Ministry of Education Ethiopia

Ministry of Education  Ethiopia

Share

This is FDRE Ministry of Education Official Face Book Page.We are promoting Educational Achievement & Attainment.

Photos from Ministry of Education  Ethiopia's post 31/05/2026

በኢትዮጵያና በቤልጂየም መካከል ያለው የከፍተኛ ትምህርት አካዳሚክ ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተደረገ።

-------------------------- // -----------------------

‎(ግንቦት 23/2018 ዓ.ም) የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፉ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ በኢትዮጵያ የቤልጅየምን አምባሳደር የሆኑትን ዶ/ር አኔሊስ ቬርስቲቼልን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።


ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው በዚሁ ጊዜ በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ እየተተገበሩ ስላሉ ዋና ዋና የሪፎርም ተግባራት ለክብርት አምባሳደሯ አብራርተዋል።


‎በሁለቱ አገራት መካከል በትምህርት መስክ በሰው ኃይል ልማት ፣ በጥናትና ምርምር ፣በልምምድ ልውውጥና በሌሎችም ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ የትብብር ግንኙነቶች መኖሩን አንስተዋል።


‎የትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርስቲ ራስገዝነትን ጨምሮ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ጥራት፣ ብቃትና ተወዳዳሪነት ለማሳደግ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝም ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ጠቅሰዋል።


‎በኢትዮጵያና ጅቡቲ የቤልጂየም አምባሳደርና የአፍሪካ ሕብረት የኢጋድና የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ቋሚ ተወካይ ዶክተር አኔሊስ ቨርስቲቼል በበኩላቸው በኢትዮጵያና በቤልጂየም መንግስታት መካከል 120 ዓመታትን ያስቆጠረ ወዳጅነትና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መኖሩን ተናግረዋል።


‎በተለይም በከፍተኛ ትምህርቱ ዘርፍ ባለው የትብብር ግንኙነት ባለፉት ዓመታት በርካታ ኢትዮጵያውያን በቤልጂየም ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ነጻ የትምህርት እድል ተጠቃሚ እንደሆኑ አብራርተዋል።


‎በሁለቱ አገራት መካከል በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ያለው የአካዳሚክ ትብብር ለወደፊቱም ተጠናክሮ እንዲቀጥል አገራቸው በጋራ መሥራት እንደምትፈልግም ዶ/ር አኔሊስ ተናግረዋል።


‎በመጨረሻም ሁለቱ ወገኖች በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ያለውን የአካዳሚክ ትብብር በምርምር፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በመምህራንና ተማሪዎች ልውውጥ እንዲሁም በአቅም ግንባታ መስኮች የበለጠ ለማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት አድርገዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት ማስፈንጠሪያዎች ያግኙ፡-
በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
ዩቱዩብ- https://www.youtube.com/-of-education-ethiopia
በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/.../ministry-of-education-ethiopia
በዌብሳይት - www.moe.gov.et ይከታተሉ

26/05/2026
Photos from Ministry of Education  Ethiopia's post 26/05/2026

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ከመንግስት የሚሰጥ የበጀት ድጋፍ አፈጻጸም ረቂቅ ደንብን አጸደቀ።

(ግንቦት 18/2018 ዓ.ም) የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 55ኛ መደበኛ ስብሰባ፣ ለራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ከመንግስት የሚሰጥ የበጀት ድጋፍ አፈጻጸምን ለመደንገግ በቀረበው ረቂቅ ደንብ ላይ በስፋት ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

በዚህም ምክር ቤቱ በረቂቅ ደንቡ ላይ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ፣ አስፈላጊ ግብአቶችን በማከል ደንቡ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን በሙሉ ድምፅ አጽድቆታል።

ደንቡ ለራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠውን የመንግስት የበጀት ድጋፍ በታወቀ የጥቅል በጀት ስርዓት ላይ በመመስረት፣ የፋይናንስ ተጠያቂነትን፣ ፍትሃዊነትን እና ውጤታማነትን ለማረጋገጥ ያለመ ሲሆን፣ ዩኒቨርሲቲዎች የራሳቸውን ወጪ በራሳቸው የመሸፈን አቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ እንዲያሳድጉ ያግዛል።

