Ethiopian Biodiversity Institute - EBI

Website Contact the organization

Ethiopian Biodiversity Institute - EBI Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethiopian Biodiversity Institute - EBI, Government Organization, Addis Ababa, Ababa.

We ensure that the country’s biodiversity and the associated community knowledge are properly conserved and sustainably utilized, and the country and its communities get fair and equitable share of the benefits arising from their utilization.

01/11/2026

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1 FM)
ጥቅምት 21 2019

ኢትዮጵያ ውስጥ በሚካሄደው የኮፕ 32 የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ አለማቀፍ የሀይማኖት ተቋማትን በጉባኤ እንዲሳተፉ ለማድረግ እየተሰናዳ መሆኑን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የልማና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ተናገረ፡፡

ይህ የሚደረገው ከጉባኤው ዋና አዘጋጅ ጋር በመተባበር መሆኑን ተጠቅሷል፡፡

በኮሚሽኑ የሰብአዊ እርዳታዎች ዋና ኃላፊ ገብረስላሴ አፅብሃ ከዓመት በኋላ በሚደረገው ኣለማቀፉ ጉባኤ የሀይማኖት ተቋማት በዚህ ዙሪያ እንዲመካከሩ ለማድረግ ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን ነግረውናል፡፡

በኢትዮጵ ኦርቶዶክስር ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚገኙ ደኖች በአመት በርካታ ካርበን አምቀው ይይዛሉ፣ ከፋይናንስ አኳያ ግን ተጠቃሚ አይደሉም ብለዋል፡፡

አያይዘውም ህዝቡ ባለበት የኢኪኖሚ ችግር ምክንያት አንዳንዴ ደኖችን ሲቆርጥ ይታያል ያሉ ሲሆን ይህንን ለማስተካከል አማራጭ የስራ ዘርፎች ላይ እንዲሰማሩ ለማድረግ እንደሚሞከር ነገውናል፡፡

ደኖቹን የተሻለ በአለም እንዲታወቁ ለማድረግ ከኢትዮጵያ ብዝሃ ህይወት ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር የቤተክርስቲያን ደኖች በዩኔስኮ ለማስመዝገብ ስራዎች እየተሰራ ነው ያሉ ሲሆን በአርሲ የሚገኘው የአቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም ደን በዩኔስኮ ለመመዝገብ የመጨረሻው ደረጃ መድረሱን ጠቁመዋል፡፡

በኮሚሽኑ ከፍተኛ የአየር ንብረት ባለሙያ ተዋናይ ሰይፈስላሴ የሰው ቁጥር እየበዛ በመምጣቱ የተፈጥሮ ሃብት ከፍተኛ አደጋ ውስጥ እንዲገባ እያደረገ ነው ይላሉ፡፡

የእምነት ተቋማት ሀይማኖታዊ አስተምህሯቸውን በመጠቀም ደኖች እንዲጠበቁ ለማድረግ አቅማቸው ሰፊ ነው በማለት ያብራራሉ፡፡

ማህበረሰቡ በደኖች አካባቢ ሲኖር አማራጭ ቴክኖሎጂ ለኑሮው ማስኪኬጃ አስፈላጊ ነው በዚህም ዙሪያ ኮሚሽኑ በስፋት እንደሚሰራም አብራርተዋል፡፡

ባለፈው በተካሄደው የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ የሃይማኖት ተቋማትን በጉባኤው እንዲሳተፉ ከመንግስት ጋር በመሆን የማስተባበር ስራ መሰራቱን የጠቀሱ ሲሆን በኮፕ 32 የአየር ንብረት ጉባኤ ላይም የሀይማኖት ተቋማት በስብሰባው ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ ከጉባኤው አዘጋጆች ጋር በመሆን የማስተባበር ስራ ለመስራት እየተሰናዳ መሆኑን ነው የነገሩን፡፡

በረከት አካሉ

የኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት በሳይንስ ሙዚየም ካቀረበው ኤግዚቢሽን ላይ የተወሰደ
30/10/2026

የኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት በሳይንስ ሙዚየም ካቀረበው ኤግዚቢሽን ላይ የተወሰደ

ከለጋሽ ድርጅት ልኡካን ጋር ውይይትና ጉብኝት ተካሄደየኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት ከለጋሽ ድርጅት ልኡካን ጋር ጥቅምት 18 ቀን 2019 ዓ.ም ውይይትና ጉብኝት አካሄደ፡፡አቶ አበራ ስ...
28/10/2026

