Finote Selam City Revenue Office

Call Directions Website Contact the organization

Finote Selam City Revenue Office The aim of fenotselam city revenue office is to collect tax properly

30/10/2026

፨ ብር 225,074,013 ገቢ ተሠበሠበ፣
ግብር ለሀገር ክብር መሆኑን የተገነዘቡ የከተማችን ግብር ከፋዮች የ2018 ዓ/ምን ግብር እየከፈሉ ነው። የፍ/ሠላም ከተማ አስተዳድር ገቢዎች ጽ/ቤት እስከ ጥቅምት 20/2019 ዓ/ም ከመደበኛ ገቢ ብር 183,846,073 ከከተማ አገልግሎት ገቢ ብር 41,227,940 በድምሩ ብር 225,074,013 ገቢ ሠብስቧል። እስካሁን ግብሬን ደስ ብሎኝ እከፍላለሁ በሚል ቁርጠኝነት 2458 የደረጃ "ለ" እና 1354 የአከራይ ተከራይ ግብር ከፋዮች የግብር ግዴታቸውን ተወጥተዋል። ጥቂት ግብር ከፋዮች ይቀራሉ። ስለዚህ እስከ ጥቅምት 30/2019 ዓ/ም ከፍላችሁ እንድታጠናቅቁ እያሳሰብን በቀጣይ ከኅዳር 1 እስከ 30/2019 ዓ/ም የ1ኛው ሩብ ዓመት የሚከፈልበት ቀናት ስለሆነ ቅጣት ውስጥ እንዳትገቡ እናሳስባለን።
" የፍ/ሠላም ከተማ አስ/ገቢዎች ጽ/ቤት!

የፍ/ሠላም ከተማ አስተዳድር ገቢዎች ጽ/ቤት አገልግሎት ፈልጎ የመጣውን ግብር ከፋይ በማረፊያ ቦታ ስለ ግብር አጠናን ለይግባኝ የመጣውን ግብር ከፋይ አጭር ግንዛቤ  በግብር ትምህርትና ኮሙኒኬ...
27/10/2026

የፍ/ሠላም ከተማ አስተዳድር ገቢዎች ጽ/ቤት አገልግሎት ፈልጎ የመጣውን ግብር ከፋይ በማረፊያ ቦታ ስለ ግብር አጠናን ለይግባኝ የመጣውን ግብር ከፋይ አጭር ግንዛቤ በግብር ትምህርትና ኮሙኒኬሽን አስተባባሪ አማካኝነት ትምህርት ተሠጥቷል።

የፍ/ሠላም ከተማ አስተዳድር ገቢዎች ጽ/ቤት ማኔጅመንት አካል የተቋሙን የ1ኛውን ሩብ ዓመት አፈፃፀም እያንዳንዱ የሥራ ሒደት ሪፖርት እያቀረቡና እዚያው ላይ አሉ የሚባሉ ችግሮችን እያነሳን እ...
26/10/2026

የፍ/ሠላም ከተማ አስተዳድር ገቢዎች ጽ/ቤት ማኔጅመንት አካል የተቋሙን የ1ኛውን ሩብ ዓመት አፈፃፀም እያንዳንዱ የሥራ ሒደት ሪፖርት እያቀረቡና እዚያው ላይ አሉ የሚባሉ ችግሮችን እያነሳን እየገመገምን ነው። ግምገማውን የተቋሙ ኃላፊ አቶ አዝመራው ሙሉሰው አየመሩ እየተካሄደ ነው። ሒደቶች ደረጃ ለባለሙያውም ለሒደቱ መሰጠት አለበት ሲሉ የተቋሙ ኃላፊ ገልፀውና ለዚህ ግምገማ ለእያንዳንዱ ግብረ መልስ መሰጠት አንዳለበት መመሪያ በመስጠት ተጠናቋል።

ግብር ሰንከፍል በምትኩ ዕቃ ሳይሆን የምንጠብቅ ለማኀበረሰቡ፣ ለእኔ፣ ለእናንተ፣ ለረጅም ጊዜ የሚያገለግል ከትውልድ ትውልድ የሚሸጋገር ልማት ይበረከታል። የፍ/ሠላም ከተማ የአገልግሎት አሰጣቱ...
24/10/2026

ግብር ሰንከፍል በምትኩ ዕቃ ሳይሆን የምንጠብቅ ለማኀበረሰቡ፣ ለእኔ፣ ለእናንተ፣ ለረጅም ጊዜ የሚያገለግል ከትውልድ ትውልድ የሚሸጋገር ልማት ይበረከታል። የፍ/ሠላም ከተማ የአገልግሎት አሰጣቱን ለማሳለጥና ተገልጋዮ ማኀበረሰብ አገልግሎቱን በአንድ ሞሰብ ተገልግሎ ውጣ ውረድ ሰይኖርበት ጨርሶ የሚወጣበት የአንድ ሞሰብ አገልግሎት ማዕከል ግንባታ በቅርብ ጊዜ ሲጀመር እና አሁን ምን ደረጃ እንደደረሰ ከፎቶው ተመልከቱ፣
ከዚህ በኋላ ደግሞ ለውጡን አያሰየናችሁ ሲጠናቀቅ እናንተ ለመገልገል አኛ ለማገልገል እዚያው እንገናኝ በከፈልነው ግብር ይህ ሲከፈለን ደስ አይልም?
✈ "ግብር ለሀገር ክብር!!🎂

