03/06/2026
lemi kura woreda 08 communication1
መረጃ ሀብት ነው
03/06/2026
03/06/2026
የወርሀ ሚያዝያ እና ግንቦት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቁልፍ ተግባራት ቅኝት
03/06/2026
03/06/2026
“የኢትዮጵያ ሕዝብ እና መንግሥት በራሳቸው ሊኮሩ ይገባል” - ኡሁሩ ኬንያታ
የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን እና የኢጋድ ታዛቢ ቡድን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሂደት አስመልክቶ የመጀመሪያ ዙር የግምገማ ውጤት ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።
የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ የሆኑት የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ እና መንግሥት በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ ባሳዩት ድንቅ የሆነ አፈጻጸም በራሳቸው ሊኮሩ ይገባል ብለዋል።
“ኢትዮጵያውያን ከማለዳው ጀምሮ በቁርጠኝነት ለመምረጥ ተሰልፈዋል፤ ይህን ታላቅ ሁነት በኢትዮጵያ የተለያዩ ቦታዎች ተመልክተነዋል፤ እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ የታዘብነው ምርጫ በስኬት በመጠናቀቁ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ” ሲሉ አጠቃላይ ሁኔታውን ገልጸውታል።
“ኢትዮጵያውያን ታሪክ ይሠራሉ፤ ቀኝ ገዢዎችን በጋራ ተዋግተዋል፤ ይህም በአፍሪካ ብቸኛ ሀገር እንድትሆን አስችሏታል፤ የአፍሪካ የነፃነት ምልክቷ ኢትዮጵያ ነች” ብለዋል።
የአፍሪካ ኅብረት ምርጫውን ለመታዘብ ቀጠሮ ከያዘ ጊዜ ጀምሮ የምርጫውን ታማኝነት እና ዴሞክራሲያዊነት ስንከታተል ነበር ያሉት ኡሁሩ ኬንያታ፣ ምርጫ ቦርድ ቀደም ብሎ የሠራው ሥራ መራጮች ሳይደናገሩ ድምፅ እንዲሰጡ እንዳስቻለ አንሥተዋል።
በምርጫው ዕለት የፖለቲካ ፓርቲ ታዛቢዎች የምርጫውን ሂደት በነጻነት ሲከታተሉ እንደነበር ጠቁመው፣ “በዚህም የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ያለውን ታላቅ ቁርጠኝነት የታዘብንበት ነበር” ብለዋል።
03/06/2026
በወረዳ 08 አስተዳደር የአገልግሎት አሰጣጥ ምልከታ ተካሄደ።
ለሚ ኩራ ወረዳ 08 ኮሙኒኬሽን ግንቦት 26/2018 ዓ.ም
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት የሲቪል ምዝገባ እና ነዋሪዎች አገልግሎት ጽ/ቤት የአገልግሎት አሰጣጥ ሁኔታን ምልከታ አካሂዷል ።
አቶ ተረፈ ወ/ሚካኤል የአገልግሎት አሰጣጡን አስመልክተው እንደተናገሩት ጽ/ቤቱ የቴክኖሎጅ አሰራሮችን በመዘርጋት በስነምግባር በታነጹ ባለሙያዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ አገልግሎት ማግኘታቸውን የተናገሩ ሲሆን አንዳንዴ የሲስተም መቆራረጥ ማየታቸውን ገልጸው የወረዳ አስተዳደሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት የአገልግሎት አሰጣጡ መዘመኑን ገልፀዋል፡፡
03/06/2026
03/06/2026
የአውሮፓ ኅብረትና አጋር ሀገራት የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሒደት አደነቁ
የአውሮፓ ኅብረት እና አጋር ሀገራት ግንቦት 24/2018 ዓ.ም የተካሄደውን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አድንቋል፡፡
ምርጫውን አስመልክቶ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ካደረጉ የኅብረቱ አባል ሀገራትና በኢትዮጵያ የካናዳ፣ የኖርዌይ እና ስዊዘርላንድ ኤምባሲዎች የጋራ መግለጫ አውጥተዋል፡፡
ሀገራቱ በመግለጫቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ እጩዎችና የሲቪል ተቋማት ጠቅላላ ምርጫው በስኬት እንዲካሄድ ያደረጉትን አስተዋጽኦ አድንቀዋል፡፡
የአፍሪካ ኅብረት እና የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) በምርጫው ላይ ለነበራቸው የታዛቢነት ሚና እውቅና እንደሚሰጡም ሀገራቱ አረጋግጠዋል፡፡
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Website
Address
Addis Ababa