በተጨማሪም፣ በተቋማቱ መካከል ተመጣጣኝ የመማርና ማስተማር ጥራት፣ የአገልግሎት ፍትሃዊነት እና ኃላፊነት የተሞላበት አሰራር እንዲጠናከር ያስችላል።
ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት ማስፈንጠሪያዎች ያግኙ፡-
በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
ዩቱዩብ- https://www.youtube.com/-of-education-ethiopia
በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/.../ministry-of-education-ethiopia
በዌብሳይት - www.moe.gov.et ይከታተሉ See less

Photos from Ministry of Education  Ethiopia's post 21/05/2026

በትምህርት ሚኒስቴር፣ በውጭ አገራት የጋራ ሀብት ልማት ቢሮ (FCDO) እና በብሪቲሽ ካውንስል መካከል የ5 ሚሊዮን ፓውንድ ስምምነት ተፈረመ፤
----------------------------- // ----------------------------

(ግንቦት 13/2018 ዓ.ም) በትምህርት ሚኒስቴር፣ በዩናይትድ ኪንግደም የውጭ አገራት የጋራ ሀብት ልማት ቢሮ (FCDO) እና በብሪቲሽ ካውንስል መካከል በኢትዮጵያ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርትን ለማሻሻል የሚያስችል የሶስትዮሽ ስምምነት ተፈራርመዋል።


በለንደን ከተማ እየተካሄደ ከሚገኘው የአለም የትምህርት ፎረም 2026 ጎን ለጎን የትምህርት ሚኒስቴር፣ በውጭ አገራት የጋራ ሀብት ልማት ቢሮ (FCDO) እና በብሪቲሽ ካውንስል መካከል የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርትን ለማጠናከርና ለማሻሻል የሚያስችል የአምስት ሚሊየን ፓውንድ ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱ በኢትዮጵያ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ጥራትን ለማሻሻል፣ የመምህራን አቅምን ለማጎልበት እና የተማሪዎችን የቋንቋ ክህሎት ተገልጿል።

ይህ ስምምነት የአምስት ሚሊየን ፓውንድ ፕሮጀክት ሲሆን በኢትዮጵያ የእንግሊዝኛ ቋንቋን በማሻሻል ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋልም ተብሏል።

በተጨማሪም ስምምነቱ በትምህርት ዘርፉ ያለውን ዓለም አቀፍ ትብብር የሚያጠናክር ሲሆን፣ ተማሪዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሚያደርጋቸውን የቋንቋ ክህሎት እንዲያዳብሩ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።

ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት ማስፈንጠሪያዎች ያግኙ፡-
በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
ዩቱዩብ- https://www.youtube.com/-of-education-ethiopia
በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/.../ministry-of-education-ethiopia
በዌብሳይት - www.moe.gov.et ይከታተሉ

Photos from Ministry of Education  Ethiopia's post 21/05/2026

በአጣዬ ከተማ በትምህርት ሚኒስቴር ድጋፍ የተገነባ የአጣዬ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማስፋፊያ ፕሮጀክት ተመረቀ፤

------------------------ // ----------------------

(ግንቦት 13/2018 ዓ.ም) በትምህርት ሚኒስቴር ድጋፍ በአጣዬ ከተማ የተገነባው የአጣዬ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመማሪያ ክፍል ማስፋፊያ ፕሮጀክት ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።

ትምህርት ሚኒስቴር ከ33 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ያስገነባው ይህ ፕሮጀክት ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎችን እና ዘመናዊ መፀዳጃ ቤቶችን ያካተተ ሲሆን የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች፣ የአካባቢው አስተዳደር፣ የትምህርት ዘርፍ ኃላፊዎች እና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በይፋ ተመርቋል።

የግንባታ ፕሮጀክቱ 10 ዘመናዊ የመማሪያ ክፍሎችን ያካተተ ሲሆን፣ ለወንድና ለሴት ተማሪዎች የተለያዩ መፀዳጃ ክፍሎችን ይዟል።

ፕሮጀክቱ በአካባቢው የትምህርት ተደራሽነትን እና ምቹ የመማር ማስተማር ሂደትን ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረውም ተገልጿል።

በተጨማሪም በ“ትምህርት ለትውልድ” የትምህርት ቤቶች መሰረተ ልማት ማሻሻል ንቅናቄ የትምህርት ማህበረሰቡን፣ የቀድሞ ተማሪዎችን፣ ባለሃብቶችን መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን በማስተባበር በመላ ሀገሪቱ በሺዎች የሚቆጠሩ የአዳዲስ ትምህርት ቤቶች ግንባታ፣ የነባር ትምህርት ቤቶች ጥገና እና የትምህርት ተቋማት መሰረተ ልማት ማሻሻያ ሥራዎች በስፋት እየተከናወነ እንደሚገኝ ይታወቃል።

