Gurage Zone Job Creation and Enterprise Development Department

Directions

Gurage Zone Job Creation and Enterprise Development  Department private

22/10/2026
21/10/2026
ለወጣቶች የስራ እድል በመፍጠርና ብድር በማሰራጨት በዘርፉ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በትኩረት እየተሰራ ነው፦አቶ ሙራድ ያሲንጥቅምት 11/2019(ወልቂጤ)የጉራጌ ዞን ስራ እድል ፈጠራና ኢን...
21/10/2026

ለወጣቶች የስራ እድል በመፍጠርና ብድር በማሰራጨት በዘርፉ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በትኩረት እየተሰራ ነው፦አቶ ሙራድ ያሲን

ጥቅምት 11/2019(ወልቂጤ)

የጉራጌ ዞን ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት መምሪያ የJHUCCP (የማህበረሰብ አገልግሎት ለስራ ሽግግር) ፕሮጀክት የመሁር አክሊል ወረዳ እና የወልቂጤ ከተማ የ2018 አፈጻምና የ2019 እቅድ ላይ ትኩረት ያደረገ የውይይት መድረክ በወልቂጤ ከተማ አካሂዷል።

የጉራጌ ዞን ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙራድ ያሲን እንዳሉት በዞኑ ለዜጎች የስራ እድል በመፍጠርና ብድር በማሰራጨት በዘርፉ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በትኩረት እየተሰራ ነው።

JHUCCP ፕሮጀክት በዞኑ ዜጎችን ከሥራ ዕድል ጋር በማገናኘት የሥራ ልምድ፣ ገቢና ክህሎት እንዲያገኙ በማድረግ ወደ ቋሚ የሥራ ዕድል ሽግግርን እያመቻቸ ይገኛል ብለዋል።

አቶ ሙራድ አክለውም የሥራ ልምድ በማስገኘት፣ ቋሚ ሥራ እድል በመፍጠር፣ሥራ ፈጣሪነትን በማበረታታት ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ነው ያሉት።

በመሆኑም በፕሮጀክቱ የተገኘውን ክህሎትና ልምድ በመጠቀም ወጣቶች ራስን በራስ የመተዳደርና አነስተኛ ሥራ የመጀመር ልምድ ማሳደግ እንደሚገባ አብራርተዋል።

የስራአጥ ልየታን በአግባቡ መለየት ፣የመረጃ አያያዝ ስርአትን ማዘመንና በዘርፉ የድጋፍና ክትትል ስራዎች በመስራት ቅንጅታዊ አሰራር ማጠናከር እንደሚገባ አቶ ሙራድ መክረዋል።

የJHUCCP ፖሮጀክት አስተባባሪ አቶ ሸዋ መርጋ ብድር ለወሰዱ ወጣቶች ትርፋማ እንዲሆኑ ጥብቅ ክትትል ማድረግ ያስፈልጋል ብለው የባንክ አማራጮች የማስፋትና በዘርፉ የሚገጥሙ ችግሮች በማረም ፕሮጀክቱ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

በውይይቱ የተሳተፉት አቶ በሀሩ እና ወ/ሮ ፈሰሱ ገ/ማረያም እንዳሉት ፕሮጀክቱ ለወጣቶች በሚሰጠው የብድር አቅርቦት በርካታ ሴቶች፣ ወጣቶችና አካል ጉዳተኞች ኢኮኖሚያዊ አቅም ፈጥረው የተሻለ ካፒታል ማስመዝገብ ችለዋል።

በዚህም ሴቶች 70 ፐርሰንት፣ወንዶች 20 ፐርሰንትና አካል ጉዳተኞች ደግሞ 10 ፐርሰንት እያስጠቀመ ሲሆን ለወጣቶች አዲስ የስራ እድል እየፈጠረ ያለ ፕሮጀክት ስለመሞኑ አንስተዋል።

የባንክ አማራጮች ማሳደግና ብድር የሚሰጡ ባንኮቹ አገልግሎቶቹ በቅርበት ቢሆን የተሻለ ስራ መስራት እንደሚችል ገልጸዋል።

ጥቅምት 10/2019 ዓ.ም ================" በእኖር ወረዳ በስራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ የወጣቶች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ ታቅዶ እየተሰራ ይገኛል።" አቶ ፈቂ ዲነካ የወረዳው ስ...
20/10/2026

ጥቅምት 10/2019 ዓ.ም
================" በእኖር ወረዳ በስራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ የወጣቶች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ ታቅዶ እየተሰራ ይገኛል።" አቶ ፈቂ ዲነካ የወረዳው ስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ

የጉራጌ ዞን ስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት መምሪያ የድጋፍ ክትትል ቡድን በወረዳው በ1ኛው ሩብ ዓመት በዘርፉ የተከናወኑ ተግባራት በመገምገም በኢንተርፕራይዝ ተደራጅተው የሚሰሩ ማህበራት የስራ እንቅስቃሴ የመስክ ምልከታ አካሂዷል።

የወረዳው ስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፈቂ ዲነካ በዚህ ወቅት እንደተናገሩት በወረዳው በስራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ የወጣቶች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ ታቅዶ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

የፕሮግራሙ ዋና አላማ ውጤታማ ስራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠልና ያጋጠሙ ክፍተቶችን ፈጥኖ በማረም የስራ ዕድል የተፈጠረላቸው ወጣቶች ተጠቃሚነት ለማሳደግ ያለመ እንደሆነም ተጠቁሟል።

በመሆኑም የድጋፍ ክትትል ቡድኑ በተቋሙ በ1ኛው ሩብ አመት የተከናወኑ ተግባራት የገመገመ ሲሆን በቀጣይ ጥንካሬዎችን እንዲጎለብቱና መሻሻል ያለባቸው ውስን ክፍተቶች እንዲስተካከሉ አመላክቷል።

ከሪፖርት ግምገማ በሗላ ቡድኑ የመስክ ምልከታ ባካሄደባቸው ከረቤት፣ጠረደና ተርሆኘ ቀበሌ በኢንተርፕራይዝ በተለያዩ ዘርፎች የተደራጁ ወጣቶች ውጤታማ ስራ በማከናወን ላይ መሆናቸውን ጠቁሟል።

የወል መሬቶችን ለወጣቶች በማመቻቸት፣የብድር አገልግሎት እንዲያገኙና ሌሎችም ድጋፎች በማድረግ እንዲያለሙ ምቹ ሁኔታ እንደተፈጠረላቸው በመስክ ምልከታ ማረጋገጡንም ቡድኑ አመላክቷል።ዘገባው የወረዳው መ/ኮ ነው።

20/10/2026

Address

Wolkite

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gurage Zone Job Creation and Enterprise Development Department posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share