከተሰጣቸው ጉዳዮች መካከል ናቸው።

በቀጣይም የኢትዮጵያ መንግሥት እና ዓለም ባንክ የጋራ የትግበራ ድጋፍና ግምገማ ተልዕኮዎችን ለማካሄድ ተስማምተዋል።

ውይይቱ የፕሮጀክቶቹን አፈፃፀምም በቅርበት ለመከታተል፣ የሚታዩ ተግዳሮቶችን በጋራ ለመፍታትና የታቀዱ ውጤቶችን ለማሳካት የሚያግዝ እንደሆነም ተነስቷል።

#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ

በ3R-4-CACE ፕሮጀክት በከሚሴ ከተማ በ100 ሚሊዮን ብር ወጪ የሶላር የውሃ ፓምፖች የግንባታና ተከላ ሥራ ተጀመረ በዓለም ባንክ ድጋፍ በሚከናወነው Response – Recovery – Re...
04/11/2026

በ3R-4-CACE ፕሮጀክት በከሚሴ ከተማ በ100 ሚሊዮን ብር ወጪ የሶላር የውሃ ፓምፖች የግንባታና ተከላ ሥራ ተጀመረ

በዓለም ባንክ ድጋፍ በሚከናወነው Response – Recovery – Resilience for Conflict-Affected Communities in Ethiopia (3R-4-CACE Project) መርሐ ግብር በከሚሴ ከተማ በሦስት ቦታዎች ላይ በ100 ሚሊዮን ብር ወጪ የኤሌክትሮሜካኒካል መሣሪያዎች (የሶላር የውሃ ፓምፖች) የግንባታና የተከላ ሥራ ተጀምሯል።

የፕሮጀክቱን የግንባታና የተከላ ሥራ የጃርሶ የውሃ ሥራዎችና አጠቃላይ ኮንትራክተር ጄቪ ከዴቪስ እና SHRTILIF ትሬዲንግ ኢትዮጵያ ኃ.የተ.የግ.ማህበር ጋር በመተባበር፣ በፌዴራል ገንዘብ ሚኒስቴር በወጣው ጨረታ በማሸነፍ እንደሚያከናውን ተገልጿል።

የሶላር ፓምፖች መገጠም ለከተማዋ የውሃ አቅርቦት ሥርዓት ከፍተኛ ፋይዳ ያለው ሲሆን፣ የኤሌክትሪክና የአሠራር ወጪን በመቀነስ፣ የውሃ አቅርቦትን በማሻሻል እንዲሁም ንጹህ የኃይል አጠቃቀምን በማስፋፋት ረገድ ጉልህ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።

ፕሮጀክቱ በተግባር ሲጠናቀቅ የከተማዋን የውሃ አቅርቦት አቅም ከማሳደጉም በላይ ዘላቂ፣ ተደራሽና የተሻለ የውሃ አገልግሎት ለማቅረብ የሚያግዝ ሲሆን፣ ለአካባቢ ጥበቃና ለከተማዋ ዘላቂ ልማትም አዎንታዊ ሚና ይኖረዋል።

የውኃ ሀብትን ለዘላቂ ልማት ለማዋል የተቀናጀ አሠራርን ማጠናከር ያስፈልጋል።የውኃ ሀብትን በአግባቡ በመጠቀም የግብርና ልማትን ማሳደግና ለቀጣዩ ትውልድ ዘላቂ የተፈጥሮ ሀብት ማስረከብ እንደሚ...
04/11/2026

የውኃ ሀብትን ለዘላቂ ልማት ለማዋል የተቀናጀ አሠራርን ማጠናከር ያስፈልጋል።

የውኃ ሀብትን በአግባቡ በመጠቀም የግብርና ልማትን ማሳደግና ለቀጣዩ ትውልድ ዘላቂ የተፈጥሮ ሀብት ማስረከብ እንደሚገባ ተገለጸ።

የአማራ ክልል ውኃና ኢነርጂ ቢሮ የተቀናጀ የውኃ ሀብት አስተዳደርና አጠቃቀምን ለማሻሻል ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያካሄደ ነው።

የዓባይ ቤዚን አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዮሐንስ መላክ እንደገለጹት፣ የውኃና የመሬት ሀብትን በተቀናጀ መንገድ ማስተዳደር ለዘላቂ ልማት ወሳኝ ነው። በተለይም ፕሮጀክቶችና ፈጻሚ ተቋማት ከተናጠል አሠራር በመውጣት የልማት ሥራዎችን በቅንጅት ማከናወን ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

