PP Star Youth Wing

PP Star Youth Wing PP Star youth wings

11/11/2026

ከተደመርን ዛሬ ለእኛ ነገ ለልጆቻችን የምትሆንና የምታጓጓ አፍሪካን መፍጠር እንችላለን።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር)

10/11/2026
09/11/2026

ኢትዮጵያ፡ ከራስ አቅም ልማት እስከ አፍሪካዊ የብልጽግና ተምሳሌትነት

ኢትዮጵያ የራስን ሀብት መጠቀምና መበልጸግ እንደሚቻል ባለፉት ዓመታት ባከናወነቻቸው የልማት ስራዎች አረጋግጣለች፡፡ በተለይም በሕዳሴ ግድብ የውጭ ጫናን በመቋቋም የራስን አቅምና የተፈጥሮ ሃብት በማስተባበር ወደ ልማት መቀየር የቻለችበትም ነው፡፡ ከቀጠናው አገራት አልፎ መላ አፍሪካን በሃይል አቅርቦት ፣ በመሰረተ ልማት ፣ በንግድ ለማስተሳሰር ያከናወነቻቸው ተግባራት ምስክሮች ናቸው።

በስንዴ ልማት ፣ በማዕድን ዘርፍ፣ በዲጅታል ኢትዮጵያ ፣ በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እንዲሁም በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በብልጽግና ፓርቲ የሚመራው የመደመር መንግስት አገር በቀል እሳቤ በመምራት ኢትዮጵያ የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት የማድረግ ራዕይ ይዞ በመንቀሳቀስ ተጨባጭ ውጤቶችን ማስመዘገብ ተችሏል፡፡

ኢትዮጵያ በኮሪደር ልማት፣ በፕሮጀክት አፈጻጸም፣ በከተማ ልማት ፣ በታዳሽ ሃይል ልማት አንዲሁም በፖለቲካዊ ተሳትፎ ኢትዮጵያ ለሌሎች የአፍሪካ አገራት ተምሳሌት መሆን የምትችል ናት፡፡

በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከ48 ቢሊየን በላይ አገር በቀልና ለምግብነት የሚውሉ ችግኞችን በመትከል የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ እያስመዘገበ ያለችው ውጤት ዓለም አቀፍ እውቅና የተሰጠው እና ለአህጉሪቷም ተምሳሌት የሚሆን ነው፡፡

በአገራችን ነጻ፣ ፍትሃዊና ዴሞክራሲ ምርጫ በማካሄድ እንዲሁም ከ54 ሚሊየን በላይ ኢትዮጵያውያን ከጠዋት እስከ ማታ ድረስ በመሰለፍ ለአገራቸው ሀገረ መንግስት ግንባታ ያላቸውን ቁርጠኝነት ያሳዩበት የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎች በማሳተፍ በአገራቸው የዴሞክራሲ እድገት ላይ የራሳቸው አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚችሉ አንዱ ማሳያ ነው ፡፡

ከሰሞኑ በአገራችን የተካሄደው ሁለተኛው የአፍሪካ የፓለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ ፓርቲዎች ወቅት እየጠበቁ በምርጫ ከመሳተፍ ባለፈ ተጨባጭ የሕዝብ መሠረታዊ ችግሮችን በመፍታትና በአገራዊ ልማት በመሳፍ የበኩላቸውን መወጣት እንዲችሉ እንዲሁም አፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ ምላሽ መስጠት ያላቸው ሚና ተቋማዊ በሆነ መንገድ መፍታት ሚቻልበት ሁኔታ በማመቻቸት አይነተኛ ሚና ይጫወታል፡፡

ብልጽግና ፓርቲ በዚህ ጉባኤ ላይ የተወሰኑ የአዲስ አበባ ቃልኪዳን እና የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ኢንሸቲቭን ለቀጣይ ሶስት ዓመት በማስፈጸምና ተግባራዊነቱን በመወጣት ኢትዮጵያ የአፍሪካ የስልጣኔ ማማ ፈር ቀዳጅነቷን የምታስመሰክርበት ይሆናል፡፡

09/11/2026

ወደ ፤ #ከአንታሊያ እስከ
++++++++++++
ኢትዮጵያ በCOP31 ላይ የምታደርገው ተሳትፎ በዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ዲፕሎማሲ መድረክ ላይ የምታሳየው ተሳትፎ ብቻ ሳይሆን፣ ለCOP32 አዘጋጅነት ያበቋትን የልማት ስኬቶች፣ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታና የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም እየተከተለች ያለውን ተግባራዊ አቅጣጫ ለዓለም የምታስተዋውቅበት ታላቅ አጋጣሚ ነው።

