Basketo Zone PP Youths Wing

Directions Website

Basketo Zone PP Youths Wing Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Basketo Zone PP Youths Wing, Political organisation, South Ethiopia, Basket, NY.

በባስኬቶ ዞን ብልፅግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ የ100 ቀናት ዕቅድ አፈጻጸም የመጀመሪያ ዙር ግምገማ ተካሄደ!በባስኬቶ ዞን ብልፅግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ ጽሕፈት ቤት የ100 ቀናት ዕቅድ አፈ...
11/10/2026

በባስኬቶ ዞን ብልፅግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ የ100 ቀናት ዕቅድ አፈጻጸም የመጀመሪያ ዙር ግምገማ ተካሄደ!

በባስኬቶ ዞን ብልፅግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ ጽሕፈት ቤት የ100 ቀናት ዕቅድ አፈጻጸምን የሚመለከት የመጀመሪያ ዙር ግምገማ አካሂዷል።

በግምገማው የ100 ቀናት ዕቅዱን ለማሳካት በተያዙ የሥራ አቅጣጫዎችና ተግባራት ላይ እስካሁን የተከናወኑ እንቅስቃሴዎች፣ የተመዘገቡ ውጤቶች፣ የታዩ ክፍተቶችና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች በዝርዝር ተገምግመዋል።

የግምገማው ዋነኛ ትኩረት የወጣቶችን ተሳትፎና አደረጃጀታዊ ተሳትፎ ማሳደግ፣ የወጣቱን የፖለቲካ ግንዛቤ ማጎልበት፣ በልማት ሥራዎች ያለውን ተሳትፎ ማስፋፋት፣ የተደራጀና ውጤታማ አሠራር መዘርጋት እንዲሁም የተቀመጡ ተልዕኮዎችን በወቅቱና በጥራት ማስፈጸም ላይ ነበር።

በውይይቱ የታዩ ጥንካሬዎችን ማስቀጠል፣ የተለዩ ክፍተቶችን በግልጽ ለይቶ ለመፍታት ተገቢ አቅጣጫ ማስቀመጥና ቀጣይ የሥራ አፈጻጸምን በተሻለ የክትትልና የድጋፍ ሥርዓት ማጠናከር የግምገማው ዋነኛ ዓላማዎች መሆናቸው ተገልጿል።

የባስኬቶ ዞን ብልፅግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወጣት ጎፋ ዋሴ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ማብራሪያ፣ በየመዋቅሩ የሚገኙ የወጣቶች ክንፍ አደረጃጀቶችን የፓርቲውን ተልዕኮ በብቃት ለመፈጸም ዝግጁ ማድረግ የወጣቶች ሥራ አስተባባሪ አካላት ቀዳሚ ተግባር መሆኑን አመላክተዋል። በተጨማሪም የግምገማው መድረክ የተመዘገቡ ጥንካሬዎችን ለማስቀጠልና ክፍተቶችን በመፍታት የቀጣይ አፈጻጸምን ለማሻሻል ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

በመድረኩ መጨረሻም በቀሪው የዕቅድ አፈጻጸም ወቅት የተለዩ ክፍተቶችን በማረም፣ የተያዙ ተግባራትን በጊዜና በጥራት በመፈጸም፣ የወጣቶችን ተሳትፎ በማጠናከርና የአፈጻጸም ክትትልን በማሻሻል የ100 ቀናት ዕቅዱን ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር በሚያስችሉ ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ የጋራ ሀሳብ ተለዋውጠዋል።

በግምገማው መድረክ የዞን፣ የወረዳዎችና የላስካ ከተማ አስተዳደር የወጣቶች ክንፍ ሥራ አስተባባሪዎችና የጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።

ህዳር 1/2019 ዓ.ም ላስካ

10/07/2026
09/29/2026
09/29/2026
‎ #አበባየሁ አትቾ(ዶክተር) ለላስካ ከተማ መሠረት የልማት ድጋፍ የሚውል 10,000 (አስር ሺህ ብር) ድጋፍ አደረጉ። ‎ ‎የላስካ ከተማ እድገትን ለማፋጠን በከተማዋ በሚከናወኑ ልማታዊ ተግ...
09/25/2026