የዓባይ ቤዚን ከኢትዮጵያ 12 ቤዚኖች ውስጥ እስከ 50 በመቶ የሚደርሰውን የውኃ ሀብት እንደሚይዝና ከፍተኛ የመስኖ ልማት አቅም እንዳለው የገለጹት ኃላፊው፣ ያለውን እምቅ ሀብት በአግባቡ መጠቀም እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

በወርልድ ሪሶርስ ኢንስቲትዩት የመርሐግብርና ጥናት ባለሙያ ሙሉነህ ቢምረው በበኩላቸው፣ ቀደም ሲል በተቋማት መካከል የቅንጅት እጥረት መኖሩ የውኃ ሀብት አጠቃቀም ውጤታማ እንዳይሆን እንቅፋት መሆኑን ገልጸዋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በክልሉ የተቀናጀና ዘላቂ የውኃ አጠቃቀም ማዕቀፍ ተቋቁሞ በትብብር መሠራቱ አዎንታዊ ለውጦችን እያስገኘ መሆኑንና በተመረጡ አካባቢዎችም የሙከራ ጥናቶች እየተከናወኑ መሆኑን አብራርተዋል።

በአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የተፈጥሮ ሀብት ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም ዳይሬክተር እስመለዓለም ምህረት፣ ቢሮው ከተለያዩ ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል።

በተለይም በቅንጅታዊ የተፋሰስ ልማት ሥራዎች የመኖ አቅርቦትን፣ የአትክልትና የፍራፍሬ ልማትን በማሳደግ ውጤቶች እየተገኙ መሆኑን ጠቁመዋል። ከኅብረት ሥራ ኮሚሽን ጋር በመተባበርም የተፋሰስ ኅብረት ሥራ ማኅበራት ዓመቱን ሙሉ የተፋሰስ ልማት ሥራዎችን እንዲያከናውኑ እየተደረገ መሆኑን አብራርተዋል።

የተቋማት ቅንጅትን ማጠናከር ያሉትን የውኃ ሀብቶች በተሻለ ሁኔታ ለልማት ከማዋል ባለፈ፣ የተፈጥሮ ሀብትን ለቀጣይ ትውልድ በዘላቂነት ለማስረከብ ወሳኝ መሆኑ ተጠቁሟል።

ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የቱለፋ ሴራሚክ ፋብሪካን ጎበኙ።ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኘውን የቱለፋ ሴራሚክ ፋብሪካን ጎብኝተዋል።በጉብኝቱ ከርእሰ መሥተዳድር አረጋ...
01/11/2026

ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የቱለፋ ሴራሚክ ፋብሪካን ጎበኙ።

ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኘውን የቱለፋ ሴራሚክ ፋብሪካን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ከርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በተጨማሪ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል። ፋብሪካው ደረጃውን የጠበቀ ሴራሚክ በማምረት በኮንስትራክሽን ዘርፉ የራሱን አስተዋጽኦ እያበረከተ መኾኑ ተገልጿል።

በመቶዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች የሥራ ዕድል የፈጠረው ፋብሪካው ለአካባቢው እና ለክልሉ ትልቅ አቅም መኾኑ ተገልጿል። የማምረት አቅሙም ትልቅ መኾኑ ተመላክቷል።

ሰሜን ሸዋ ዞን ለኢንዱስትሪ የተመቸ፣ በርካታ አልሚ ባለሀብቶች የሚፈልጉት አካባቢ ነው። በዞኑ በርካታ ባለሀብቶች መዋለ ነዋያቸውን ፈሰስ እያደረጉም ነው።

ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በደብረ ብርሃን ከተማ የተሠሩ የልማት ሥራዎችን መርቀው ሥራ አስጀመሩ።ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር የተሠሩ የልማት ሥራዎችን መ...
01/11/2026

ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በደብረ ብርሃን ከተማ የተሠሩ የልማት ሥራዎችን መርቀው ሥራ አስጀመሩ።

ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር የተሠሩ የልማት ሥራዎችን መርቀው አስጀምረዋል።
በማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓቱ ከርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በተጨማሪ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር እቴጌ ጣይቱ ክፍለ ከተማ የቀበሌዎችን ደረጃ ለማዘመን የተሠራውን የልቼ ቀበሌ አሥተዳደር ጽሕፈት ቤትን፣ የደብረ ብርሃን ከተማ የፍሳሽ ማጣሪያ ፕሮጄክትን፣ የደብረ ብርሃን የኮሪደር ልማትን እና የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ መምሪያ የሕንጻ ግንባታን ነው መርቀው ሥራ ያስጀመሩት።

