Office Of Gambella Region Auditor General

Directions

Office Of Gambella Region Auditor General Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Office Of Gambella Region Auditor General, Government Organization, Gambela.

28/04/2026
የጋምቤላ ክልል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የኑዌር ብሔረሰብ ዞን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ከየካታት 2017 እስከ ሰኔ 30/2017 ዓ/ም የመደበኛ ሂሳብ ምርመራ ልዩ ልዩ ግኝቶችና የኦዲት ው...
28/04/2026

የጋምቤላ ክልል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የኑዌር ብሔረሰብ ዞን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ከየካታት 2017 እስከ ሰኔ 30/2017 ዓ/ም የመደበኛ ሂሳብ ምርመራ ልዩ ልዩ ግኝቶችና የኦዲት ውጤት ላይ የመውጫ ስብሰባ አካሔደ።
የክልሉ ዋና ኦዲተር መ/ቤት ኮሙኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት ክፍል። ( ሚያዝያ 20/2018 ዓ/ም )

የክልሉ ምክትል ዋና ኦዲተር ክቡር አቶ ሉል ቦል ውይይቱን በንግግር የከፈቱ ሲሆን በንግግራቸው ሆስፒታሉ ከዚህ ቀደም ልዩ ኦዲት የተደረገበት ሲሆን በልዩ ኦዲት ወቅት የተገኙ የኦዲት ግኝቶችን መስተካከያ የደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

ኦዲቱን በቡድን መሪነት ያከናወኑት የክልሉ ዋና ኦዲተር መ/ቤት የኦዲት ባለሙያ አቶ ግዛቸው ጫሚሶ የተገኙ የኦዲት ምርመራ ልዩ ልዩ ግኝቶችን በዝርዝር ሊያቀርቡ ችለዋል።
የዞኑ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ኃላፊ ፣ የሆስፒታሉ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ እና ሌሎች የሚመለከታቸው ኃላፊዎች በተገኙ ግኝቶች መተማመን ላይ ደርሰዋል።

የክልሉ ሞክትል ዋና ኦዲተር አክለውም በኦዲት ምርመራ ወቅት የተገኙ ልዩ ልዩ የኦዲት ውጤቶች በ15 ቀናት ውስጥ ግብረ- መልስ እንዲሰጥባቸው በማሳሰብ ውይይቱ ሊጠናቀቅ ችሏል ።

ዋስይሁን አበራ ለገሠ

የጋምቤላ ክልል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የኑዌር ብሔረሰብ ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ የ20😂7በጀት ዓመት የመደበኛ ሂሳብ ምርመራ ልዩ ልዩ ግኝቶችና የኦዲት ዉጤት ላይ የመውጫ ስብሰ...
28/04/2026

የጋምቤላ ክልል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የኑዌር ብሔረሰብ ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ የ20😂7በጀት ዓመት የመደበኛ ሂሳብ ምርመራ ልዩ ልዩ ግኝቶችና የኦዲት ዉጤት ላይ የመውጫ ስብሰባ አካሔደ ።
የክልሉ ዋና ኦዲተር መ/ቤት ኮሙኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት ክፍል ። ( ሚያዝያ 20/2018ዓ/ም )

የክልሉ መክትል ዋና ኦዲተር ክቡር አቶ ሉል ቦል ውይይቱን በንግግር የከፈቱ ሲሆን በንግግራቸውም ኦዲት የዞኑን ሀብትና ንብረት በአግባቡ እንድንጠቀም አቅጣጫ የሚያሳይ መሆኑን አመራሩና የሂሳብ ባለሙያዎች መገንዘብ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ኦዲቱን በቡድን መሪነት ያከናወኑት የክልሉ ዋና ኦዲተር መ/ቤት ከፍተኛ የኦዲት ባለሙያ አቶ ግዛቸው ጫሚሶ በኦዲት ወቅት የተገኙ ልዩ ልዩ ግኝቶችና የኦዲት ውጤቶችን አብራርተዋል።

የዞኑ ፋይናንሰና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ኃላፊ ፣ የዞኑ ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ እና የሚመለከታቸው አካላት የቀረቡትን የኦዲት ምርመራ ልዩ ልዩ ግኝቶችና የኦዲት ውጤቶች ተማምነዋል።