COP32 አስተናጋጇ የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የCOP31 ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ቱርክ አንታሊያ ገብተዋል።

ከንቲባ አዳነች በአንታሊያ ቆይታቸው ከተለያዩ ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥ ተደራዳሪ ቡድኖችና ከአጋር አካላት ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። አዲስ አበባም የአየር ንብረት ለውጥን ተፅዕኖ ለመቋቋም ያደረገችውን ከፍተኛ አስተዋጾኦ ለሌሎች ሀገራት ልምዷን ታካፍላለች፡፡

በቱርክዋ አንታሊያ በሚካሄደው COP31 ኢትዮጵያ ለCOP32 የምትወስዳቸው ግብዓቶች በቀጣይ የሚኖራትን ዝግጅት ከማጠናከር ባለፈ፣ በዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ድርድሮች፣ በአረንጓዴ ፋይናንስ ማሰባሰብ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በንጹህ ኃይል ልማትና በአየር ንብረት መቋቋም አቅም ግንባታ ዙሪያ ያላትን ልምድና አቅም እንድታሳድግ ዕድል ይፈጥራል።

ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር፣ በታዳሽ ኃይል ልማት፣ በደን ልማትና ጥበቃ፣ በአፈርና ውሃ ጥበቃ፣ በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታና በአየር ንብረት መከላከያ እያከናወነች ያለችው ሥራዎች በCOP31 ላይ በተግባር ለዓለም ሊቀርቡ የሚችሉ ተሞክሮዎች ናቸው።

የCOP32 አስተናጋጇ አዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤም በውይይታቸው በአዲስ አበባ በቀጣይ የሚካሄደው COP32 አካታች፣ በተግባር ላይ ያተኮረና ተጨባጭ ውጤት የሚያስገኝ እንዲሆን የጋራ መግባባትንና ትብብርን ለማጠናከር ያለሙና ከCOP31 ወደ COP32 የሚደረገውን ሽግግር ለማስቀጠል ትኩረት ያደርጋሉ

ኢትዮጵያ ከአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ጋር የምትታገል አገር ብቻ ሳትሆን፣ ለችግሩ መፍትሔ በማበርከት የራሷን ልምድና መፍትሔዎች ለዓለም ማካፈል የምትችል አገር መሆኗን ለማሳየት ያስችላል። አዲስ አበባም የአገሪቱን ስኬት በከተማ ልማት ዘርፍ የምታስመሰክርበት ወሳኝ መድረክ ይሆናል።

በወንዞች ዳርቻ ልማት፣ በኮሪደር ልማት፣ በከተማ አረንጓዴነት፣ በዘመናዊ የትራንስፖርት መሠረተ ልማትና በሕዝብ መዝናኛ ስፍራዎች ግንባታ እየተከናወኑ ያሉት ለውጦች ከከተማ ውበት ባለፈ የአካባቢ ጥበቃን፣ የኑሮ ጥራትንና ዘላቂ የከተማ ልማትን ያማከሉ፤ ተግባራዊ ምሳሌዎች ናቸው።

ኢትዮጵያ የCOP32 አዘጋጅ አገር እንድትሆን መመረጧም ከአንድ የጉባኤ አዘጋጅነት ኃላፊነት በላይ ትርጉም አለው።
ይህ ምርጫ በአህጉራዊና ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ዲፕሎማሲ ውስጥ ኢትዮጵያ ያላትን ሚና፣ የአረንጓዴ ልማት አቅጣጫዋንና ታላላቅ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎችን የማዘጋጀት ልምዷን የሚያንጸባርቅ እድል ነው።

በ2025 የሁለተኛውን የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ በአዲስ አበባ ማስተናገዷ ለዚህ አዲስ ኃላፊነት ያላትን የዝግጅትና የትብብር ልምድ የሚያጠናክር ነው። በመሆኑም COP31 ኢትዮጵያ ከዓለም ለመማር፣ አዳዲስ የትብብር አጋሮችን ለማፍራት፣ የአየር ንብረት ፋይናንስና ቴክኖሎጂ ተደራሽነቷን ለማሳደግ እንዲሁም ለCOP32 የምታዘጋጀውን አጀንዳ ለማጠናከር የሚያስችላት ወሳኝ የዝግጅት መድረክ በመሆኑ፤ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የCOP32 ተመራጭ ፕሬዝዳንት እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) እና ሌሎችም ልኡካን ከተለያዩ ተቋማት ጋር ውይይቶችን እያደረጉ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ።