‎ #አበባየሁ አትቾ(ዶክተር) ለላስካ ከተማ መሠረት የልማት ድጋፍ የሚውል 10,000 (አስር ሺህ ብር) ድጋፍ አደረጉ።
‎
‎የላስካ ከተማ እድገትን ለማፋጠን በከተማዋ በሚከናወኑ ልማታዊ ተግባራት ላይ ህብረተሰቡ በንቃት እንዲሳተፉ የቀረበውን ጥሪ በመቀበል አበባየሁ አትቾ(ዶክተር) 10,000 (አስር ሺህ ብር) ድጋፍ አበርክተዋል።
‎
‎የዞኑ መንግስት የከተማውን ልማት ለማፋጠን እየተደረገ ላለው ድጋፍ በህዝብ ስም ምስጋና ተችሮታል።
‎
‎የላስካ ከተማ እድገትን ለማፋጠ በእውቀት፣ በክህሎት፣ በጉልበትና በገንዘብ አስተዋፅኦ በማበርከት እርስዎም ታርካዊ አሻራዎን ያኑሩ።

የላስካ ከተማ ኮሪደር ልማት ገቢ ማሰባሰቢያ አካውንት ቁጥር ፦ 1000799926435
‎
‎

📰   !በትጋት፣ በታታሪነትና በተሰጠውን ኃላፊነት በብቃት የመወጣት ተሞክሮ ያለው ወጣት ይሉሃል ታደሴ፣ ቀደም ሲል በባስኬቶ ዞን ወጣቶች ክንፍ የሥራ አስተባባሪ ኮሚቴ አባል በመሆን ያገለገለ...
09/03/2026

📰

!

በትጋት፣ በታታሪነትና በተሰጠውን ኃላፊነት በብቃት የመወጣት ተሞክሮ ያለው ወጣት ይሉሃል ታደሴ፣ ቀደም ሲል በባስኬቶ ዞን ወጣቶች ክንፍ የሥራ አስተባባሪ ኮሚቴ አባል በመሆን ያገለገለ ሲሆን፣ በተለያዩ የወጣቶችና የማህበረሰብ ሥራዎች ላይ በትጋትና በታታሪነት ሲያገለግል ቆይቷል።

ይህንን የሥራ ተሞክሮና ታታሪነት በመመልከት፣ ወጣት ይሉሃል ታደሴ የባስኬቶ ዞን ላስካ 01 ቀበሌ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆኖ እንዲያገለግል የሥራ ኃላፊነት (ሹመት) ተሰጥቶታል።

ታታሪነት የስኬት መሠረት፣ ኃላፊነት ደግሞ የታማኝነት መገለጫ ነው!



ባስኬቶ ዞን ወጣቶች ክንፍ ኮሙኒኬሽን

⚠️  ለባስኬቶ ዞን ላስካ ከተማ ነዋሪዎች በሙሉየላስካ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ ከተጀመረበት ለረዥም ጊዜ መቆየቱ ይታወቃል።ነገርግን በአሁኑ ወቅት የውሃ ፕሮጀክቱ የሙከራ ሥራ (Testin...
08/31/2026

⚠️

ለባስኬቶ ዞን ላስካ ከተማ ነዋሪዎች በሙሉ

የላስካ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ ከተጀመረበት ለረዥም ጊዜ መቆየቱ ይታወቃል።

ነገርግን በአሁኑ ወቅት የውሃ ፕሮጀክቱ የሙከራ ሥራ (Testing) እየተካሄደ ይገኛል። በመሆኑም በሙከራ ሂደቱ ምክንያት ወደ የውሃ ቦኖዎች የሚደርሰው ውሃ ለመጠጥ የተፈቀደና የጥራት ማረጋገጫ ያገኘ ውሃ አይደለም ፣ በመሆኑ እስኪረጋገጥ ድረስ ለመጠጥ እንዳትጠቀሙበት በአክብሮት እናሳስባለን።

በተለይም ውሃው በታንከሮች ውስጥ ለረዥም ጊዜ ተከማችቶ የቆየ በመሆኑ፣ በአሁኑ ወቅት ለመጠጥ ሳይሆን ለሌሎች የቤት ውስጥ አገልግሎቶች ብቻ እንድትጠቀሙ እናሳስባለን።

⚠️ አስፈላጊ ማሳሰቢያ

ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ፣ የውሃው ጥራት ተረጋግጦ ለመጠጥ ተስማሚ መሆኑ ሲረጋገጥ፣ ለመጠጥ መጠቀም መቻሉን በይፋ እናሳውቃለን።

ስለሆነም ሁሉም ነዋሪ ለራሱና ለቤተሰቡ ጤና ሲል ይህንን የጥንቃቄ መልዕክት እንዲያከብር እንጠይቃለን።

ኢንጅነር በዛብህ ገበየሁ
የባስኬቶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ
ላስካ

Address

South Ethiopia
Basket, NY

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Basketo Zone PP Youths Wing posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share