ከለጋሽ ድርጅት ልኡካን ጋር ውይይትና ጉብኝት ተካሄደ
የኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት ከለጋሽ ድርጅት ልኡካን ጋር ጥቅምት 18 ቀን 2019 ዓ.ም ውይይትና ጉብኝት አካሄደ፡፡
አቶ አበራ ስዩም የኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር ተወካይ እና የደንና ግጦሽ መሬት እጽዋት ብዝሀ ሕይወት ምርምር መሪ ሥራ አስፈጻሚ ለለጋሽ ድርጅት ልኡካን የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈው ስለ ኢንስቲትዩት አጠቃላይ መረጃዎችን አቅርበዋል፡፡ አያይዘውም በደንና ግጦሽ እጽዋት ብዝሀ ሕይወት ምርምር ክፍል ያጋጠሙ ማነቆዎችን ዘርዝረው አሁን በስራ ክፍሉ በመከናወን ላይ ያለዉ ፕሮጀክት ያሉብንን ክፍተቶች መሙላት የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል። ለለጋሽ ድርጅት(በKFW) እና ስራው ላይ ለተሳተፉ አካላት በሙሉም በኢንስቲትዩቱ ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የደን ጂን ባንክ፣ የላቦራቶሪ፣ የእጽዋት ቤተ-መዘክርና እና የዘር ማድረቂያ ክፍል እድሳትና ተያያዥ የግብዓት አቅርቦት ያሉበትን ደረጃ በባለሙያዎች ማብራሪያ የቀረበ ሲሆን የጀርመን ልማት ባንክ ተወካዮች Dr. Jochen, KfW Development Bank, Head of Division, Biodiversity & Agriculture-West & East Africa እና Dirk Wenzel, KfW Development Bank, Senior Engineer (Principal), Biodiversity and Agriculture. West and East Africa የማብራሪያ ጥያቄ አቅርበው ምላሾች ተሰጥተዋል፡፡
የለጋሽ ድርጅት ልኡካን የደን ጂን ባንክ እድሳት እና የግብዓት አቅርቦት ያለበትን ደረጃ ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን በፕሮጀክቱ ድጋፍ በተከናወኑት ተግባራት ደስተኞች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ በኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት የደን የጂን ባንክ እድሳት እየተከናወነ የሚገኘው በkfw ድጋፍ መሆኑ ይታወሳል፡፡

Ethiopia Shares Its Experience in Developing the ABS Easy Guide at COP17 in ArmeniaEthiopia shared its experience in dev...
26/10/2026

Ethiopia Shares Its Experience in Developing the ABS Easy Guide at COP17 in Armenia

Ethiopia shared its experience in developing the Access and Benefit-sharing (ABS) Easy Guide during a panel discussion at the seventeenth meeting of the Conference of the Parties to the Convention on Biological Diversity (COP17), held in Yerevan, Armenia.

Ethiopia is among the few countries that have developed an ABS Easy Guide with support from the Japan Biodiversity Fund, under the Secretariat of the Convention on Biological Diversity (C*D), in collaboration with Leibniz Institute DSMZ.

During the panel discussion, Million Adane Daba, Ethiopia’s National Focal Point for the Nagoya Protocol on Access and Benefit-sharing, served as a panellist and shared Ethiopia’s experience in developing the guide with representatives from other selected countries.

The ABS Easy Guide is intended to help users better understand access to genetic resources and the fair and equitable sharing of benefits arising from their utilization. Ethiopia’s experience provides an opportunity to exchange knowledge and lessons with other countries working to strengthen the implementation of the Nagoya Protocol.

The Ethiopian Biodiversity Institute (EBI) continues to support the implementation of the Nagoya Protocol and efforts to improve understanding of Ethiopia’s ABS framework.

ብዝሀ ህይወት ለምርምርና ለልማት
26/10/2026

ብዝሀ ህይወት ለምርምርና ለልማት

25/10/2026

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የብዝሀ ህይወት ስምምነት መድረክ COP 17 በመሳተፍ ላይ ትገኛለች። የልዑካን ቡድኑ መሪ ዶ/ር ተስፉ ፈከንሳ ያስተላለፉት መልዕክት

24/10/2026
በ2019 በጀት ዓመት የአንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ዙሪያ ውይይት ተካሄደየኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት በ2019 በጀት ዓመት የአንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት...
23/10/2026

በ2019 በጀት ዓመት የአንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ዙሪያ ውይይት ተካሄደ
የኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት በ2019 በጀት ዓመት የአንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ዙሪያ ከኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች ጋር ጥቅምት 13 ቀን 2019 ዓ.ም ውይይት አካሄደ፡፡
የ2019 በጀት ዓመት የአንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በአቶ ማስረሻ የማነ የኢንስቲትዩቱ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ሥራ አስፈጻሚ የቀረበ ሲሆን የመሪ ሥራ አስፈጻሚዎች፣ የሥራ አስፈጻሚዎች፣ የሪፎርም ስራዎች፣ የካፒታል እና ፕሮጀክቶች አፈጻጸም፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና የመፍትሄ እርምጃዎች እንዲሁም ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች በዝርዝር ለውይይት ቀርበዋል፡፡
በቀረበው የአፈጻጸም ሪፖርት ዙሪያ የኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች የተለያዩ ጥያቄዎችን አቅርበው በሚመለከታቸው አካላት ተገቢ ምላሾች ተሰጥተዋል፡፡ በተጨማሪም በግብዓትነት ሊያገለግሉ የሚገባቸው ሀሳቦችና አስተያየቶች ቀርበው ተቀባይነትን አግኝተዋል፡፡
ውይይቱን አቶ አበራ ስዩም የኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት የም/ዋና ዳይሬክተር ተወካይና አቶ መኳንንት እያዩ የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊ የመሩት ሲሆን የማጠቃለያ ምላሾችን ሰጥተው ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

Address

Addis Ababa
Ababa

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:00
Tuesday 08:00 - 17:00
Wednesday 08:00 - 17:00
Thursday 08:00 - 17:00
Friday 08:00 - 17:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Biodiversity Institute - EBI posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Ethiopian Biodiversity Institute - EBI:

Shortcuts

Share

Nearby government services