Bahir Dar International Stadium Center

Call Directions Website

Bahir Dar International Stadium Center This is the official page of Bahir dar international stadium center LETS DO !!!

ድንቅ ፋክክር፤ምርጥ ደጋፊ፤በታላቁ ባህርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየምፋሲል ከነማ 2-2 ባህርዳር ከነማ
31/10/2026

ድንቅ ፋክክር፤
ምርጥ ደጋፊ፤
በታላቁ ባህርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም
ፋሲል ከነማ 2-2 ባህርዳር ከነማ

የስታዲየም መግቢያ በሮች ጥቆማጥቅምት 20/2019 ዓ.ምተጠባቂው የአማራ ደርቢ በፋሲል ከነማ እና በባህርዳር ከተማ መካከል ነገ ጥቅምት 21/2019 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 በባህርዳር ዓለም አቀ...
30/10/2026

የስታዲየም መግቢያ በሮች ጥቆማ
ጥቅምት 20/2019 ዓ.ም

ተጠባቂው የአማራ ደርቢ በፋሲል ከነማ እና በባህርዳር ከተማ መካከል ነገ ጥቅምት 21/2019 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 በባህርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ይካሄዳል።

በእለቱ የደጋፊዎችን መጨናነቅ እና እንግልት ለመቀነስ ከዚህ በታች በተጠቀሱት የስታዲየም የመግቢያ በሮች እንድትጠቀሙ እናሳውቃለን።

1. በር ቁጥር 1 (በሳፋሪ በኩል)
-የሁለቱ ክለብ ተጫዋቾች የጨዋታ ዳኞች፣የውድድር አመራሮች፣ ሚዲያ፣ VIP እና VVIP እንግዶች የመግቢያ በር ሲሆን

2. ፕላዛ በር (በዲላኖ ሆቴል ፊት ለፊት)
-የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች መግቢያ

3. በአዘዋ ሆቴል እና በአመዶ ገበያ ባሉት በሮች
-የባህርዳር ከነማ ደጋፊዎች መግቢያ ይሆናል

#ወደ ዋናው የስታዲየም መቀመጫዎች መግቢያ በሮች ደግሞ፦
- ደረጃ አንድ VIP = 1000 ብር
መግቢያ በር VIP ለሁለቱም ክለቦች

- ደረጃ ሁለት premium = 500 ብር
መግቢያ በር ቁጥር 2 ለፋሲል ከነማ ደጋፊ
መግቢያ በር ቁጥር 1 ለባህር ዳር ከነማ ደጋፊ

- ካታጎሪ 3 ከሁለቱ ጎል ጀርባ = 300 ብር
መግቢያ በር ቁጥር 3, 4, 5 እና 6 ለፋሲል ከነማ ደጋፊ
መግቢያ በር ቁጥር 9, 10, 11 እና 12 ለባህር ዳር ከነማ ደጋፊ
- ካታጎሪ 2 = 200 ብር
መግቢያ በር ቁጥር 7 ለፋሲል ከነማ ደጋፊ
መግቢያ በር 8 ለባህርዳር ከነማ ደጋፊ

መልካም ጨዋታ ለሁለቱም ክለቦች!!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ጋር በመኾን የባሕርዳር ስታዲየምን ጎበኙ። ጥቅምት 14/2019ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በማኅበራዊ ትስስር ገ...
24/10/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ጋር በመኾን የባሕርዳር ስታዲየምን ጎበኙ።
ጥቅምት 14/2019

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት 12ኛውን የጣና ፎረም ከታደምን በኋላ ከአፍሪካ መሪዎች እና ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር በመኾን ባሕር ዳር ስታዲየም ጎብኝተናል ብለዋል።

ጉብኝቱ በስፖርት መሠረተ ልማት ረገድ ያለውን መሻሻል፣ ባሕር ዳር ለስፖርት፣ ለቱሪዝም እና ቀጣናዊ ትብብር ማዕከል የሚያደርጋትን ትልቅ አቅም ለመመስከር ዕድል የሚሰጥ ነበር ነው ያሉት
አሚኮ