በመጨረሻም የክልሉ ዋና ኦዲተር መ/ቤት የፋይናንሻል ህጋዊነት ኦዲት ዳይሬክተር አቶ ሙሉጌታ ታደሰ በኦዲት ምርመራ ወቅት የተገኙ ልዩ ልዩ የኦዲት ውጤቶች በ15 ቀናት ውስጥ ግብረ- መልስ እንዲሰጥባቸው በማሳሰብ ስብሰባው ሊጠናቀቅ ችሏል ።

ዋስይሁን አበራ ለገሠ

የጋምቤላ ክልል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋምቤላ ቅርንጫፍ ጋር በባንኩ የተመቻቸውን የመንግስት ሠራተኞች የገንዘብ ብድር አሰጣጥና አመላለስ ላይ ውይይት አካሔደ።የክልሉ...
10/04/2026

የጋምቤላ ክልል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋምቤላ ቅርንጫፍ ጋር በባንኩ የተመቻቸውን የመንግስት ሠራተኞች የገንዘብ ብድር አሰጣጥና አመላለስ ላይ ውይይት አካሔደ።
የክልሉ ዋና ኦዲተር መ/ቤት ኮሙኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት ክፍል ። ( መጋቢት 30/2018 ዓ.ም )

በክልሉ ዋና ኦዲተር መ/ቤት ጋባዥነት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋምቤላ ቅርንጫፍ ለመንግስት ሠራተኞች የተመቻቸውን የገንዘብ ብድር አሰጣጥና አመላለስ ላይ ከተቋሙ አመራሮችና ሠራተኞች ጋር ውይይት ሊያደርግ ችሏል።
የክልሉ ዋና ኦዲተር ክቡር አቶ ኡጁሉ ኡጁሉ ዉይይቱን በንግግር ከፍተዋል ። በንግግራቸውም ሠራተኞች ብድር ከወሰዱ በኃላ ገንዘቡን ለታለመለት ዓላማ ማዋል እንዳለባቸው አሳስበዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋምቤላ ቅርንጫፍ ቢዝነስ ማናጀር አቶ ዲሪባ አሰፋ በገንዘብ በብድር አሰጣጥና አመላለስ ላይ ሰፊ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን የመ/ቤቱ ሠራተኞች የተለያዩ አስተያየቶችችና ጥያቄዎች አንስተዋል።
ቢዝነስ ማናጀሩ ለቀረቡ ጥያቄዎች በመመሪያው መሠረት መልስ ሰጥተዋል። በመጨረሻም በዋና ኦዲተሩ የመዝጊያ ንግግር ተደርጎ ውይይቱ ሊጠናቀቅ ችሏል።

የጋምቤላ ክልል የኦዲት ፎረም በክልሉ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ከ2014 በጀት ዓመት እስከ 2016 በጀት ዓመት ድረስ ያቀረበውን የኦዲት ግኝቶች መመለስ በሚችሉባቸው አቅጣጫዎች ላይ ተወያይቶ...
06/02/2026

የጋምቤላ ክልል የኦዲት ፎረም በክልሉ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ከ2014 በጀት ዓመት እስከ 2016 በጀት ዓመት ድረስ ያቀረበውን የኦዲት ግኝቶች መመለስ በሚችሉባቸው አቅጣጫዎች ላይ ተወያይቶ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ ።
የክልሉ ዋና ኦዲተር መ/ቤት ኮሙኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት ክፍል ።( ጥር 29/2018 ዓ/ም )

የክልሉ ኦዲት ፎረም በክልሉ ዋና ኦዲተር መ/ቤት ከ2014 በጀት ዓመት እስከ 2016 በጀት ዓመት ድረስ በቀረቡ የኦዲት ግኝቶች መመለስ በሚችሉባቸው አቅጣጫዎች ላይ የተለያዩ ውሳኔዎችን ሊያስተላልፍ ችሏል
የኦዲት ፎረሙ ሰብሳቢ ክብርት አፈ - ጉባኤ ወ/ሮ መሠረት ማቲዮስ ውይይቱን በንግግር ከፍተዋል ።
ክብርት አፈ ጉባኤ በመክፈቻ ንግግራቸው መንግስት የሰጠንን አደራ መጠበቅና ማስጠበቅ የሁሉም አመራሮች ተግባርና ኃላፊነት ሲሆን ፤ በተለይ የኦዲት ግኝት የተገኘባቸውን ግለሰቦችና ተቋማት ግኝቶች ተመላሽ እንዲያደርጉ ፎረሙ ጠንክሮ እንደሚሠራ ገልፀዋል።