የፍ/ሠላም ከተማ አስተዳድር ገቢዎች ጽ/ቤት የ2019 በጀት ዓመት መደበኛና የከተማ አገልግሎት ገቢ ለመሰብሰብ ቸክ ሊስት በማዘጋጀት በ2 / ሁለት/ ቡድን አደረጃጀት በመፍጠር ማኔጅመንትን ጨ...
15/10/2026

የፍ/ሠላም ከተማ አስተዳድር ገቢዎች ጽ/ቤት የ2019 በጀት ዓመት መደበኛና የከተማ አገልግሎት ገቢ ለመሰብሰብ ቸክ ሊስት በማዘጋጀት በ2 / ሁለት/ ቡድን አደረጃጀት በመፍጠር ማኔጅመንትን ጨምሮ የሰው ኃይል በመመደብ የተዘጋጀውን ቸክ ሊስት ለቡድኑ አባላት በ05/02/2019 ዓ/ም በም/ኃላፊው በአቶ ታየ ሠሎሞን ኦሬንቴሽን ተሠጥቶ ወደ ተግባር የተገባ ሲሆን ቡድኑ፣
▸ ደረሰኝ ክትትል ማድረግ፣
▸ የአልከፈሉ የደረጃ "ለ" ግብር ማስከፈል፣
▸ ውዝፍ ግብር ማስከፈል፣
▸ የሊዝ ክፍያ ማስከፈል፣
▸ ሥራ ግብር ማስከፈል፤
ዋና ዋና ተግባር በማድረክ ለማከናወን በመግባባት ሥራው ተጀምሯል።

ለከተማችን ነጋዴዎች የተላለፈ አስቸኳይ ማስታወቂያ ከፍኖተ ሰላም ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽሕፈት ቤት!ስማችሁ ከዚህ በታች ለተዘረዘራችሁ ግብር ከፋዮች በሙሉ የኦዲት ሰነዶችን እንድታቀርቡ ለ...
07/10/2026

ለከተማችን ነጋዴዎች የተላለፈ አስቸኳይ ማስታወቂያ ከፍኖተ ሰላም ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽሕፈት ቤት!

ስማችሁ ከዚህ በታች ለተዘረዘራችሁ ግብር ከፋዮች በሙሉ የኦዲት ሰነዶችን እንድታቀርቡ ለመጨረሻ ጊዜ ስለማሳወቅ፤

ማንኛውም ግብር ከፋይ በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 241/2008 አንቀጽ 18 መሠረት የሂሳብ ሰነዶቹን ለባለሥልጣኑ ምርመራ ማቅረብ ይኖርበታል።

በዚህም መሠረት በተለያዩ የበጀት ዓመታት ዓመታዊ የሂሳብ መዝገብ ያቀረባችሁ ቢሆንም፣ ለኦዲት ምርመራ የሚያስፈልጉ ዋና ዋና የሂሳብ ደጋፊ ሰነዶችን ሳታቀርቡ በመቅረታችሁ በኦዲት አሠራሩ ላይ ችግር ተፈጥሯል። በመሆኑም አስፈላጊዎቹን ሰነዶች እንድታቀርቡ በተደጋጋሚ ተጠይቃችሁ ያላቀረባችሁ በመሆኑ ጽሕፈት ቤቱ ይህንን ማስታወቂያ ለማውጣት ተገዷል።

ስለሆነም በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 241/2008 አንቀጽ 80(1/ሐ) እና በመመሪያ ቁጥር አገ/አገ/26/2016 አንቀጽ 26(1) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት፣ ማስታወቂያው ከተጻፈበት ከ20/01/2019 ዓ.ም. ጀምሮ ባለው ጊዜ ውስጥ ለኦዲት ምርመራ የሚሆኑ ዋና የሥራ ደረሰኞችን እና የሂሳብ መዝገቦችን ለጽሕፈት ቤቱ ታክስ ኦዲትና ኢንቨስትመንት ዋና የሥራ ሂደት እንድታቀርቡ እናሳውቃለን።

የተሰጠው የጊዜ ገደብ አልፎ ሰነዶቹን የማያቀርብ ግብር ከፋይ ካለ፣ ጽሕፈት ቤቱ በመመሪያ ቁጥር አገ/አገ/26/2016 አንቀጽ 24(ለ) እና በአዋጁ ድንጋጌዎች መሠረት አስፈላጊውን ውሳኔ የሚወስድ መሆኑን ከወዲሁ ያሳውቃል።