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ከተሞችን ውብ፣ ለነዋሪዎች እና ለጎብኝዎች የተመቹ ለማድረግ በትኩረት እየተሠራ መኾኑን ገልጸዋል። ጽዱ፣ ደኅንነቱ የተጠበቀ እና ጤናው የተጠበቀ ማኅበረሰብ እንዲኖር እንዲህ አይነት ሥራዎች አስፈላጊ መኾናቸውንም ገልጸዋል። የፍሳሽ ማስወገጃ ፕሮጄክቱ ጽዱ ከተማን ለመፍጠር እንደሚያስችልም ተናግረዋል። የተሠሩትን ፕሮጄክቶች በአግባቡ መጠበቅ እንደሚገባም አመላክተዋል።

ፕሮጄክቶቹን ሠርተው ለፈጸሙ ሁሉ ምሥጋናም አቅርበዋል። በፍሳሽ ማጣሪያው ውስጥ የሚቀሩ ሥራዎችን ማጠናቀቅ እንደሚገባም አስገንዝበዋል። የተሠሩ ሥራዎችን በአግባቡ መጠቀም ደብረ ብርሃንን የኢንዱስትሪ እና የአገልግሎት መስጫ ከተማ ማድረግ ያስችላታል ነው ያሉት።

የልቼ ቀበሌ አሥተዳደር ጽሕፈት ቤት ግንባታ የከተማ አሥተዳደሩ ሕዝብን ለማገልገል ያለውን ቁርጠኝነት፣ ሕዝብ በዘመናዊ ተቋም ለመገልገል ያለውን ፍላጎት እና ድጋፍ ያሳየበት መኾኑንም ተናግረዋል። ግንባታው ዘመናዊ መኾኑንም አንስተዋል።

ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በ455 ሚሊዮን ብር በደብረ ብርሃን ከተማ የተገነባውን ዘመናዊ የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያና ማስወገጃ ፕሮጀክት መረቁ።በአማራ ክልል ውኃና ኢነርጂ ቢሮ እና በዓለም ባ...
01/11/2026

ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በ455 ሚሊዮን ብር በደብረ ብርሃን ከተማ የተገነባውን ዘመናዊ የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያና ማስወገጃ ፕሮጀክት መረቁ።

በአማራ ክልል ውኃና ኢነርጂ ቢሮ እና በዓለም ባንክ ሁለተኛው የከተሞች መጠጥ ውኃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት የ455 ሚሊዮን ብር ትብብር በደብረ ብርሃን ከተማ የተገነባው የሳኒቴሽን ፕሮጀክት ነው በርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ እና የክልሉ ከፍተኛ መሪዎች በተገኙበት የተመረቀው።

ፕሮጀክቱ ለ15 ዓመታት እንዲያገለግል እና ለ120 ሺህ ነዋሪዎች አገልግሎት መስጠት የሚያስችል አቅም ያለው ነው። በተጨማሪም በተማዋ የነበረውን የፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃና ማጣሪያ ችግር ለመፍታት የሚያስችል ነው።

አዲሱ የፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ ፕሮጀክት በውስጡ 22 የማጣሪያና ማጠታቀሚያ ቦታዎችን አካቶ የተገነባ መሆኑ ጥራቱን ከፍ ያደርገዋል።

የከተማዋን መጸዳጃ ቤቶች ፍሳሽ ቆሻሻ አጣርቶ ለአካባቢ ጥበቃ ተስማሚ በሆነ መንገድ ማስወገድም የሚያስችል ነው።

በተጨማሪም የተጣራው ቆሻሻ ለአፈር ማዳበሪያና ሌሎችም የኢኮኖሚ ጠቀሜታ እንዲኖረው ተደርጎ ተገንብቷል።

30/10/2026

"ባሕርዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ፣ደብረብርሃን፣ እንጂባራና አረርቲን ጨምሮ በኢትዮጵያ 23 ትላልቅ ከተሞች ዘመናዊ የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያና ማስወገጃ ፕሮጀክቶች እየተገነቡ ነው።

ከነዚህ ፕሮጀክቶች መካከል በኢፌዴሪ የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እና በዓለም ባንክ የ455 ሚሊዮን ብር ትብብር የተገነባው የደብረብርሃን ዘመናዊ የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያና ማስወገጃ ፕሮጀክት ግንባታ ተጥርናቋል።