የኦዲት ፎረሙ አባላት የቀረቡ የኦዲት ግኝቶች መመለስ የሚችሉባቸውን አቅጣጫዎች ላይ ሰፊ ውይይት አድርገዋል

በመጨረሻም በክልሉ በግለሰቦች እና በተቋማት ላይ የተገኙ ግኝቶች የክልሉ ዋና ኦዲተር መሰሪያ ቤት እና የክልሉ ፍትህ ቢሮ በጋራ በመሆን ግኝቶቹን እንዲያስመልሱ ፎረሙ በሙሉ ድምፅ ውሳኔ አሳልፏል ።

የጋምቤላ ክልል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ከ2014 እስከ 2016 በጀት ዓመት ድረስ የኦዲት ግኝት ለክልሉ ኦዲት ፎረም  አቀረበ ።የክልሉ ዋና ኦዲተር መ/ቤት ኮሙኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት ክፍ...
06/02/2026

የጋምቤላ ክልል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ከ2014 እስከ 2016 በጀት ዓመት ድረስ የኦዲት ግኝት ለክልሉ ኦዲት ፎረም አቀረበ ።
የክልሉ ዋና ኦዲተር መ/ቤት ኮሙኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት ክፍል ። ( ጥር 29/2018 ዓ/ም )

የክልሉ ዋና ኦዲተር መ/ቤት ከ2014 በጀት ዓመት እስከ 2016 በጀት ዓመት ድረስ በተደረጉ የኦዲት ምርመራ ግኝቶችን ለክልሉ ኦዲት ፎረም ሊያቀርብ ችሏል ።

የኦዲት ፎረሙ ሰብሳቢ ክብርት አፈ - ጉባኤ ወ/ሮ መሠረት ማቲዮስ ውይይቱን በንግግር ከፍተዋል ።
ክብርት አፈ - ጉባኤ በመክፈቻ ንግግራቸው ኦዲት ዋና ዓላማው የህዝብና የመንግስት ሀብትና ንብረት ከምዝበራና ከብክነት ማዳን መሆኑን ገልፀዋል ።

በውይይቱ ወቅት በፎረም አባላት የተለያዩ ገንቢ ሀሳቦችና አስተያየቶች ቀርበዋል።
በመጨረሻም የኦዲት ፎረሙ የቀረቡትን የኦዲት ግኝቶች ማስመለሻ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ሊጠናቀቅ ችሏል ።

የጋምቤላ ክልል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት አመራሮችና ሠራተኞች ከክልሉ ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ጋር በመተባበር 22ኛው የፀረ ሙስና ቀን በዓል በፓናል ውይይት አከበሩ።የክልሉ ዋና ኦዲ...
05/12/2025

የጋምቤላ ክልል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት አመራሮችና ሠራተኞች ከክልሉ ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ጋር በመተባበር 22ኛው የፀረ ሙስና ቀን በዓል በፓናል ውይይት አከበሩ።
የክልሉ ዋና ኦዲተር መ/ቤት ኮሙኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት ክፍል ( ህዳር 24/2018 ዓ.ም )

የክልሉ ዋና ኦዲተር መ/ቤት አመራሮችና ሠራተኞች ከክልሉ ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ጋር በመተባበር ትውልድን በሥነ ምግባር ተቋምን በአሰራር በሚል መሪ ቃል በመከበር ላይ ያለውን 22ኛው የፀረ ሙስና ቀን በዓል በፓናል ውይይት ሊያከብሩ ችለዋል።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የክልሉ ምክትል ዋና ኦዲተር አቶ ሉል ቦል ውይይቱ ወቅቱን የጠበቀና ለተቋማዊ ለውጥ ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል ። ምክትል ዋና ኦዲተሩ አክለው ሙስናን መከላከል የሁሉም አመራርና ሠራተኞች የጋራ ተልዕኮ መሆኑን አሳስበዋል።

የክልሉ ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የሰው ሀብት አስተዳደር ቡድን መሪ አቶ ጌታቸው ባህሩ በተቋማት ደረጃ ሊፈፀሙ የሚችሉባቸው የአሰራር ክፍተቶችና የተቀናጀ የሙስና ትግል ሰነድን በማብራራት አቅርበዋል።

በቀረበው ሰነድ ላይ አመራሩና ሠራተኞች ጥያቄዎችና አስተያየቶችን አቅርበው፤ በቀረቡ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተገቢው መልስ ተሰጥቶባቸው ውይይቱ ተጠናቋል።

Address

Gambela

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Office Of Gambella Region Auditor General posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share