የፍኖተ ሰላም ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽሕፈት ቤት

Finote Selam City Communications

የፍ/ሠላም ከተማ አስተዳድር ገቢዎች ጽ/ቤት በ 25/01/2019 ዓ/ም ከአጋርና ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አደረገ።ውይይቱ በከተማ አስተዳድሩ ክቡር ም/ከንቲባ አቶ ጊዜው ደጋረገ ሰብሳቢነ...
05/10/2026

የፍ/ሠላም ከተማ አስተዳድር ገቢዎች ጽ/ቤት በ 25/01/2019 ዓ/ም ከአጋርና ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አደረገ።
ውይይቱ በከተማ አስተዳድሩ ክቡር ም/ከንቲባ አቶ ጊዜው ደጋረገ ሰብሳቢነት የተካሄደ ሲሆን ገቢን በመቀናጀት ካልሰበሰብነው ለአንድ ተቋም ብቻ የምንተወው አይደለም ሲሉ ገልፀው ተሠብሳቢ ተቋሞች ገቢን አስመልክቶ ተቀናጅቶ ገቢ ለመሠብሰብ ምን አስባችኋል በማለት ሀሳብ እንዲሰጡ ጋብዘዋል። የገቢ ተቋሙ ኃላፊ አቶ አዝመራው ሙሉሰው በ 22/01/2019 ዓ/ም አብዛኛው ይህ አካል በተገኘበት በዚህ አጀንዳ ተወያይተን ተቀናጅተን ገቢ ለመሰብሰብ ተግባብተናል ሲሉ ገልፀዋል። ሌሎች ተቋማትም ገቢ አንዲሰበሰብ በየድርሻቸው አየሰሩ መሆኑን ገልፀዋል። በመጨረሻም አቶ ጊዜው ገቢን በመቀናጀትና በመተባበር የገቢ ዕቅዱን ከማሳካት ባለፈ ለከተማችን ልማት ዕድገት ጉልህ አስተወፅኦ አለው ካሉ በኋላ ገቢ የሚሰበሰብበት እዚህ የተገኛችሁም የአለተገኙትን ጨምሮ በቀጣይ ሞቅ ያለ ገቢ የመሰብሰብ ንቅናቄ እናደርጋለን የገቢ ተቋሙ ለሌሎች ተቋማት ዕቅዱን ቆርሶ የሚሰጥበትን ሠነድ እና ንቅናቄው የሚመራበትን አክሽን ፕላን እንዲያዘጋጅ ማጠቃለያ ሰጥተው ውይይቱ ተጠናቋል።

የፍ/ሠላም ከተማ አስተዳድር ገቢዎች ጽ/ቤት ከአገር ሽማግሌዎች እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ማህበረሰቦች ጋር ስለ ግብር ትርጉምና ጠቀሜታ ውይይት አድርጓል። በውይይቱም ግብር ከአልተከፈለ ማህበረሰቡ የ...
02/10/2026

የፍ/ሠላም ከተማ አስተዳድር ገቢዎች ጽ/ቤት ከአገር ሽማግሌዎች እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ማህበረሰቦች ጋር ስለ ግብር ትርጉምና ጠቀሜታ ውይይት አድርጓል። በውይይቱም ግብር ከአልተከፈለ ማህበረሰቡ የሚፈልገውን የመልማት ጥያቄ ምላሽ ሊሠጠው አይችልም። ስለዚህ ግብር መክፈል ግዴታ ነው ሲሉ ተሳታፊዎች የገለፁ ሲሆን በከተማችን የሚሠራው ልማት ግን ከቀበሌ ቀበሌ ፍትሀዊ መሆን አለበት ብለዋል። በመጨረሻም ማህበረሰቡ የአልከፈለው የአከራይ ተከራይ፣ የንግድ ትርፍ ግብር አንዲከፍሉ ማሳሰቢያ ተሰጥቶ ተጠናቋል።

30/09/2026

የፍ/ሠላም ከተማ አስተዳድር ገቢዎች ጽ/ቤት እስከ 19/01/2019 ዓ/ም ብር 150,948,044.73 ገቢ ሰበሰበ፣
ተቋሙ አስከ መስከረም 19/2019 ዓ /ም
▸ ከመደበኛ ገቢ ብር 122,321,317.65
▸. ከከተማ አገልግሎት ገቢ ብር 28,626,727.07
▸ በድምሩ ብር 150,948,044.73 መሰብሰብ ችሏል። ይህ ገቢ አስከ 1ኛው ሩብ ዓመት ማጠናቀቂያ ድረስ መጠኑ ከፍ እንደሚል ይጠበቃል።
. " ግብር ለሀገር ክብር!!
የፍ/ሠላም ከተማ አስተዳድር ገቢዎች ጽ/ቤት

Address

Finote Selam

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Finote Selam City Revenue Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Finote Selam City Revenue Office:

Shortcuts

Share