Thank you Bahir Dar
30/09/2026

Thank you
Bahir Dar

‎     ‎🏟️ውጤቱ ያላደበዘዘው የባሕር ዳር ስታዲየም ደማቅ ድባብ✨ ‎‎የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግዙፍ ገጽታ እና ማራኪ ቁመና በእርግጥም ኢትዮጵያ እግር ኳስን ሌላው መገለጫዋ፣ የ...
29/09/2026

‎
‎🏟️ውጤቱ ያላደበዘዘው የባሕር ዳር ስታዲየም ደማቅ ድባብ✨
‎
‎የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግዙፍ ገጽታ እና ማራኪ ቁመና በእርግጥም ኢትዮጵያ እግር ኳስን ሌላው መገለጫዋ፣ የኢኮኖሚዋ አቅም ማሳያ እና የቱሪዝሟ የስበት ማዕከል ለማድረግ እየጣረች ለመኾኑ ምስክር ነው።
‎
‎ባለግርማ ሞገሱ ስታዲየም ከበርካታ የናፍቆት ዓመታት በኋላ የመጀመሪያውን አሕጉራዊ ጨዋታ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በማስተናገድ ዳግም ወደ ሕይወት ተመልሷል።
‎
‎🏆 ወደ ቀደመ ክብሩ ለመመለስ
‎የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) የካፍን መስፈርት ባለማሟላት ምክንያት ለዓመታት ከሜዳው እና ከደጋፊው ርቆ በባዕድ ሀገር ሲያደርገው የነበረው አሰልቺ የውድድር ጉዞ አብቅቷል። ዛሬ በጣና ዳርቻ በሚገኘው እና ደጋፊነትን ጠንቅቀው በሚያውቁት እውነተኛ የእግር ኳስ ቤተሰቦቹ ታጅቦ ወደ ቀደመ ክብሩ ተመልሷል።
‎
‎🔥 የደጋፊው አስደናቂ ድባብ
‎ስታዲየሙ ጥግ እስከ ጥግ ድረስ በሀገር ፍቅር ስሜት በነደዱ፣ የብሔራዊ ቡድኑን ማልያ በለበሱ እና የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ባነገቡ ደጋፊዎች ሙሉ በሙሉ ተጨናንቆ ውሏል።
‎
‎አረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ ቀለማት በስታዲየሙ የክብር ትሪቡኖች ላይ እንደ ማዕበል ሲወዛወዙ፣ ከየአቅጣጫው የሚሰማው የደጋፊው የማያቋርጥ የድጋፍ ጩኸት ልዩ ነበር።
‎
‎ጆሮን የሚያደነቁር ግን ደግሞ ልብን በሀገራዊ ስሜት የሚያሞቅ የደጋፊዎች ድምጽ ለዓመታት የታመቀውን እና የተጠራቀመውን የብሔራዊ ቡድኑን የአሸናፊነት ጥማት እና የድል ፍላጎት በከፍተኛ ድምቀት የሚያስተጋባ ነው።
‎
‎ተጫዋቾች ኳስን በሚነኩበት ቅጽበት ሁሉ የሚሰማው የደጋፊው የጋለ ትንፋሽ ለተጫዋቾቹ ተጨማሪ ጉልበት በመኾን የአስራ ሁለተኛ ተጫዋችነት ሚናውን በሚገባ ተወጥቷል።
‎
‎🌟 ከውጤት የዘለለ ትርጉም
‎ምንም እንኳን የጨዋታው ውጤት በሴኔጋል 1 ለ0 አሸናፊነት ቢጠናቀቅም የዕለቱ ትዕይንት ግን ከዘጠና ደቂቃ የእግር ኳስ ፉክክርም የዘለለ ጥልቅ ትርጉም አለው። የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ዛሬ የውድድር ማዕከል ብቻ አልኾነም። የኢትዮጵያውያን አንድነት፣ የማይበገር የእግር ኳስ ፍቅር እና ሀገራዊ ኩራት በግዙፍ ድምጽ የተዘመረበት ታላቅ መድረክ ኾኖ ውሏል።
‎
‎በአጠቃላይ የደጋፊው እያንዳንዱ እንቅስቃሴ፣ ጭብጨባ እና ዜማ የሀገሪቱን እግር ኳስ ወደ አዲስ ምዕራፍ ለማሸጋገር ያለውን የጋለ ስሜት እና ተስፋ አጉልቶ የሚያሳይ ነው።
አሚኮ

የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ባህርዳር ከተማ ገብቷል
28/09/2026

የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ባህርዳር ከተማ ገብቷል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የመጀመርያ ልምምዱን አከናውኗል።በ2027 አፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ሁለተኛ የምድብ ጨዋታ ሴኔጋልን የሚገጥመው ብሔራዊ ቡድናችን ትናንት...
27/09/2026

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የመጀመርያ ልምምዱን አከናውኗል።

በ2027 አፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ሁለተኛ የምድብ ጨዋታ ሴኔጋልን የሚገጥመው ብሔራዊ ቡድናችን ትናንት ጨዋታውን ወደሚያደርገበት ወደ ባህር ዳር ማቅናቱ የሚታወስ ሲሆን በዛሬው ዕለትም ከ10፡00 ጀምሮ ልምምዱን አከናውኗል።
EFF

የኢትዮጵያ እና ሴኔጋል ጨዋታ የስታዲየም መግቢያ ቲኬት ባሉበት ሆነው በኦንላይን ይቁረጡ !ማክሰኞ መስከረም 19 ከቀኑ 10፡00 የሚካሄደው ጨዋታ የስታዲየም መግቢያ ቲኬት  eff-tickets...
25/09/2026

የኢትዮጵያ እና ሴኔጋል ጨዋታ የስታዲየም መግቢያ ቲኬት ባሉበት ሆነው በኦንላይን ይቁረጡ !

ማክሰኞ መስከረም 19 ከቀኑ 10፡00 የሚካሄደው ጨዋታ የስታዲየም መግቢያ ቲኬት eff-tickets.com ላይ በመግባት በገፁ ላይ በቅደም ተከተል የተቀመጡትን መመርያዎች በማሟላት መግዛት ይችላሉ።

የቲኬት ዋጋ
ፕሪምየም ደረጃ 500 ብር
ካቴጎሪ 2 ደረጃ 200 ብር
ካቴጎሪ 3 ደረጃ 100 ብር

በካፍ የጨዋታ ደህንነትና ጥበቃ ደንብ (Safety and Security Regulation) ዙሪያ ለስቲዋርድ (STEWARD) አባላት ስልጠና መሰተጠት ተጀመረ።መስከረም 7/2019 ዓ.ምየኢትዩጵ...
17/09/2026

በካፍ የጨዋታ ደህንነትና ጥበቃ ደንብ (Safety and Security Regulation) ዙሪያ ለስቲዋርድ (STEWARD) አባላት ስልጠና መሰተጠት ተጀመረ።
መስከረም 7/2019 ዓ.ም

የኢትዩጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሴኔጋል አቻው ጋር ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በባህርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ለሚያደርጉት ጨዋታ የፀጥታ ስራውን ለሚመሩ የስቲዋርድ (STEWARD) አባላት ስልጠና እየተሰጠ ነው።

ውድድሩን በካፍ የውድድርና ደህንነት ህግ መሰረት ለመምራት እንዲቻል መሰረታዊ የደህንትና ጥበቃ (Safety and Security) ስልጠና እና የተግባር ላይ ልምምድ ከፀጥታ አካላትና በጎ-ፈቃደኛ ወጣቶች ለተውጣጡ ስቲዋርድ አባላት እየተሰጠ ነው።

በስልጠናው ማስጀመሪያ የተገኙት የአብክመ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ አማካሪ አቶ አዱኛ ይግዛው እንደተናገሩት ይህ ውድድር ከ5 ዓመታት በኋላ ወደከተማችን የመጣ በመሆኑ ጠቀሜታው ከፍተኛ ነው ብለዋል። ስልጠናውም የካፍን የደህንነትና ጥበቃ ህግ አተገባበር በመገንዘብ ጨዋታውን ለመምራት የሚያግዝ በመሆኑ በልዩ ትኩረት ክትትል ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ስልጠናው ለሁለት ቀናት የሚሰጥ ሲሆን የተግባር ላይ ልምምድም እንደሚደረግ ታውቋል።

የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ
05/06/2026

የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ

Address

Bahirdar
Bahir Dar

Telephone

+251582202202

Website

and sport face book.

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bahir Dar International Stadium Center posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share