ትምህርት ሚኒስቴር በሁሉም አካባቢዎች ፍትሃዊና ሁሉን አቀፍ ጥራት ያለው ትምህርትን ተደራሽ ለማድረግ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል።

ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት ማስፈንጠሪያዎች ያግኙ፡-
በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
ዩቱዩብ- https://www.youtube.com/-of-education-ethiopia
በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/.../ministry-of-education-ethiopia
በዌብሳይት - www.moe.gov.et ይከታተሉ

Photos from Ministry of Education  Ethiopia's post 21/05/2026

ኢትዮጵያ በለንደን በተካሄደው ዓለም አቀፍ የትምህርት ፎረም 2026 በትምህርቱ ዘርፍ ያላትን ተሞክሮ አካፈለች፤

---------------------- // ----------------------

ኢትዮጵያ በለንደን ከተማ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የትምህርት ፎረም 2026 ላይ ፍትሃዊ፣ ሁሉን አቀፍ እና ጥራት ያለው የትምህርት ሥርዓት በመገንባት ረገድ ያላትን ልምድ አቅርባለች።

በዚሁ ጊዜ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በፎረሙ ላይ ኢትዮጵያ በትምህርት ተደራሽነት፣ አካታችነት እና የትምህርት ጥራት ማሻሻያ ዙሪያ ያከናወነቻቸውን ተግባራት አብራርተዋል።
በዚህም፦

✅ በገጠርና አገልግሎት በማይደርስባቸው አካባቢዎች ትምህርት ቤቶችን በመገንባት የትምህርት ተደራሽነትን ማስፋፋት፣

✅ የቅድመ ልጅነት እድገት (ECD) እና የቅድመ መደበኛ ትምህርትን ለማጠናከር የተወሰዱ እርምጃዎች፣

✅ የአካል ጉዳተኞችንና የልዩ ትምህርት ፍላጎት ያላቸውን ተማሪዎች የሚደግፉ አካታች ፖሊሲዎችን መተግበር፣

✅ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት የአፍ መፍቻ ቋንቋ ትምህርትን በማስፋፋት የተማሪዎችን ተሳትፎና መሰረታዊ ትምህርት ማሻሻል፣

✅ የሴቶችን የትምህርት ተሳትፎ እና ቆይታ ለማሳደግ የተሰሩ ሥራዎች፣

✅ ለአርብቶ አደርና ለመድረስ አስቸጋሪ ማህበረሰቦች አማራጭ የትምህርት ፕሮግራሞችን መተግበር፣

✅ የትምህርት ጥራትን፣ ፍትሃዊነትንና አካታችነትን ለማጠናከር የመምህራን ልማትን ማበረታታት የሚሉ ቁልፍ ተሞክሮዎች አቅርባዋል።

በመድረኩ ላይ ኢትዮጵያ ለሁሉም ዜጎች ፍትሃዊ፣ ሁሉን አቀፍ እና ጥራት ያለው ትምህርት ለማረጋገጥ ያላትን ቁርጠኝነት እንደገና አረጋግጣለች።

በተጨማሪም ክቡር ሚኒስትሩ ጎን ለጎን በተካሄደው የአፍሪካ ትምህርት ሚኒስትሮች መድረክ ላይ “በትምህርት ለትውልድ የትምህርት ቤቶች መሰረተ ልማት ማሻሻል” ንቅናቄ በህብረተሰብ ተሳትፎ የተከናወኑ ሰፊ የትምህርት ልማት ተግባራትን በማቅረብ የኢትዮጵያን ተሞክሮ አካፍለዋል።


ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት ማስፈንጠሪያዎች ያግኙ፡-
በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
ዩቱዩብ- https://www.youtube.com/-of-education-ethiopia
በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/.../ministry-of-education-ethiopia
በዌብሳይት - www.moe.gov.et ይከታተሉ

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address


Arat Kilo/Patriot Square
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:30
Tuesday 08:00 - 17:30
Wednesday 08:00 - 17:30
Thursday 08:00 - 17:30
Friday 08:00 - 17:30