የCOP32 አዘጋጅነት ዓለምን ማስተናገድ ብቻ ሳይሆን፣ የአፍሪካን የአየር ንብረት ጥያቄዎች፣ የመፍትሔ ሐሳቦችና የልማት ተሞክሮዎች በዓለም አቀፍ ውይይት ውስጥ ቦታ እንዲያገኙ ማስቻልም ጭምር ነው። COP31 ለCOP32 ዝግጅት መሠረት ሲሆን፣ በCOP32 የምናቀርበው ደግሞ የኢትዮጵያንና የአፍሪካን የተግባር ስኬት፣ ምኞትና የወደፊት ራዕይ ይሆናል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት፤ በመደመር እሳቤ በመመራት የአረንጓዴ ልማት ስራዎቿ የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም እንደሚቻል በአለም አቀፍ መድረኮች ያሳየችው ሀገራችን ከCOP31 ተሞክሮ ወደ COP32 ዓለም አቀፍ አጀንዳ፤ ከኢትዮጵያ የአረንጓዴ ልማት ተሞክሮ ወደ ዓለም የጋራ መፍትሔም ትሸጋገራለች!

07/11/2026

ብልፅግና የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ኢኒሺዬቲቭን እንዲመራ ተመረጠ

| ​ብልፅግና ፓርቲ የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ኢኒሺዬቲቭን (APPI) በበላይነት እንዲመራ በሙሉ ድምፅ መመረጡ ተገለጸ።

ፓርቲው ይህንን ትልቅ አህጉራዊ ኃላፊነት የተረከበው በአዲስ አበባ በሚገኘው ታሪካዊው የዓድዋ ድል መታሰቢያ በተካሄደው ሁለተኛው የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባዔ ላይ ነው።

​"ዕድገትን መምራት፤ ፖለቲካ ፓርቲዎች እንደ የአፍሪካ መጻኢ ኢኮኖሚ መሃንዲሶች" በሚል መሪ ሀሳብ በተካሄደው በዚህ አህጉራዊ መድረክ፣ የአፍሪካን የወደፊት የኢኮኖሚና የዕድገት አቅጣጫ በመቅረጽ ረገድ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚጫወቱት ወሳኝ ሚና ሰፊ ትኩረት አግኝቷል።

በጉባዔው ላይ የተሳተፉት የአህጉሪቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ብልፅግና ፓርቲ ይህንን የጋራ ተነሳሽነት (ኢኒሺዬቲቭ) በበላይነት እንዲመራ በሙሉ ድምፅ የመረጡት ሲሆን፣ ይህም በፓርቲው የአመራር ብቃትና ራዕይ ላይ ያላቸውን ከፍተኛ እምነት ያሳየ ክስተት ሆኗል ተብሏል።

​ይህ የመሪነት ምርጫ ብልፅግና ፓርቲ በአፍሪካ ደረጃ እያደረገ ያለውን ንቁ የዲፕሎማሲና የፖለቲካ ተሳትፎ እንዲሁም እያገኘ የመጣውን አህጉራዊ እውቅና አጉልቶ የሚያሳይ ተደርጎ ተወስዷል።

ፓርቲው የተሰጠው ይህ አዲስ ኃላፊነት በአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ያለውን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከርና የአህጉሪቱን የጋራ የኢኮኖሚ ልማት ራዕይ እውን ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የጎላ ሚና እንዲጫወት ሰፊ ዕድል ይፈጥርለታል።

05/11/2026

"የበለፀገችና ጠንካራ አፍሪካን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ዉስጥ የአህጉሪቱ ወጣቶች በፖሊሲ አውጪነትና በመንግሥት ሥልጣን ደረጃ ንቁ ተሳታፊ ሊሆኑ ይገባል"

የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር አክሊሉ ታደሰ (ዶ/ር)

02/11/2026
31/10/2026

“ወታደሮች ዒላማ፤ ሲቪሎች ደግሞ ዓላማ አላቸው፡፡ የሁለቱም ግብ ድልን ማስመዝገብ ነው፡፡ ሁለቱን ዲሲፕሊኖች በማገናዘብ ዒላማውንም የሚመታ፤ ዓላማውንም የሚያሳካ ትውልድ እንፈጥራለን፡፡”

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when PP Star Youth Wing posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share