Ethiopian Embassy Kampala

Call Directions Website

Ethiopian Embassy Kampala This is the official page of the Embassy of the FDR of Ethiopia in the Republic of Uganda

28/10/2026
28/10/2026
28/10/2026
28/10/2026
ታላቅ የምስራች!!           ውድ ኢትዮጵያውያን ከፓስፖርት ጋር በተገናኘ ሚሲዮኖች የሚሰጧቸው አገልግሎቶች ውስን በመሆናቸው ዜጎች ግዴታ አገር ቤት በመሄድ ሂደቱን ማጠናቀቅ ይጠባቅባቸው...
24/10/2026

ታላቅ የምስራች!!

ውድ ኢትዮጵያውያን ከፓስፖርት ጋር በተገናኘ ሚሲዮኖች የሚሰጧቸው አገልግሎቶች ውስን በመሆናቸው ዜጎች ግዴታ አገር ቤት በመሄድ ሂደቱን ማጠናቀቅ ይጠባቅባቸው ነበር ይታወቃል፡፡ ሂደቱ ዜጎችን ለተጨማሪ ወጪ፣የጊዜ ብክነት እንዲሁም ለአላስፈላጊ ለመጉላላት ሲዳርጋቸውም ቆይቷል፡፡

በመሆኑም መንግስት ይህን ታሳቢ በማድረግ በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት መ/ቤት የሚሰጡ አገልግሎቶችን ዲጂታላይዝ በማድረግ በውጭ አገር በሚገኙ ሚሲዮኖች ሙሉ በሙሉ እንዲሰጡ በመሰን ወደ ስራ ተግብቷል፡፡

ሚሲዮናችንም ይህን አዲስ አገልግሎት አሰጣጥ መተግበር መጀመሩን እያበሰርን፣ በአዲሱ አሰራር ተጠቅመው ፓስፖርት ለማደስ ያመለከቱ አንድ ዜጋችን የመጀመሪያውን የታደሰ ፓስፖርት ዛሬ ጥቅምት 13 ቀን 2019 ዓ.ም. ከሚሲዮኑ መሪ ክብርት አምባሳደር እጸገነት በዛብህ ይመኑ እጅ ተቀብለዋል፡፡

በርክክብ ስነስርዓቱ ላይ ክብርት አምባሳደር እጸገነት ንግግር ያደረጉ ሲሆን፣ በንግግራቸውም የኢትዮጵያ መንግስት በተለያዩ ምክንያቶች ከአገር የወጡ ዜጎች በሚኖሩባቸው አገሮች መብታቸውና ደህንነታቸው ተጠብቆ እንዲኖሩ ከየትኛውም ጊዜ በላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸው፣ በዚህ አዲስ አገልግሎት ዜጎች ሁሉንም አይነት ከፓስፖርት ጋር ተያያዥ የሆኑ አገልግሎቶችን ባሉበት አገር ሆነው ያለምንም መንገላታትና ተጨማሪ የጉዞ ወጪ እንዲያገኙ መደረጉ የዚሁ መንግስት እየተከተለው ያለው የዜጎችን መብትና ደህንነት የማክበር ፖሊሲ የትግበራ አካል ነው ብለዋል፡፡

ዜጎች ይህን አገልግሎት ለማግኘት መከተል የሚገባቸው ሂደቶች፡-

1. https://immigration.gov.et ፖርታልን በመጠቀም አካውንት መክፈት (USER Name እና Password ማስገባት)፣

2. Send OTP የሚለውን በመጫን በኢሜል የሚላከውን OTP ማስገባትና ማረጋገጥ፣

3. ወደ አካውንትዎ ከገቡ በኋላ የሚፈልጉትን አገልግሎት ዓይነት እና ኤምባሲውን መምረጥ፣
4. የሚያስፈልጉ የግል መረጃዎችን መሙላት፣ የቀጠሮ ቀንና ሰዓት መምረጥ (ከምዝገባ ቀን ጀምሮ ከ45 - 90 ባሉት ቀናት እና ከተቀመጠው ሰዓት አንዱን መምረጥ)

5. የሚያስፈልጉ ሰነዶችን ማያያዝ (ፓስፖርት፣ የጋብቻ ምስክር ወረቀት፣ ወዘተ)፣

6. የማመልከቻ መረጃ በጥንቃቄ መሞላቱን ማረጋገጥ፣

7. የሚጠይቀውን ክፍያ በሲስቴም መፈፀም፣ (በሲስቴም ለመክፈል visa card ወይም master card ያስፈልጋል)

8. ለክትትልዎ ያመች ዘንድ የማመልከቻውን Confirmation ፕሪንት በማድረግ ወይም በሶፍት ኮፒ ማስቀመጥ፣

9. በቀጠሮዎ መሠረት ካምፓላ (ዩጋንዳ) ወደ ሚገኘው ኤምባሲ በአካል በመቅረብ የባዮ ሜትሪክ መረጃ መሰጠት፣

10. ቀጣይ በሚሰጠው ቀጠሮ መሠረት ፓስፖትዎን መረከብ፣

ማመልከቻን በመሙላት ሂደት ለሚገጥማችሁ ማንኛውም ችግር በኤምባሲው ስልክ ቁጥር +256 414341881 ደውለው ይጠይቁ።

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኤምባሲ
ካምፓላ

23/10/2026

ጎንደር ላይ የክብር ካባ ለብሰዋል👌

23/10/2026
23/10/2026
Today, H.E. Ambassador Etsegenet Yimenu  received a courtesy visit from Mr. Njima Ben Bolt, Chairman of the Pan-African ...
21/10/2026

Today, H.E. Ambassador Etsegenet Yimenu received a courtesy visit from Mr. Njima Ben Bolt, Chairman of the Pan-African Movement, Uganda National Chapter.

The two sides discussed ways to strengthen cooperation and enhance future collaboration to advance the shared Pan-African goals.

The Ministry of Foreign Affairs of Ethiopia Ministry of Foreign Affairs, Republic of Uganda Etv English Language World

Address

Prince Charles Drive
Kampala

Opening Hours

Monday 09:00 - 16:00
Tuesday 09:00 - 16:00
Wednesday 09:00 - 16:00
Thursday 09:00 - 16:00
Friday 09:00 - 16:00

Telephone

+256414341881

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Embassy Kampala posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share