ፕሮጀክቱ ከፍተኛ የኢንቨስት የስበት ማዕከል የሆነችውን የደብረብርሃን ከተማ የበለጠ ጽዱ እና ለኑሮ የተመቸች በማድረግ ከ120 ሺህ በላይ የሚሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎችን የፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ የሚያዘምን "የጽዱ ኢትዮጵያ" ሃገር አቀፍ ኢኒሼቲቭ ቱሩፋት ነው።

የጽዱ ኢትዮጵያ ሃገር አቀፍ ኢኒሼቲቭ ውብ የስኬት መልክ የሆነውን የከተሞች ሳኒቴሽን መሰረተ ልማት ግንባታ ተግባር ከክቡር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር-ኢ/ር) የኢፌዴሪ ውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር እነሆ ...

በራያ ቆቦ ወረዳ 245 ሚሊዮን ብር በሚጠጋ ወጪ ግንባታው እየተገባደደ ያለውን የወርቄ ያያ የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክት በፍጥነት ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ ነው።ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ በወርቄና ያያ...
30/10/2026

በራያ ቆቦ ወረዳ 245 ሚሊዮን ብር በሚጠጋ ወጪ ግንባታው እየተገባደደ ያለውን የወርቄ ያያ የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክት በፍጥነት ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ ነው።

ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ በወርቄና ያያ ቀበሌዎች የሚኖሩ 20 ሺህ የሚጠጉ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል።

በመንግስትና በዓለም ባንክ የCR-WASH ፕሮጀክት በተመደበ 244 ሚሊዮን 581 ሺህ 789 ብር በጀት በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ ግንባታው እየተገባደደ የሚገኘውን የወርቄ ያያ የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክት በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ በቅንጅት እየተሰራ ነው።

ባለ ብዙ መንደር አገናኝ የሆነው ፕሮጀክት ግንባታ ሲጠናቀቅ ሁለት ቀበሌዎች ለሚኖሩ 20 ሺህ የሚጠጉ የህብረተሰብ ክፍሎች የንጹህ መጠጥ ውኃ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

ቀሪ ስራዎችን በፍጥነት ለማጠናቀቅም የኢፌዴሪ ውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እና የአማራ ክልል ውኃና ኢነርጂ ቢሮ ከዞኑና የወረዳው አስተዳደርና ከተጠቃሚው ህዝብ ጋር በቅንጅት እየሰሩ ነው።

የምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ውሃና ኢነርጅ ልማት ፅ/ቤት የ1ኛውን ሩብ አመት አፈፃፀም ገመገመ።ግምገማው በሩብ አመቱ የነበሩ ጠንካራና ደካማ ጎኖችና የቀጣይ ወራት ተግባራት  ቀርቦ እየተገመገመ ...
29/10/2026

የምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ውሃና ኢነርጅ ልማት ፅ/ቤት የ1ኛውን ሩብ አመት አፈፃፀም ገመገመ።

ግምገማው በሩብ አመቱ የነበሩ ጠንካራና ደካማ ጎኖችና የቀጣይ ወራት ተግባራት ቀርቦ እየተገመገመ ነው።

በግምገማ መድረኩ የምዕራብ ጎንደር ዞን ውሃና ኢነርጅ ልማት መመሪያ ኃላፊ አቶ ይርዳው ካሳው፣ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ እሸቱ ስመኘው ፣የወረዳው ገንዘብ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ ማሩ ። የስራና ክህሎት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ወንዴ ወረታው የተቋሙ ባለሙያዎች እየተሳተፉ ነው።

"ኢትዮጵያ በሦስት ቁልፍ መስኮች ላይ ኢንቨስት እያደረገች ትገኛለች፤ እነሱም ምግብ፣ ኢነርጂ (ኃይል) እና እውቀት ናቸው።"ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)በራሺያ ለመሪዎች ከተናገሩት
29/10/2026

"ኢትዮጵያ በሦስት ቁልፍ መስኮች ላይ ኢንቨስት እያደረገች ትገኛለች፤ እነሱም ምግብ፣ ኢነርጂ (ኃይል) እና እውቀት ናቸው።"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)በራሺያ ለመሪዎች ከተናገሩት

Address

Poly Peda Street
Bahir Dar
088

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 17:30

Telephone

+251582201704

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara Water and Energy Bureau posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Amhara Water and Energy Bureau:

Shortcuts

Share